Get Mystery Box with random crypto!

ጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ምቹ የስልጠና እና የስራ  አካባቢ በመፍጠር ሂደት አበረታች ለውጦችን ማስ | Addis Ababa Technical Vocational Training and Technology Development Bureau

ጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ምቹ የስልጠና እና የስራ  አካባቢ በመፍጠር ሂደት አበረታች ለውጦችን ማስመዝገቡን ገለፀ

ነሐሴ ፤ 19 ቀን 2014 ዓ.ም

ጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ምቹ የስልጠና እና የስራ አካባቢ በመፍጠር ሂደት አበረታች ለውጦችን ማስመዝገቡን ገልጿል፡፡

ኮሌጁ በስልጠና ሂደት የሚስተዋሉ የግብአት አጠቃቀም እና የምርት ብክነት ሊቀንስ በሚችል መልኩ የካይዘን ፍልስፍና ተግባራዊ በማድረግ አመርቂ  ውጤት መመዝገቡን የኮሌጁ  የተቋማት አቅም ግንባታ ምክትል ዲን አቶ ጎሳዬ አለሙ ተናግረዋል፡፡

ስለ ካይዘን ፍልስፍና የኮሌጁን ማህበረሰብ አቅም በማሳደግ ወደ ተግባር መገባቱን የሚናገሩት አቶ ጎሳዬ አሁን ላይ ከ5ቱ "ማ" ዎች የመጨረሻ  የሚባለው ማላመድ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል፡፡

ለዚህም በየስራ ክፍሉ የካይዘን ትግበራ ሂደቱን የሚከታተል "ከልቡ" የተሰኘ ኮሚቴ አይነተኛ ሚና እንደተጫወተ ይነገራል፡፡

ኮሌጁ የካይዘን ፍልስፍናን በሚገባ በመረዳት ወደ ተግባር በመግባቱ ምቹ የስልጠና እና የስራ አካባቢ መፍጠር ተችሏል  እንዲሁም የንብረት አያያዝና አጠቃቀም ማሻሻል ችሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኮሌጁ ስታንዳርዱን የጠበቀ ወርክሾፖች ባለቤት ከመሆኑም በላይ በካይዘን ፍልስፍና በከተማዋ ካሉ ተቋማት ግንባር ቀደም በመሆን ልምዱን ለሌሎች  ተቋማት በማጋራት ላይ ይገኛል፡፡

በቀጣይም በሀገር አቀፍ ደረጃ እንዲሁም በምስራቅ  አፍሪካ ደረጃ  ዕውቅና ለማግኘት እንቅስቃሴ መጀመሩን የተቋማት አቅም ግንባታ ምክትል ዲን አቶ ጎሳዬ አለሙ ጠቁመዋል፡፡