Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

የቴሌግራም ቻናል አርማ aasundayschool — የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የቴሌግራም ቻናል አርማ aasundayschool — የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የሰርጥ አድራሻ: @aasundayschool
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.84K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ልሳን ነው።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-27 16:55:12 +++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
"
#ቅዱስነታቸው_ቤተክርስቲያን_ይወክላሉ!!!
#እሳቸው_ባሉበት_ኹሉ_ቤተክርስቲያን_አለች!!!
#እሳቸውን_የሚናገር_እየተደፋፈረ_ያለው_ቤተክርስቲያንን_ነው!!! "

የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ፥ የኒዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም መግለጫ ሰጡ።

የሐዋ. ፳፫፥፭ "በሕዝብህ አለቃ ላይ ክፉ ቃል አትናገር" የሚለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መነሻ በማድረግ መግለጫውን የጀመሩት ብፁዕ አቡነ አብርሃም በአንድ ቅዱስ ፓትርያርክ ላይ በጥራዝ ነጠቅነት የተሳሳተ መረጃ መስጠት ትክክል አለመሆኑን በመጥቀስ ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ይወክላሉ። እሳቸው ባሉበት ኹሉ ቤተ ክርስቲያን አለች። እሳቸውን የሚናገር እየተደፋፈረ ያለው ቤተ ክርስቲያንን ነው። በዚህም ቤተ ክርስቲያን ታዝናለች" ብለዋል።

በሀገር ውስጥና በውጭ ላለችው ቤተ ክርስቲያን አባት የሆኑ አባትን በዚህ መንገድ መናገር ሉዓላዊ የሆነች የኢ/ኦ/ቤ/ክንን እና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምእመናንን መድፈር ነው ያሉት ብፁዕነታቸው
ቤተ ክርስቲያንን በመከፋፈል ትርፍ ማግኘት አይቻልም ሲሉ አብራርተዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናትን በውጪ ሀገር መትከል ከጀመረች ጀምሮ ጽላት በአሠራሯ መሠረት ትልካለች። የታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት እና ልጆቿ በረሃብ እየተገረፉ የጠበቁትን ሁኖ ሳለ ቤተ ክርስቲያን ቅርስ ታሸሻለች ብሎ ማሰብ ንስሐ ያስገባል። ይህ የቅዱስነታቸውን ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን ክብር መንካት ነው ብለዋል።

መንግሥት ለምን ብሎ መጠየቅ እና መመርመሩ ተገቢ ነው። ነገር ግን ቅርጽና ቅርስ መለየት ያስፈልጋል። በቀጣይም በጉዳዮ ላይ ግልፅነት ለመፍጠር ከሚመለከተው የመንግሥት አካል ጋር በቀጣይ እንወያያለን በማለት በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
2.6K viewsBereket kebede, 13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 16:54:13
1.6K viewsBereket kebede, 13:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 08:08:24
ከቅዱስ ፓትርያርኩ የሕክምና ጉዞ ጋር በተያያዘ በሚናፈሱ የተዛቡ መረጃዎች ዙሪያ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል!!!

በቅዱስ ፓትርያርኩ ጉዞ ላይ በቦሌ ኤርፖርት ከተፈፀመው አሳዛኝ ድርጊት ጋር ተያይዞ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ከቀኑ 8:30 ላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነት በጉዳዩ ላይ መግለጫ ይሰጣሉ።
2.2K viewsBereket kebede, 05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 16:59:59

1.6K viewsBereket kebede, 13:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 07:41:51
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለሕክምና ወደ ሰሜን አሜሪካ ተጓዙ!!!

ቅዱስነታቸው በዛሬው ዕለት ወደ ሰሜን አሜሪካን የተጓዙ ሲሆን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በመንበረ ፓትርያርክና በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ተገኝተው አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ.ም የቤተክርስቲያኒቱ ቋሚ ሲኖዶስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ውጭ ተጉዘው እንዲታከሙ በወሰነው ውሳኔ መሠረት ብፁዓን አባቶች በተገኙበት ይፋዊ መግለጫ ሰጥተው በዛሬው ዕለት ወደሰሜን አሜሪካ አቅንተዋል።

የሰሜን አሜሪካ ዋሸንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት እንዲሁም የሰሜን አሜሪካ ካህናት ኅብረት ሀገረ አሜሪካ ሲደርሱ አቀባበል እንደሚያደርጉላቸው በመግለጫቸው አረጋግጠዋል።

በሰላም በጤና ወደ መንበረ ፕትርክናቸው ይመልስልን !!!የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን!!!
1.5K viewsBereket kebede, edited  04:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 11:12:05
ሐምሌ 24/2014 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አዳራሽ በመገኘት እህት ወንድሞቻችን ልጆቻችን ለፍሬ የሚበቁባትን ሰ/ት/ቤታችንን እንደግፍ።
የመዝሙር ሲዲው ሙሉ ገቢ ለመካነ ጎልጎታ ድልበር መድኃኔዓለም እምነት ፥ ተስፋ ፥ ፍቅር ሰንበት ት/ቤት
1.4K viewsBereket kebede, 08:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 07:34:19


የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የማጠናቀቂያ ምዘና በሁሉም ክፍለ ከተሞች በተሳካ መልኩ ተከናወነ።

በዘንድሮው ዓመት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ እና ትምህርታቸውን ሲካተታሉ የነበሩ ከሁሉም ክፍለ ከተማ
#የ4ኛ#የ6ኛ እና #የ10 ክፍል አራት ሺህ ሰማንያ ሰባት {4087} ሰንበት ተማሪዎች #ሐምሌ_17_2014_ዓ_ም ከቀኑ 4:00 -7:00 ሰዓት ድረስ የትምህርት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ምዘና የተደረገ ሲሆን በሁሉም ክፍለ ከተማ በእግዚአብሄር ፍቃድ በተሳካ መልኩ ምዘናው ተጠናቋል።

በነበረው የምዘና (የፈተና) አገልግሎት በማስተባበር ፥ በመፈተንና በማስፈተን ለተሳተፋችሁ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ ዋጋችሁን ይክፈልልን ሲል የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መደበኛ አገልግሎት ማስተባበሪያ ክፍል ምስጋናውን አቅርቧል።

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስተባበሪያ ክፍል !!

4.0K viewsBereket kebede, 04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ