Get Mystery Box with random crypto!

የብቃት ምዘና ፈተና ለወሰዳችሁ ተመዛኞች በሙሉ! በ Medicine, Nursing, Public H | Addis Ababa City Administration Health Bureau

የብቃት ምዘና ፈተና ለወሰዳችሁ ተመዛኞች በሙሉ!

በ Medicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ ከግንቦት 14 - 18/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከሰኔ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በአካል መምጣት ሳይጠበቅባችሁ በስልክ ቁጥር 0118275936/952 በመደወል ወይም በኢሜይል hpcald@moh.gov.et ላይ ሙሉ ስም፣ ሙያ ፣ የፈተና መለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን ተቋም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

@MoHEthiopia