Get Mystery Box with random crypto!

በጤና ተቋማት እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለ | Addis Ababa City Administration Health Bureau

በጤና ተቋማት እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የአዲስ በባ አከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በጤና ጣቢያ እየተሰጠ ያለውን የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ እና በጤና ተቋማት የተደረገውን ድጋፋዊክትት ከክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት እና የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ጋር ገምግሟል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ ቢሮው በጤና ጣቢያዎች ያለውን አገልግሎት አሰጣጥ አስመልክቶ ድንገታዊ ምልከታ በማድረግ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥን እና የሪፎርም ትስስርን መሰረት ያደረገ አገልግሎት ያለበት ሁኔታን ዳሰሳ መሰራቱ ተገልጿል፡፡

በምልከታው የታዮ ጤና ጣቢያዎች አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡

በውይይት መድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ አከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀንጋቱ መሀመድ በጤና ጣቢያዎች ዳሰሳዊዊ ምልከታ መካሄዱ ለህብረተሰቡ ጥራቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው መሰል ዳሰሰሠዊ ጥናቶችን አጠናክሮ በማድረግ የተገልጋዩን እርካታ ለመጨመር እና ወቅቱ የሚፈልገውን የጤና አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

በቢሮው የሜዲካል ሰርቪስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ጥሩነህ በበኩላቸው በጤና ተቋማት የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት እና ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋት ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

@AACAHealthBureau
@MoHEthiopia