Get Mystery Box with random crypto!

Addis Ababa City Administration Health Bureau

የቴሌግራም ቻናል አርማ aacahealthbureau — Addis Ababa City Administration Health Bureau A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aacahealthbureau — Addis Ababa City Administration Health Bureau
የሰርጥ አድራሻ: @aacahealthbureau
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.85K

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-08 21:52:33 የብቃት ምዘና ፈተና ለወሰዳችሁ ተመዛኞች በሙሉ!

በ Medicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ ከግንቦት 14 - 18/2015 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከሰኔ 1/2015 ዓ.ም ጀምሮ hple.moh.gov.et ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration No) በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በአካል መምጣት ሳይጠበቅባችሁ በስልክ ቁጥር 0118275936/952 በመደወል ወይም በኢሜይል hpcald@moh.gov.et ላይ ሙሉ ስም፣ ሙያ ፣ የፈተና መለያ ቁጥር እና የተማራችሁበትን ተቋም በመሙላት ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

@MoHEthiopia
318 views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 05:18:11
በጤና ተቋማት እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ውጤታማ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የአዲስ በባ አከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በጤና ጣቢያ እየተሰጠ ያለውን የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ እና በጤና ተቋማት የተደረገውን ድጋፋዊክትት ከክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት እና የጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ጋር ገምግሟል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ ቢሮው በጤና ጣቢያዎች ያለውን አገልግሎት አሰጣጥ አስመልክቶ ድንገታዊ ምልከታ በማድረግ ህክምና አገልግሎት አሰጣጥን እና የሪፎርም ትስስርን መሰረት ያደረገ አገልግሎት ያለበት ሁኔታን ዳሰሳ መሰራቱ ተገልጿል፡፡

በምልከታው የታዮ ጤና ጣቢያዎች አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡

በውይይት መድረኩ የተገኙት የአዲስ አበባ አከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሀንጋቱ መሀመድ በጤና ጣቢያዎች ዳሰሳዊዊ ምልከታ መካሄዱ ለህብረተሰቡ ጥራቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ጠቀሜታው ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው መሰል ዳሰሰሠዊ ጥናቶችን አጠናክሮ በማድረግ የተገልጋዩን እርካታ ለመጨመር እና ወቅቱ የሚፈልገውን የጤና አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል ተናግረዋል፡፡

በቢሮው የሜዲካል ሰርቪስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መልካሙ ጥሩነህ በበኩላቸው በጤና ተቋማት የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት እና ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋት ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ለመስጠት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

@AACAHealthBureau
@MoHEthiopia
862 views02:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 07:29:18



@MoHEthiopia
546 views04:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-06 07:28:12
በአዲስ አበባ እየተሰሩ ያሉ ሜጋ ፕሮጀከክቶችና በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ሆስፒታሎች ላይ እየተሰጠ ያለውን የጤና አገልግሎቶች ተጎብኝተዋል።

በጎብኝቱ ከታዩት ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል የአድዋ ሙዚዮም ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት ፣ የለሚኩራ እንጀራ መጋገሪያ ፕሮጀክት፣ የአበበች ጎበና የእናቶችና ህጻናት ሆስፒታል ወረቀት አልባ /ዲጂታል የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ፣ የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ማእከል እና የአይን ህክምና ማዕከል ለህሙማን እየሰጠ ያለውን አገልግሎት መጎብገኘት ተችሏል።

በጉብኝቱ የተገኙት የአ/አ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመመደብ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆኑን ገልጸው በተለይም ለጤናው ሴክተር ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ላይ አዳዲስ ማስፋፊያና የህክምና ማዕከል በመገንባት፣ ዘመናዊ የህክምና መሣሪያዎችን በማሟላት ወደተግባር ተገብቶ የህብረተሰቡን የጤና ችግር ለመፍታት በቁርጠኝነት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የአበበች ጎበና እናቶችና ህጻናት ሆስፒታል የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፐርንሲቭ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ህክምና ማዕከል እና የአይን ህክምና ማዕከል አገግሎት እንዲሰጥ መደረጉ ለህብረተሰቡ ትልቅ እፎይታን የፈጠረ መሆኑንም ገልፀዋል።

በጉብኝቱ ለጎብኝዎች በሚመለከታቸው ባለሙያናዎች ገለጻና ማብራሪያ የተደረገ ሲሆን በምልከታቸው ባዩት ነገር መደሰታቸውንና መንግስ በየዘርፋ እየሰራ ያለውን የልማት ስራ አድንቀው በተሰማሩበትየስራ መስክ ለበለጠ ትጋት እንደሚያነሳሳቸው ትምህር ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

@AACAHealthBureau
@MoHEthiopia
873 views04:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 07:36:34
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ በዓሉ ሠላም፣ ፍቅር ፣ ጤና እና ደስታ በቤታችሁ የሚሞላበት በዓል እንዲሆን እየተመኘን በተለይም በዓሉን ምክንያት በማድረግ መሰባሰብ ባለባቸው ቦታዎች የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማክስ በመጠቀም ፣ ከግብይት በኋላ እጅዎን በሳሙና /በሳኒታይዘር በማጽዳት ራስዎንና ቤተሰብወን ከኮቪድ 19 በሽታ እንዲጠብቁ እያሳሰብን መልካም በአል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ !!

@AACAHealthBureau
170 viewsedited  04:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 23:36:24
ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 3,695 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ 35 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በአጠቃላይ እስካሁን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 470,833 ደርሷል። በሌላ በኩል 3 ሰዎች ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 455,746 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
Status update on #COVID19Ethiopa

ወቅታዊና የተሟላ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ/Website: https://www.moh.gov.et
ፌስቡክ/Facebook: Ministry of Health Ethiopia
ቲውተር/Tiwteer: twitter.com/FMoHealth
ዩቲዩብ/YouTube: tv.moh.gov.et/tv/
ቴሌግራም/Telegram: @MoHEthiopia
ይጠቀሙ ፡፡
እናመሰግናለን፡፡
1.4K views20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 23:36:24
1.3K views20:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 04:32:12
1.0K views01:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 23:00:49
በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ኮሌጅ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል HCP በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት እገዛ 500 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና /CATARACT SURGERY/ ከ ሰኔ 6-12/2014 ዓ.ም ለማድረግ አስቧል፡፡ ስለሆነም ይህን የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ቅድመ ምርመራ፣ልየታና ምዝገባ በግንቦት ወር ባሉት ቅዳሜና እሁድ ቀናቶች ማለትም (ግንቦት 6፣7፣13፣14፣20፣21፣27፣28 ) ስለምናደርግ በኮሌጁ የስልክ አገልግሎት 976 በመደወል ለቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ ቀጠሮ እንድትይዙ ስንል በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- በስልክ ቀጠሮ ያልተሰጠዉ ታካሚ ቅድመ ምርመራም፣ ልየታም ይሁን ምዝገባ ማድረግ አይችልም፡፡

#SPHMMC
#MoHEthiopia

@MoHEthiopia
866 views20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 23:00:39
725 views20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ