Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ እየተሰሩ ያሉ ሜጋ ፕሮጀከክቶችና በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ሆስፒታሎች ላይ | Addis Ababa City Administration Health Bureau

በአዲስ አበባ እየተሰሩ ያሉ ሜጋ ፕሮጀከክቶችና በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ሆስፒታሎች ላይ እየተሰጠ ያለውን የጤና አገልግሎቶች ተጎብኝተዋል።

በጎብኝቱ ከታዩት ሜጋ ፕሮጀክቶች መካከል የአድዋ ሙዚዮም ዜሮ ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት ፣ የለሚኩራ እንጀራ መጋገሪያ ፕሮጀክት፣ የአበበች ጎበና የእናቶችና ህጻናት ሆስፒታል ወረቀት አልባ /ዲጂታል የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ፣ የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ማእከል እና የአይን ህክምና ማዕከል ለህሙማን እየሰጠ ያለውን አገልግሎት መጎብገኘት ተችሏል።

በጉብኝቱ የተገኙት የአ/አ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሙሉጌታ እንዳለ ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመመደብ እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆኑን ገልጸው በተለይም ለጤናው ሴክተር ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ላይ አዳዲስ ማስፋፊያና የህክምና ማዕከል በመገንባት፣ ዘመናዊ የህክምና መሣሪያዎችን በማሟላት ወደተግባር ተገብቶ የህብረተሰቡን የጤና ችግር ለመፍታት በቁርጠኝነት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የአበበች ጎበና እናቶችና ህጻናት ሆስፒታል የዳግማዊ ምኒልክ ኮምፐርንሲቭ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ህክምና ማዕከል እና የአይን ህክምና ማዕከል አገግሎት እንዲሰጥ መደረጉ ለህብረተሰቡ ትልቅ እፎይታን የፈጠረ መሆኑንም ገልፀዋል።

በጉብኝቱ ለጎብኝዎች በሚመለከታቸው ባለሙያናዎች ገለጻና ማብራሪያ የተደረገ ሲሆን በምልከታቸው ባዩት ነገር መደሰታቸውንና መንግስ በየዘርፋ እየሰራ ያለውን የልማት ስራ አድንቀው በተሰማሩበትየስራ መስክ ለበለጠ ትጋት እንደሚያነሳሳቸው ትምህር ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

@AACAHealthBureau
@MoHEthiopia