Get Mystery Box with random crypto!

ወሊድ ወይም የወር አበባ ላይ      ያለች ሴት ፆምን በተመለከተ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደ | وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا🌹🌹

ወሊድ ወይም የወር አበባ ላይ
     ያለች ሴት ፆምን በተመለከተ

የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም
     በማየት ላይ ያለች ሴት ፆም መፆም
     ሀራም ነው የሚሆንባት። እንዲያውም
     በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ከፆመች
     ወንጀለኛ ከመሆኗም በላይ ፆሙም
     ውድቅ(ባጢል) ነው።ማስረጃውም:–

እናታችን አዒሻ(ረዓ) ባስተላለፉት
      ሀዲስ:–"በነብዩ(ሰዐወ) ዘመን የወር
      አበባ እናይ ነበር። ፆምን ቀዷ
      እንድናወጣ ስንታዘዝ ለሰላት ግን ቀዷ
      አንታዘዝም ነበር።" ብላዋል።
      (ሙስሊም 335፣ አቡዳውድ 263)

በወር አበባ የወሊድ ደም ላይ ያለች
     ሴት በቀኑ መካከል ከወር አበባዋ
     ወይም ከወሊድ ደሟ ብትጠራ
     ቀሪውን ቀን ከምግብና የመሳሰሉት
     ነገሮች(ኢምሳክ) ማድረግ
     አይጠበቅባትም።መብላት መጠጣት
     ትችላለች።

ከእውነተኛውና ከትክክለኛው ፈጅር
     ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ከደሟ
     ፀድታ ከመታጠቧ በፊት ለፆም ኒያ
     ካደረገች ፆሟ ትክክል ነው።የሚታየው
     ደሙ መቆሙ ነውና።እንዲሁም ፆሟን
     ልታፈጥር(ፀሀይ ልትጠልቅ) ሽርፍራፊ
     ደቂቃዎች እየቀሩ የወር አበባ ደም
     ካየች ፆሟ ይበላሻል።ቀዷም
     ማውጣት ግዴታ ነው።

የበሽታ ደም እያየች ያለች ሴት
     ከመፆም የማትከለከል ሲሆን ፆሟን
     መቀጠል አለባት።በደሙ ምክንያት
     መፍታትም አትችልም።ስለዚህ ሴት
     እህቶቻችን የወር አበባቸውን በደንብ
     ለይተው ማወቅ ይገባቸዋል።
=====================
የሑረልዒይን የሱና መድረሳ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!!
https://t.me/hooral_ayn