Get Mystery Box with random crypto!

ለምን ይዋሻል ---------------------- ፊዳከ እያልን በቀንም በማታ ያ ነቢ እያልን | وَتَوَكَّلْ عَلَى ٱللَّهِ ۚ وَكَفَىٰ بِٱللَّهِ وَكِيلًا🌹🌹

ለምን ይዋሻል
----------------------

ፊዳከ እያልን በቀንም በማታ
ያ ነቢ እያልን ቃልን ሳንገታ
ሲያሻንም ስናለቅስ
ስንል መለስ ቀለስ
-----------------------
አቤት ስናስመስል
ውስጣችን ሳይበስል
እውነት ከወደድን
ሱናና ተውሂድን
ከልብ ከሆነ ፊዳከ ማለቱ
ታዳ ለምን ይሆን ሱሪ መጎተቱ

-----------------------------------
ክረምት ሲመጣ ትሰበስባለህ
ከጀሀነም ይልቅ ጭቃይቱን ፈርተህ
አቤት ማሳዘንህ
ከየትስ መቶ ነው ፂምን መላጨቱ
ማን ነበር የሚሏት ያች ስታይሊቱ
ትዝ አለኝ ኦ ቅርፅ ማውጣቱ
---------------------------------
ነብዩ እንዳላሉህ ይደግ ልቀቀው
ስለምቶዳቸው ትዛዙን ጣስከው
አይ ሰው ጉድ ነው
የፀጉር ስታይል አቆራረጥህ
የስሙ ብዛቱ ምኑን ልንገርህ
ፀጉርህን ስትቆርጥ እንዳታበላልጥ ብለው መክረውህ

---------------------------------
ሴትን አትጨብጥ
ከአጅ ነቢ ጋ ለብቻ አትቀመጥ
ከቻልክ አግባ ሲሉህ
ካልቻልክ ፁም ብለውህ
---------------------------
አይንህንም ሰበር አድርግ እንዳላሉህ
ዝሙትን ተጠንቀቅ አደራ ብለውህ
እሳቸውን ትተህ በስሜት ተመራህ
ይሄን ሁሉ አጥፍተህ
ቲኒሽም ሳይከብድህ
እኔን የገረመኝ ፊዳከ ማለትህ

----------------------------------
ነፍስህ ፊዳ ሳቶን
ምነው ተቀደሙ ሚስኪን ወላጆችህ
ሌላ ምን ይባላል አሏህ ይዘንልህ
ቀጥ ወዳለው መንገድ እሱ ይመልስህ
-------------
አሚን
አንችስ
ሂጃብ አሳጥረሽ
ፊትሽን ተገልጠሽ
ፎቅ ጫማ ላይ ወተሽ
ሽቶ ተቀባብተሽ

-----------------------
ስቶጭ ተኩለሽ ተኩለሽ ተኩለሽ
የቀለም አይነትን ፊትሽ ላይ ቀብተሽ
ደግሞ ስታወሪ ድምፅሽን ከፍ አርገሽ
ይህን መገለጫ ራቂ እንዳላሉሽ
----------------------------------
ያ ምርጡ ነብይሽ
ኢማን በልቤ ነው ስትይ ትውያለሽ
ፊዳከ ያ ረሱል እያልሽ ብሰማሽ
ነፍስሽ ፊዳ ሳቶን ለምን ትዋሻለሽ
እህቴ ሆይ አሏህ ይዘንልሽ
ግን ተው አንወሻሽ

---------------------------
ፍቅርን በተግባር ከሰው ካላገኘን
መቸ ይቀርና መሄዳችን ጥለን
የነብዩም ፍቅር ተግባር ይፈልጋል
ሱናቸውን ያዙ ከእሳት ያድናል::


https://t.me/umufwzan/5531