Get Mystery Box with random crypto!

ህይወት ጥበብ ፍልስፍና

የቴሌግራም ቻናል አርማ zolaarts — ህይወት ጥበብ ፍልስፍና
የቴሌግራም ቻናል አርማ zolaarts — ህይወት ጥበብ ፍልስፍና
የሰርጥ አድራሻ: @zolaarts
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 120
የሰርጥ መግለጫ

Qዳማዊw ነው ሰላምታዬ ✌ ማንኛውንም የስዕል ስራ ለመግዛት ወይም
ለማሳል ከፈለጉ ይደውሉ
👇👇👇👇
0935647014
አላማችንሰአሊዋችንማበረታት

Lift ባለማለት ተባበሩን🙏 @zolaarts

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-12 16:26:38
37 views+Zelalem..*Arts , 13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 14:40:00 ነፃነት
ኦሾ/Osho

# ነፃነትህን የሚያሳጣህ ጥገኝ የመሆን ፍላጎት ራስህን የመሆን ኃላፊነት ላለመሸከም ያለህ ፍላጎት ነው።

ሙሉ በሙሉ ነፃ ለመሆን ሙሉ በሙሉ ግንዛቤ ማግኘት አለብን ምክንያቱም የባርነት ስር መሠረቱ ያለው ባለማወቃችን ውስጥ ነው። ከውጭ የሚመጣ ነገር አይደለም ማንም ነፃነትህን ሊያሳጣ አይችልም። ጥፋት ሊደርስብህ ይችላል። ግን አንተ አሳልፈህ ካልሰጠኸው በስተቀር ነፃነትህን ሊወስድብህ አይችልም።

ጠልቀን ስንመረምረው ነፃነትህን የሚያሳጣህ ነፃነትን ለማግኘት ያለመፈለግህ ነው። ነፃነትህን የሚያሳጣህ ጥገኝ የመሆን ፍላጎት ራስህን የመሆን ኃላፊነት ላለመሸከም ያለህ ፍላጎት ነው።

ሰው ለራሱ ኃላፊነት ለመውሰድ በፈቀደ ጊዜ በነገራችን ላይ ይህን ማድረግ ሙሉ በሙሉ አስደሳች ነገር አይደለም በውስጡ እሾህና መራር ነገሮች ይገኙበታል። ጣፋጫ ነገር ሁሉ ሚዛናዊ ነገር እኩል በእኩል ተከትለው ይመጣሉ። ጽጌሬዳዎች ያለ እሾህ አይበቅሉም ቀናትን ሌሊትን ተከትለው ክረምቱ አብቅቶም ፀሐይ ትወጣለች። ሕይወት የተቃራኒ ነገሮች ሚዛን አጣጥማ ትኖራለች።

ራስን የመሆን ኃላፊነትን ከውበቱና ከመራርነቱ ፣ከደስታውና ከስቃዩ ጋር ለመቀበል ፍቃደኛ የሆነ ሰው ነፃ መውጣት ይችላል። ነፃ ሊሆን የሚችለው ይህን መሠል ሰው ብቻ ነው።

@zolaarts
39 views+Zelalem..*Arts , 11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 21:19:35 ‹‹በአዕምሮው ህልም የተያዘ ሰው በሕይወት ጉድጓድ መውደቁ አይቀርም››
---------------------------
፪ . . .
‹‹ማንም ሰው በጉዞ ላይ የሚገኝ አዕምሮውን እንዳሻው እንዲሄድ መፍቀድ የለበትም። ሥጋን እንደመለማመድና እንደመግዛት አዕምሮን መግዛት ቀላል አይደለምና። ለአዕምሮ የሚሰጥ ነፃነት እጅግ በጣም ጥቂትና ውሱን ሊሆን ይገባል። በተለይ ደግሞ አዕምሮን የሕይወት ዕድልና አጋጣሚ እንዳሻው እንዲያሽከረክራት መፍቀድ የማያቋርጥ ስቃይን በራስ ላይ እንደመጋበዝ ይቆጠራል።

እውነትና ፍፁም የሆነውን ነገር ሕይወት በአዕምሯችን ውስጥ ብታስቀምጥም አላዋቂነት ሁለቱንም እንደሌሉ አድርጎ እያሳየ ቅዠታችን ከፍቷል።›› በማለት ሳራስዋቲ ለእዚህ ተ ስማሚ የሆነ ወግ ያስከትላሉ።

‹‹ከሕንድ በአንዲት የገጠር ከተማ በልብስ አጣቢነቱ የታወቀ አንድ ሰው ነበር። ይህ ሰው የየሰዉን ልብስ ከየቤቱ እየሰበሰበ በአህዮቹ በመጫን ወደ ወንዝ ይወስድና ሲያጥብ ውሎ አመሻሽ ላይ በመመለስ ለየባለቤቱ ያጠበውን ልብስ ማስረከቡ የሚታወቅበት ሥራው ነበር።

ይሁንና አንድ ቀን ይኽ ሰው ይታመምና የተለመደ የአጠባ ሥራውን ማከናወን ይሳነዋል። በዚህ ጊዜ ወንድ ልጁን ጠርቶ በአህዮቹ ልብ ሱን ጭኖ ወደ ወንዝ በመውሰድ አጥቦ እንዲያመጣ ይነግረዋል።
ልጁም አባቱ እንዳዘዘው የሰበሰበውን ልብስ በአህዮቹ ላይ በመጫን ሊነዳቸው ቢሞክር አህዮቹ ከቆሙበት ቦታ አልንቀሳቀስ አሉ። አህዮቹ እግራቸው በገመድ ሳይታሰር ከቆሙበት አልንቀሳቀስ በማለታቸው ግራ የተጋባው ልጅ ወደ አባቱ በመሄድ፦

‹‹አባባ! አህዮቹን ለመንዳት ብሞክር ሊንቀሳቀሱልኝ ፈቃደኛ አልሆኑም›› ይለዋል።

በዚህ ጊዜ አባትየው ከተኛበት ቀና ብሎ፦ ‹‹ልጄ አንድ ምስጢር ሳልነግርህ ረስቼው ነው። አህዮቹን ማታ ወደ ማደሪያቸው ሳስገባቸው የሁሉንም እግር በእጆቼ እነካዋለሁ። አህዮቹም በገመድ ያሰርኳቸው ስለሚመስላቸው ከቦታቸው አይንቀሳቀሱም። በነጋታው መጥቼ የሁሉንም እግር በእጆቼ ስነካ ገመዱን የፈታሁላቸው ይመስላቸዋል።
በዚህ መንገድ ስላለማመድኳቸው ገመድ ሳልጠቀም በመሸና በነጋ ቁጥር ሳስርና ስፈታቸው ኖሬአለሁ። አሁንም ሂድና የሁሉንም እግሮች በእጆችህ ንካቸው። እንደፈታሀቸው አምነው መንቀሳቀስ ይጀምራሉ›› አለው።

ልጁም ወደ አህዮቹ ተመልሶ እንደታዘዘው ቢያደርግ አህዮቹ ከቆሙበት መንቀሳቀስ ጀመሩ።
~
‹‹እንግዲህ›› ይሉናል ሳራስዋቲ
‹‹የሰው ልጅ የሚገኝበት ሁኔታም ከዚህ ጋር በእጅጉ ተመሳሳይ ነው። ከፍጥረቱ ነ ፃ የሆነው ሰው በተለያዩ ህጎችና እምነቶች አዕምሮውን አስሮ ይሰቃያል። እነዚያ ሕጎችና እምነቶች ግን ቀድሞውኑ ለእሱው ነፃነትና ደስታ የተፈጠሩ መሆናቸውን አያውቅም፤ እናም በቅዠቱ በፈጠረው ገመድ ራሱን አስሮ የሚማቅቅ ፍጡር ሆኗል። ለዚህም ይመስላል እውነትና ቅድስና ለሰው ልጅ የሰማይ ያህል ርቀው ሲታዩ የኖሩት።›› በማለት ሳራስዋቲ የሕይወት ሥርዓት ራስን ለመግለጥና ለማወቅ ብሎም ወደ እውነታ ሁሉ ለመድረስ የተሻለው መንገድ መሆኑን የሚያስቀምጡት።
. . .
-----------------------------
"ጥ በ በ"
ከ ጲ ላ ጦ ስ
(ኃይለጊዮርጊስ ማሞ)

@zolaarts @zolaarts @zolaarts
48 views+Zelalem..*Arts , 18:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 14:32:50
41 views+Zelalem..*Arts , 11:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ