Get Mystery Box with random crypto!

ነፃነት ኦሾ/Osho # ነፃነትህን የሚያሳጣህ ጥገኝ የመሆን ፍላጎት ራስህን የመሆን ኃላፊነት ላለ | ህይወት ጥበብ ፍልስፍና

ነፃነት
ኦሾ/Osho

# ነፃነትህን የሚያሳጣህ ጥገኝ የመሆን ፍላጎት ራስህን የመሆን ኃላፊነት ላለመሸከም ያለህ ፍላጎት ነው።

ሙሉ በሙሉ ነፃ ለመሆን ሙሉ በሙሉ ግንዛቤ ማግኘት አለብን ምክንያቱም የባርነት ስር መሠረቱ ያለው ባለማወቃችን ውስጥ ነው። ከውጭ የሚመጣ ነገር አይደለም ማንም ነፃነትህን ሊያሳጣ አይችልም። ጥፋት ሊደርስብህ ይችላል። ግን አንተ አሳልፈህ ካልሰጠኸው በስተቀር ነፃነትህን ሊወስድብህ አይችልም።

ጠልቀን ስንመረምረው ነፃነትህን የሚያሳጣህ ነፃነትን ለማግኘት ያለመፈለግህ ነው። ነፃነትህን የሚያሳጣህ ጥገኝ የመሆን ፍላጎት ራስህን የመሆን ኃላፊነት ላለመሸከም ያለህ ፍላጎት ነው።

ሰው ለራሱ ኃላፊነት ለመውሰድ በፈቀደ ጊዜ በነገራችን ላይ ይህን ማድረግ ሙሉ በሙሉ አስደሳች ነገር አይደለም በውስጡ እሾህና መራር ነገሮች ይገኙበታል። ጣፋጫ ነገር ሁሉ ሚዛናዊ ነገር እኩል በእኩል ተከትለው ይመጣሉ። ጽጌሬዳዎች ያለ እሾህ አይበቅሉም ቀናትን ሌሊትን ተከትለው ክረምቱ አብቅቶም ፀሐይ ትወጣለች። ሕይወት የተቃራኒ ነገሮች ሚዛን አጣጥማ ትኖራለች።

ራስን የመሆን ኃላፊነትን ከውበቱና ከመራርነቱ ፣ከደስታውና ከስቃዩ ጋር ለመቀበል ፍቃደኛ የሆነ ሰው ነፃ መውጣት ይችላል። ነፃ ሊሆን የሚችለው ይህን መሠል ሰው ብቻ ነው።

@zolaarts