Get Mystery Box with random crypto!

#ለመጥፎ_ነገሮች_ራስህን_አዘጋጅ “ከእንቅልፍህ ስትነቃ እና አይንህን ስትገልጥ ለራስህ እንዲህ በ | ህይወት ጥበብ ፍልስፍና

#ለመጥፎ_ነገሮች_ራስህን_አዘጋጅ

“ከእንቅልፍህ ስትነቃ እና አይንህን ስትገልጥ ለራስህ እንዲህ በለው፡- መጨናነቅን፣ ምስጋና ቢስነትን፣ ውሸቶችን፣ ቅናት እና ቁጣን እፋለማቸዋለሁ። ሁሉም ሰዎች በእነዚህ ህመሞች ይሰቃያሉ፤ ምክንያቱም በመልካም እና በክፉ መሃል አለዩምና። የመልካምን ውበት ተመልክቻለሁ እና የመጥፎነትም ማስጠላት አውቃለሁ፤ መጥፎ አድራጊዎች ከእኔ አይርቁም፤ ሆኖም ምንም ጉዳት አያደርጉብኝም ወይም በእነሱ አስቀያሚነት ውስጥ ራሴን አልዘፍቅም - እነሱንም አልጠላቸው ወይም በእነሱ ላይ አልቆጣም።”
ማርከስ_አውሬሊየስ

ልክ እንደ ግድግዳ ሰዓት ሁሉ አንተም ፍጹም እና እርግጠኛ ልትሆን ትችላለህ፤ ሆኖም ዛሬ ላይ ከአስቸጋሪ ሰዎች ጋር መስማማት ትችላለህ? ጥያቄውም ተዘጋጅተህበታል? ነው፡፡ይህም ልምምድ በአስራ አምስተኛው ክፍለዘመን የነበረው ጸሐፊ ኒኮላስ ቻምፎርት ሃሳብ ጋር ይወስደናል፤

“ሁል ጊዜ በጥዋት እንቁራሪት ዋጥ” እናም ቀኑን ሙሉ ከዚህ የባሰ አስቀያሚ ነገር ሳይገጥምህ ያልፋል።

ምናልባትም ይህን ቃል እንዳለ ባትረዳው መልካም ይሆናል - ሰዎች ራስ ወዳድ እና ስለሌሎች ስሜት ግድ የሌላቸው ይሆናሉ፤ ያንተ እንቁራሪቶችም እነዚህ ሰዎች ናቸው - ቀኑን ሙሉ ስለነሱ ስትጨነቅ መዋልም የለብህም።

ማርከስም “እነሱንም አልጠላቸው ወይም በእነሱ ላይ አልቆጣም።” ይለናል - የዚህም ትርጓሜው ያጋጠሙህን ሰዎች ሁሉ ክፋታቸውን መጻፍ የለብህም ይሆናል። እናም ምናልባት ከቤትህ ስትወጣ የምትሸከምበትን ጫንቃ ካሰፋህ፣ ቀንህን በትዕግስት፣ በይቅርታ እና በመረዳት ውስጥ ታሳልፋለህ።

ምንጭ፦አፒክቲተስ

@zolaarts