Get Mystery Box with random crypto!

_ሁሉም ሰው የሚወድህ ስትሞት ብቻ ነው፡፡ በህይወት እያለህ የሚወድህም የሚጠላህም ብዙ ሰው ነው፡፡ | ህይወት ጥበብ ፍልስፍና

_ሁሉም ሰው የሚወድህ ስትሞት ብቻ ነው፡፡ በህይወት እያለህ የሚወድህም የሚጠላህም ብዙ ሰው ነው፡፡ ስትሞት ግን ያለልዩነት ሁሉም ሰው ይወድሃል፡፡ ለምንድን ነው? ለዚህ ብዙ የስነ -ልቦና ትንታኔዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ለእኔ ለጊዜው የገባኝ ግን ሁለት ነገር ነው።


1) ስትሞት ጠላት መሆን አትችልም። ማለት ከሞትክ የእነሱን ህይወት አትጋፋም ማለት ነው፡፡ ስትኖር ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ትፈጥራለህ፡፡ በዚህ የተነሳ የሚወድህም የሚጠላህም ይኖራል። ስትሞት ግን ምንም ተፅዕኖ መፍጠር አትችልም። ሰዎች ስትሞት ሁሉም ሰው የሚወዱህ ተፅዕኖ መፍጠር ስለማትችል ለማንም ሰው ጠላ። መሆን እንደማትችል ስለሚረዱ ነው።በዚህ የተነሳ ከሞትክ ያለ ልዩነት ሁሉም ሰብ ይወድሃል።ስለዚህ ስትሞት ሁሉም ሰው የሚወድህ እነሱን እንደማትጉዳቸው ስለሚያውቁ ይሆናል፡፡ የማትጎዳቸው ከሆነ ለምን ይጠሉሃል?

2) ስትሞት ሁሉም ሰው የሚወድህ አንተ ሬሳ ውስጥ ራሱን ሞቶ ስለሚያየው ነው ሁሉም ሰው ራሱን ይወዳል፡፡ ራሱን ስለሚወድ አንተ ስትሞት ስለራሱ ሞት ያስባል። የዚህ ጊዜ የሚወደው ራሱን አንተ ሬሳ ውስጥ ያየዋል። ስትሞት ሁሉም የሚወድነ የሚወደውን ራሱን አንተ ሞት ውስጥ ሞቶ ስለሚያየው ነው፡፡ ስለዚህ ስትሞት ሁሉ የሚወድህ ራሱን ስለሚወድ ነው፡፡
ሌላ ትንታኔ ይኖረው አይኖረው አላውቅም። ለኔም በጣም የገረመኝ ግን ይህ ነው፡፡ሁሉም ሰው ያለልዩነት የሚወድህ ስትሞት ብቻ ነው፡፡

ለምንድነው?

@zolaarts