Get Mystery Box with random crypto!

ለውጥ - በ‹ጊዜ» እና «ዘላለማዊነት መካከል የተሰነቀረ ተቃርኖ ? እነሆ ለለውጥ ያህል ራሱ | ህይወት ጥበብ ፍልስፍና

ለውጥ - በ‹ጊዜ» እና «ዘላለማዊነት
መካከል የተሰነቀረ ተቃርኖ ?


እነሆ ለለውጥ ያህል ራሱን «ለውጥ» /የማይለወጥስ ምን አለ? ከፈጣሪ በስተቀር ! እሱ እንደማይለወጥ እርግጠኛ ብንሆንም «ይለወጣል» የሚሉንን ተከራካሪዎች ሐሣብ ከማቅረብ ደግሞ ወደኋላ አንልም:: እንኳን በዘላለም ውስጥ ለሚኖረው ለ«እሱ» ይቅርና እኛ እንኳን በዚህች አጭር የዕድሜ ዘመናችን ስንቱን እንለውጣለን፤ እንለወጣለንም!

«ለውጥ» አቻ ትርጉም ሲፈልጉለት «እንቅስቃሴ፧ ከነበረው ውስጥ አዲስ ነገር መፍጠር፤ ወደመሆን መምጣት (ማምጣት) እንዲሁም ማለፍ ወይም መለየት» በማለት ያስቀምጡልናል:: «ለውጥ»ን እንግዲህ በዚህ መነጽር ስንመለከተው በቋሚና በሚንቀሳቀስ ነገር መካከል የሚገኝ ክስተት ይሆብናል:: በ«ጊዜ» እና «ዘላለማዊነት» መሀከል የተሰነቀረ ተቃርኖም ነው:: የሚለወጥ ነገር ሁሉ በ«ጊዜ» /time/ ሲገለፅ፤ የማይለወጠው ነገር ደግሞ (የማይለወጥ ነገር ካላ) እሱን ዘላለማዊ eternal/ እንለዋለን ። ወደ አሳብያኑ የ«ለውጥ» ምንነት ለመዝለቅ ደግሞ ቀጣይዋን ዕድሜ ጠገብ ትርጉም እናስቀድም፡- «ለውጥ» “ይሉናል ጥንታዊ አሳብያን፡- «የቀደመውና የኋለኛው መለኪያ ነች

አንደአሳብያኑ እምነት በጊዜ ውስጥ የሚኖር ማንኛውም ነገር “ይለወጥ ዘንድ የግድ ይሆናል:: ይኸ ማለት ግን የሚኖር ነገር ሁሉ ይለወጣል ማለት እንዳልሆነ ደግሞ ይነግሩንና በአንድ የዘመን ሂደት ሳይለወጥ «ፀንቶ» የቆየን ነገር እንደማይለወጥ ማሰብ ይቻላል ባይ ናቸው:: ዞሮ ዞሮ የለውጥ ወይም አለመለወጥ መለኪያው ጊዜ ከሆነ «ለውጥ» በራሱ ከጥንት እስከዛሬ የፍልስፍናው ዓለም በቂ ምላሽ ያጠረው አስቸጋሪ ጥያቄ ሆኖ እንዲዘልቅ አድርጐታል፡፡ የጥንት የግሪክ ፈላስፎች በ«ለውጥ» ጉዳይ እጅግ አጥብቀው የሚያስቡና የሚከራከሩ ነበሩ፡፡ እንዲያውም ለውጥን እንደአንድ የፍልስፍና ዘርፍ የሚያጠኑ ተማሪዎች በዚያ ዘመን የነበሩ ሲሆን መጠሪያቸውም «ፊዚስት» ይባል ነበር፡፡ የፊዚክስ የቀድሞ ትርጓሜም የእንቅስቃሴ በዓለም የምናያቸው ነገሮች እንቅስቃሴና ለውጥ) ጥናት እንደነበር እናውቅ ዘንድ እግረ መንገድ ይነግሩናል::

የ«ለውጥ» /Change/ ክርክር ከጥንቱ ዘመን ፍልስፍና በመነሳት ስንመለከት ሁለት ተፃራሪ ጐራዎችን የፈጠሩ ታላላቅ አሳብያንን ከግሪክ እናገኛለን፡- ሄራክሊተስ እና ፓርሜኒደስ፡፡ ሄራክሊተስ «ማንኛውም ነገር ይለወጣል» የሚል የአንድ ፅንፍ አስተሳሰብ ይዞ ሲያራምድ ፤ ፓርሜኒደስ ደግሞ «ማንኛውም ነገር አይለወጥም፤ ባለበት የፀና ነው» የሚል ሌላ ፅንፍ ይዞ ሲያራምድ ኖሯል:: ይኸ ክርክርና ልዩነት እስከዘመናችን ፈላስፎች ድረስ የቀጠለ ቢሆንም እንደእነዚህ ሁለት የጥንት የግሪክ ፈላስፎች አስተሳሰብ ግን አንድን ፅንፍ በወጉ ይዞ ሲያራምድ አልተገኘም::
ሄራክሊተስ የማይለወጥ ነገር የለም» የሚለውን አስተሳሰቡን ማረጋገጫ ሊያቀርብልን:- ማንም ሰው አንድ ወንዝ ላይ ሁለት ጊዜ ዘሎ መግባት አይችልም» በማለት ነበር፡፡ እንዴት? የሚል ጠያቂ ሲነሳበት:- «መጀመሪያ የገባበት ወንዝ ውሃ አልፎ ሄዷልና በድጋሚ ዘሎ ሲገባ የሚገባው አዲስ ውሃ ውስጥ ነው» ይለዋል፡፡

ይቀጥላል

ጥበብ ከ ጲላጦስ

@zolaarts