በዶ/ር ኤልያስ ገብሩ አርምሞ" ከመጽሐፉ የውስጥ ገጾች የተወሰዱ፦ - የእያንዳንዳችን የውስጥ ዓለም ሲያምር እንደ ህዝብ ውጫዊ ህይወታችንም ይዋባል። ውስጣቸው የተረበሹ ሰዎች ግን ህዝብና ሀገርን ይረብሻሉ። - ሰው በጥሞና ተቀምጦ አእምሮውን ሲያዋቅር፣ ነፍሱን ከሀልዮቱ ሲያስታርቅ ከራሱ አልፎ በዙሪያው ባሉ ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል። - ውስጣቸው የሰለጠነ፣ እግረ-ህሊናቸው የበረታ፣ በአርምሞ የመጠቁ ዜጎች ሲበዙ፣ ያኔ ሀገር ሰላምና አንድነቷ የእውነት ይፀናል። 27 views+Zelalem..*Arts , 20:10