Get Mystery Box with random crypto!

(ለ ግንቦት ፳ (20)) #በድጋሚ #በወረሀ_ግንቦት የማሩ ባተሌ | ነገረ - ጥበብ 📚📚

(ለ ግንቦት ፳ (20))
#በድጋሚ
#በወረሀ_ግንቦት

የማሩ ባተሌ
ከጫካ የወጣች
ምን ብትሆን ነዳፊ
ላ'መል የማትመች
ግብሯ እውነት አለው
አበባ መቅሰሙ
ውሉ ለዝንብ ነው
ግንቦት መሠየሙ
እናም በእኛ እድሜ
በምኖረው ትውልድ
በሀያዎች ዘመን
በመጣነው መንገድ
በወርሀ ዘጠኝ
በጠባ መስከረም
የዝንብ መንጋ እንጂ
ንቡን አለየንም!።


fanuel a.
@zikiretibeb
@zikiretibeb