Get Mystery Box with random crypto!

ዘኆኅተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት (official) ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ zhohitebirhan — ዘኆኅተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት (official) ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ zhohitebirhan — ዘኆኅተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት (official) ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @zhohitebirhan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 872
የሰርጥ መግለጫ

የቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ሰንበት ት/ቤት ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው ::
በዚህም ገጽ ላይ መንፈሳዊ ጹሁፎች ፣ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ መረጃዎች ፣ መልእክቶች እና ሌሎችም ይቀርቡበታል።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-12 18:45:25 ††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

†††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቁጽረታ (ጽንሰታ) ለማርያም †††

††† ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል::
ስለ ምን ነው ቢሉ:-
ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው:: አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ::
"ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ::"
"ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል (ያለ ጥፋት) ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው::"
(መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ. 1:9, መኃ. 4)

ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል::
የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ(አሮን) የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር::

ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም::

የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች::

ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ::

እርሷ ደግሞ:- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ::

በሰባተኛው ቀን (ማለትም ነሐሴ 7) መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ::

እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች::
"ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ"
"ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ::
(ቅዳሴ ማርያም)

††† "መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል::
የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . .
ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::" †††
(መዝ. ፹፮፥፩-፮)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
695 views15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 16:51:21
681 views13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 11:19:33
691 views08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 10:07:31
ኦርቶዶክሳዊያን በመጽሐፍ ምርቃው መርሐ ግብር እንዳይምታቱ፡፡

-“ኦርቶዶክሳዊ የክርስትና እምነትና መስፈርቶቹ” በሚል ርእስ መጽሐፍ አዘጋጀን የሚሉ አካላት የምርቃት መርሐ ግብር አዘጋጅተዋል፡፡

እዚህ መርሐ ግብር ላይ የመጽሐፉን ርእስ በየዋህነት በመመልከት ብቻ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረውን አስተምህሮ የያዘ መጽሐፍ መስሏችሁ በመርሐ ግብሩ ላይ ባይሳተፉ መልካም ነው፡፡ በፍጹም አይሳተፉ፡፡ መጽሐፉንም ሆነ መርሐ ግብሩን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጆች ያዘጋጁት ነው፡፡ መጽሐፉ የእኛ ወገን መስሏችሁ የዋህ ምዕመናን ገዝተው አያንብቡ አያስነብቡ፡፡ የመጽሐፉ አላማ ሲገልጹ “ቤተ ክርስቲያንን ከቅይጥ ትምህርተ ሃይማኖት እና ሥርዓተ አምልኮ ወደ ቀደመው የነቢያትና የሐዋርያት ትምህርት ለመመለስ ነው” በማለት ገልጸዋል፡፡

በመጽሐፍ ምርቃት መርሐ ግብሩም እንደለመዱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንደሚያንቋሽሹ መገመት ይቻላል፡፡ ስለዚህ በተለይ የዋህ ምዕመናን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ የአላማቸው ሰለባ እንዳይሆኑ አይሳተፉ፡፡ ምናልባት በመርሐ ግብሩ በመሥራ ቤት ሆነ በልዩ ልዩ ቦታ አግኝተዋችሁ በመጥሪያ ካርድ ሊሆን ይችላል የተጋበዛችሁ ኦርቶዶክሳዊያን ካላችሁ በይሉኝታ ተጠፍረው ለመሄድ አይወስኑ፡፡ ይሉኝታ የሚሠራበት ቦታ አለው፡፡ በእንደዚህ አይነት ምዕመናንን ሰለባ ለማድረግ በሚካሄድ መርሐ ግብር ለመሳተፍ ግን ይሉኝታ አያሰፈልግም፡፡ በትህትና ለመሄድ እንደማይፈልጉ ቢያሳውቁ መልካም ነው፡፡ በልዩ ልዩ ስልት ከሚመጡ አጭበርባሪዎች ራሳችንን እንጠብቅ፡፡ እናም ኦርቶዶክሳዊያን በመጽሐፍ ምርቃው መርሐ ግብር እንዳይምታቱ፡፡

መጽሐፉንም አይግዙ
1.1K views07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 12:40:21 ዘኆኅተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት (official) ቻናል pinned a photo
09:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 08:16:54
1.7K views05:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 14:39:22 ዘኆኅተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት (official) ቻናል pinned « ††† እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† ††† ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም ††† ††† ቸር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ ጽድቅ መድረስ…»
11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 14:39:17 ††† እንኳን ለቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† ቅድስት ጾመ ፍልሠታ ለማርያም †††

††† ቸር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጠው ጸጋ አንዱ ጾም ነው:: የሰው ልጅ ከፈጣሪው ክብር እንዲደረግለት ክፋትን መስራት የለበትም:: መልካም መሆንም ይጠበቅበታል:: ለዚህ ምንጮቹ ደግሞ ጾም: ጸሎትና ስግደት ናቸው:: ያለ እነዚህ ምግባራት መቼም ወደ ጽድቅ መድረስ አይቻልም::

ይቅርና እኛ ክፉዎቹ የሰማይና የምድር ፈጣሪ: የክብር ሁሉ ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደ ጊዜ ከጥምቀት በኋላ የመጀመሪያ ሥራው ያደረገው ጾምን ነው:: ስለዚህም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 7 አጽዋማትን በጉባዔ ሠርታ: በአዋጅ እንዲጾሙ ታደርጋለች:: ከእነዚህም አንዱ ጾመ ፍልሠታ ነው::

"ፈለሠ" - ሔደ: ተጓዘ እንደ ማለት ሲሆን " ፍልሠታ" ማለት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን የዕርገት ጉዞ የሚያዘክር ቃል ነው:: እመ ብርሃን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ኑራ ካረፈች በሁዋላ ሥጋዋ እንደ እኛ አልፈረሰም::

ለጊዜው በዕጸ ሕይወት ሥር ቆይታ እንደ ልጇ ትንሳኤ ተነስታ ዐርጋለች:: እርሷ በሁሉ ነገሯ ቀዳሚና መሪ ናትና:: ጾመ ፍልሠታን የጀመሩት አበው ሐዋርያት ሲሆኑ እንድትጾምም ሥርዓት የሠሩ ራሳቸው ናቸው:: ከ7ቱ አጽዋማትም እጅግ ተወዳጅና እየተናፈቀች የምትፈጸም ናት::

ካህናትና ምዕመናንም ጾሟን እንደየአቅማቸው ክብር በሚያሰጥ መንገድ ይፈጽሟታል::
*የቻሉ ወደ ገዳማት ሔደው ጥሬ እየቆረጠሙ: ውሃ እየተጐነጩ ክብርን ያገኛሉ::
*ሌሎቹ ደግሞ ባሉበት ደብር አካባቢ እያደሩ ሌሊት ሰዓታቱን: በነግህ ኪዳኑንና ውዳሴ ማርያም ትርጉዋሜውን: በሰርክ ደግሞ ቅዳሴውን ይሳተፋሉ::

እመቤታችን ሀገራችን ኢትዮጵያን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቅልን ዘንድ እንማጸናት። በእርሷ አምነን አፍረን አናውቅምና ነጋ መሸ ሳንል እንማጸናታለን::

††† #ጽንዕት_በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን ልበለብዎውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::

*ጾሙን የፍሬ: የትሩፋትና የበረከት ያድርግልን::*

††† "በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ:: ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ::" †††
(ኢዩ. 2:15)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

ምንጭ፡ መጽሐፈ ስንክሳር ፣ዓምደ ሃይማኖት
834 views11:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 20:56:16
689 views17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 11:14:00
675 views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ