Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክሳዊያን በመጽሐፍ ምርቃው መርሐ ግብር እንዳይምታቱ፡፡ -“ኦርቶዶክሳዊ የክርስትና እምነት | ዘኆኅተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት (official) ቻናል

ኦርቶዶክሳዊያን በመጽሐፍ ምርቃው መርሐ ግብር እንዳይምታቱ፡፡

-“ኦርቶዶክሳዊ የክርስትና እምነትና መስፈርቶቹ” በሚል ርእስ መጽሐፍ አዘጋጀን የሚሉ አካላት የምርቃት መርሐ ግብር አዘጋጅተዋል፡፡

እዚህ መርሐ ግብር ላይ የመጽሐፉን ርእስ በየዋህነት በመመልከት ብቻ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረውን አስተምህሮ የያዘ መጽሐፍ መስሏችሁ በመርሐ ግብሩ ላይ ባይሳተፉ መልካም ነው፡፡ በፍጹም አይሳተፉ፡፡ መጽሐፉንም ሆነ መርሐ ግብሩን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጆች ያዘጋጁት ነው፡፡ መጽሐፉ የእኛ ወገን መስሏችሁ የዋህ ምዕመናን ገዝተው አያንብቡ አያስነብቡ፡፡ የመጽሐፉ አላማ ሲገልጹ “ቤተ ክርስቲያንን ከቅይጥ ትምህርተ ሃይማኖት እና ሥርዓተ አምልኮ ወደ ቀደመው የነቢያትና የሐዋርያት ትምህርት ለመመለስ ነው” በማለት ገልጸዋል፡፡

በመጽሐፍ ምርቃት መርሐ ግብሩም እንደለመዱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እንደሚያንቋሽሹ መገመት ይቻላል፡፡ ስለዚህ በተለይ የዋህ ምዕመናን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ የአላማቸው ሰለባ እንዳይሆኑ አይሳተፉ፡፡ ምናልባት በመርሐ ግብሩ በመሥራ ቤት ሆነ በልዩ ልዩ ቦታ አግኝተዋችሁ በመጥሪያ ካርድ ሊሆን ይችላል የተጋበዛችሁ ኦርቶዶክሳዊያን ካላችሁ በይሉኝታ ተጠፍረው ለመሄድ አይወስኑ፡፡ ይሉኝታ የሚሠራበት ቦታ አለው፡፡ በእንደዚህ አይነት ምዕመናንን ሰለባ ለማድረግ በሚካሄድ መርሐ ግብር ለመሳተፍ ግን ይሉኝታ አያሰፈልግም፡፡ በትህትና ለመሄድ እንደማይፈልጉ ቢያሳውቁ መልካም ነው፡፡ በልዩ ልዩ ስልት ከሚመጡ አጭበርባሪዎች ራሳችንን እንጠብቅ፡፡ እናም ኦርቶዶክሳዊያን በመጽሐፍ ምርቃው መርሐ ግብር እንዳይምታቱ፡፡

መጽሐፉንም አይግዙ