Get Mystery Box with random crypto!

እንደ ሃገርስ ቢሆን ይሄን ቋሚ ገመና ተሸክመን የት ልንደርስ ነው? // አቶ የሱፍ ኢብራሒም// | ዘሪሁን ገሠሠ

እንደ ሃገርስ ቢሆን ይሄን ቋሚ ገመና ተሸክመን የት ልንደርስ ነው?

// አቶ የሱፍ ኢብራሒም//

ወለጋ ውስጥ በአማራዎች ላይ የሚፈፀመው የዘር ጭፍጨፋ ተጠናክሮ መቀጠሉን የሚያሳዩ መረጃዎች ደርሰውናል።

በዚህ መሰረት በዛሬው እለት በኪረሙ ወረዳ በህፃናት እና እናቶች ላይ ሳይቀር መጠነ-ሰፊ፣ የተቀናጀ እና ዘግናኝ ጭፍጨፋ እየተካሄደ ነው። አስክሬኖችን ማንሳትና መቅበር እንኳን እንዳልተቻለ ታውቋል።

ይሄ ለእኛ አሳዛኝ ብቻ አይደለም፤ አሳፋሪና አዋራጅም ነው! እንደ ሃገርስ ቢሆን ይሄን ቋሚ ገመና ተሸክመን የት ልንደርስ ነው? ከእንግዲህ ሌላውን ሁሉ ተውት—ከምር የህሌና እዳ ያለብን ወገኖች ትኩረት ሰጥተን መፍትሄ ብንፈልግለት ጥሩ ነው!