Get Mystery Box with random crypto!

ፕሬዝደንት ኡህሩ ኬኒያታ - በደቡብ አፍሪካ ሊደረግ ከነበረው የትህነግና የመንግሥት አደራዳሪነት ራ | ዘሪሁን ገሠሠ

ፕሬዝደንት ኡህሩ ኬኒያታ - በደቡብ አፍሪካ ሊደረግ ከነበረው የትህነግና የመንግሥት አደራዳሪነት ራሳቸውን ማግለላቸው ታውቋል፡፡ በሌላ ዜና ድርድሩም "በሎጂስቲክ አለመሟላት " በሚል ሰበብ መቅረቱ ተነግሯል!

ከዚህ በፊት በነበሩት የድርድር ሂደቶች ፥ ነፍሰበላዋ ትህነግ " ወደ ዝርዝር የድርድር ሂደት ከመግባታችን በፊት 'አሸባሪ' ብሎ የሰየመኝ ፓርላማ በይፋ ይቅርታ ጠይቆ ውሳኔውን ይሻር!" የምትለው ነገር " የብብቴን ፀጉር አበጥሩልኝ!" ከማለት አይተናነስም!

በነገራችን ላይ አሸባሪው ትህነግ ከነሀሴ 24/2014 ዓ.ም በኃላ በነበሩት ጊዜያት እንኳ በአሜሪካ አዛዥነት ሮቢላ ተልኮላቸው ፈልሰስ ብለው ጅቡቲ ላይ ተደራድረው ነበር! "ተኩስ አቁም ተስማምተናል!" እስከማለትም ደርሰው ነበር!

በርግጥ ጦርነት እየተካሄደ እንኳ "ድርድር" መደረጉ ያለ ፣ የነበረና የሚኖርም ነው፡፡ ነገርግን በየትኛውም አለም ከአሸባሪዎች ጋር ሀገረ-መንግስታዊና አለማቀፋዊ እውቅና የተሰጠው ድርድር ተደርጎ አያውቅም ፥ አይደረግም ፥ ሊደረግም አይገባም!

ሲቀጥል የዚች ሀገር የመከራና ስቃይ ጠንሳሹ ነፍሰበላ ከሀዲ ቡድን ፥ ከነአስተሳሰቡ ተቀብሮ ፥ አርማ ምልክቱን መጠቀም በህግ የሚያስጠይቅበት ዘመን እስካልመጣ ድረስ ፥ ኢትዮጵያ ረፍት አልባ ሆና ትቀጥላለች! በተለይም የአማራ ህዝብ " ከአጋም እንደተጠጋ ቁልቋል" ሆኖ መቀጠሉ ሳይታለም የተፈታ ነው! ስለዚህ አጋሙን ነቅሎና መንጥሮ መጣል ብቸኛው መፍትሔ ነው!

ድርድር አጋሙ እሾሆቹን ለማሳደግ የሚጠቀመው ጊዜ የመግዣ ስልት ብቻ ነው!

PP ግን ለህዝብ ቀርቶ ለራሱም የማይታመን ስለሆነ ምናልባት ከነቃ ፥ ህዝቡ ይንቃ!