Get Mystery Box with random crypto!

ፋኖ እስራኤልን ምን አድርግ ነው የምትሉት ? ' የመንግሥት ደህንነቶች ስራዬን ተረጋግቼ መስራት | ዘሪሁን ገሠሠ

ፋኖ እስራኤልን ምን አድርግ ነው የምትሉት ?

" የመንግሥት ደህንነቶች ስራዬን ተረጋግቼ መስራት እንዳልችል አርገውኛል!"

// ፋኖ እስራኤል እሸቴ - የቀድሞው የምስ/አማራ ፋኖ ም/አዛዥ //

ፋኖ እስራኤል እሸቴ አሸባሪውና ነፍሰበላው የትግራይ ወራሪ ሀይል በህዝባችን ላይ የጥፋት አዋጅ ካወጀበት ጊዜ አንስቶ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ ፥ " ቤቴን ፣ ልጆቼን ፣ ስራዬን ፣ ...!" ሳይል ፥ በተለያዩ ግንባሮች ተሰልፎ ከፍተኛ ዋጋ ሲከፍል የኖረ ፥ በተግባር መገለፅን እንጂ እንዲወራለት የማይሻ የአማራ ህዝብ የቁርጥ ቀን ልጅ ነው፡፡

እስራኤል በቅርቡ በግንባር ረዥም ጊዜ ከመቆየቱ ጋር ተያይዞ መደበኛ ስራውን መጀመር ካልቻለ ስራውን ሊያጣ በመሆኑና ቤተሰቡን ማስተዳደር ሀላፊነት ስላለበት ፥ ከምስራቅ አማራ ፋኖ በይፋ በመልቀቅ ወደመደበኛ ስራው ተመልሷል፡፡

ይሁን እንጂ የኛ ነገር "ወርቅ ላበደረ ጠጠር..!" ሆነና እስራኤል ካለፉት ወራት ጀምሮ ህይወቱን አደጋ ውስጥ እክከመጣል የደረሰ ማሳደድ ሲፈፀምበት ቆይቶ ፥ አሁን ደግሞ ስራውን ከጀመረ በኃላ ተረጋግቶ ህይወቱን እንዳይኖር የመንግሥት የደህንነት አካላት እስከ መስሪያ ቤት ድረስ በመሄድ የማሳደድና ረፍት የመንሳት ተግባር እየፈፀሙበት እንደሚገኙ ገልፇል፡፡

የመንግሥት የፀጥታ አካላት በጭንቅ ሰአት ወንድ ሆነው የተገኙትንና ለሀገርና ለህዝባቸው ታሪክ የማይሽረው ገድል የፈፀሙ ጀግኖችን ፥ ማመስገንና መደገፉ ቢቀር ተረጋግተው መደበኛ ህይወታቸውን እንዳይመሩ ማድረግ ፈፅሞ ለሞራል ተቃራኒ የሆነ አሳፋሪ ተግባር ነው!

የመንግሥት ሰዎች በፋኖ እስራኤል ላይ የሚፈፀመውን ወከባና ማሳደድ በአስቸኳይ እንድታቆሙ እየጠየኩ ፥ መላው ህዝባችንም ይህን መሠሉን ነውረኛ ተግባር በአንክሮ እንዲከታተለው ለማሳሰብ እወዳለሁ!