Get Mystery Box with random crypto!

'ለደፋር ሰው ቦታ የለኝም!' - አቶ የሱፍ ኢብራሒም ለወንድማማችነት ፥ ለፍቅር ፥ ለውይይትና ለ | ዘሪሁን ገሠሠ

"ለደፋር ሰው ቦታ የለኝም!" - አቶ የሱፍ ኢብራሒም

ለወንድማማችነት ፥ ለፍቅር ፥ ለውይይትና ለመተማመን ካልሆነ ለማደናገሪያና ለስም ጥሪ የሚገብር— ሃጂ ነስረላ የለም!

"ለደፋር ሰው ቦታ የለኝም!" ለማለት ነው። ደፋር ማለት ጀግና ለማለት አይደለም። ለማለት የፈለኩት ከወሎ፣ ከአማራና ከኢትዮጵያ አንዱን ምረጥ ወይም አንዱን ተው የሚሉኝን—ደፋሮች ፤ የሙስሊምና የክርስቲያን ፣ የቆላና የደጋ ፖለቲካ የሚያራግቡ—ደፋሮችን ፤ የአንዱን ጎጥ ህዝብ ነጥለው የሚያንቋሸሹ—ደፋሮችን ፤ በሌላ አካል እስትንፋስና የልብ ትርታ ላይ ተወስነው ውሳኔ ለመጫን የሚመኙ—ደፋሮችን ፤ በነጠላና መለመላ ሆነው "ህዝብ ነን" የሚሉ—ደፋሮችን እንዲሁም በሳንሱር ብርድ ልብስ ለማፈን የሚሹ—ደፋሮችን ነው!

ይኸው ነው!