Get Mystery Box with random crypto!

ኑ አዲስ ጎጆ እንስራ ማነው አዲስ ልብሱን አሮጌው ላይ የሚደርብ? አሮጌ እርሱነቱ እንዲሞት ካልፈ | ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

ኑ አዲስ ጎጆ እንስራ

ማነው አዲስ ልብሱን አሮጌው ላይ የሚደርብ? አሮጌ እርሱነቱ እንዲሞት ካልፈቀደ፣ ለአዲሱ እርሱነት መች ስፍራ አበጀ? የሰው ልጅ አሮጌው ማንነቱ ካልሞተ በቀር ትንሣኤ አያገኝም።

አዲስ ሕይወት፥ አሮጌውን ለቀበረ ሽልማት ናት። ንስር አሞራም ጥፍሩን እና ላባውን አራግፎ ጥሎ አዲስ ጥፍር እና ላባ ያበቅላል። ዳግም ንቁና ጠንካራ ኾኖም ይፈጠራል። የሰው ልጅም አሮጌ ማንነቱን አራግፎ ሲጥል ያኔ አዲስ ማንነትን ይላበሳል።

የበሰበሰ  ፍሬ፥ አፈር ለብሶ ከርሞ ሊበሉት የሚያጓጓ ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ኾኖ ይበቅላል። አሮጌውን ቤት እናፍርስ፤ አዲስ ቤትም እንስራ፤ መሰረቱን ከእምነት የማይናወጥ አለት፣ ግድግዳውን ሰላምን ከሚያላብሰው የይቅርታ ጡብ፣ ኹሉ እንዲኾን ከሚያደርገው የምሥጋና ቃል አዋቅረን፣ ኑ አዲስ ጎጆ እንሥራ።

እምነት በጸናበት በዚያ ተዓምር አለ። ይቅርታ ባለበት በዚያ ጥልቅ ሰላም አለ። ምሥጋናም ባለበት የተትረፈረፈ ጸጋ አለ። በዚኽ ጎጆ ላደረ፣ ይኽቺኛዋም ኾነች የወዲያኛዋ ዓለም ታምነው ይታዘዙታል።

ዮቶር- 2
አለማየሁ ደመቀ
@Zephilosophy