Get Mystery Box with random crypto!

Zena Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ zena_tube — Zena Tube Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zena_tube — Zena Tube
የሰርጥ አድራሻ: @zena_tube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.07K
የሰርጥ መግለጫ

ዜና Tube በኢትዮጵያ ወቅታዊ ፣ ጠቃሚና አንገብጋቢ መረጃወችን ከስር ከስር ለመከታተል የዜና Tube ቴሌግራም ቻናል ቤተሰብ ይሆኑ!
በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉ
👇👇👇👇
@ZenaTube_bot
@ZenaTube_bot

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-05 23:06:18
የነዳጅ ዋጋ

ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሬ መደረጉን የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

ቤንዚን በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም
ነጭ ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም
ኬሮሲን በሊትር 49 ብር ከ02 ሳንቲም
ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 53 ብር ከ10 ሳንቲም
ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር ከ37 ሳንቲም
የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 98 ብር ከ83 መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከላይ የተገለጸው የቤንዚን ፣ የኬሮሲን እና የነጭ ዋጋ ላይ ለህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ወይም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች 15 በመቶ በመንግስት እንዲደጎሙና ቀሪውን 10 በመቶ እንዲከፍሉ በማድረግ የድጎማ መጠኑን በቴሌ ብር ተመላሽ እንዲሆንላቸው ይደረጋል ተብሏል።

የተደረገው የዋጋ ማስተካከያ የተደረገባቸው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዝርዝር ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ሁሉ ተግባራዊ ይሆናል።

ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር
747 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:06:18
የነዳጅ ድጎማ !

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በአዲሱ የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ሥርአት ተጠቃሚ የማይሆኑ ተቋማትና ተሽከርካሪዎች በ4 ወራት ጊዜ ውስጥ ከመንግሥት የሚያገኙት የነዳጅ ድጎማ ሙሉ ለሙሉ ተነስቶ ዋጋውን ራሳቸው እንደሚሸፍኑ አስታውቋል።

ለ3 ወራት ግን መንግስት ከሚገዙት ነዳጅ ውስጥ ከ25 እስከ 75 በመቶ ዋጋ እንደሚደጉም ዛሬ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተነግሯል።

በሌላ በኩል ፤ ድጎማ የሚደረግላቸው የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ድጎማ ደግሞ በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ እንደሚነሳ ተገልጿል።

በዚህም መንግሥት በየስድስት ወሩ ተፈፃሚ በሚያደርገው ሥርዓት መሰረት 10 በመቶ ድጎማን እያነሳ የሚሄድ ሲሆን በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ በድጎማ የሚደገፋ የሕዝብ ትራንስፖርት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከድጎማ የሚወጡ ይሆናል ተብሏል።

መረጃው የኢትዮ ንግድ እና ኢንቨስትመንት መድረክ እና WMCC ነው።
623 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:06:18
#AASTU

የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች " ትምህርት ስለተጠናቀቀ ግቢውን ለቃችሁ ውጡ እንደተባሉና ችግር ላይ መሆናቸውን" ገልጸውልናል።

በተለይ ከትግራይ ክልል የመጡ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ለመመለስ ትራንስፖርት አለመኖሩ እንዲሁም ሌሎች ምክንያቶችን በማንሳት መቸገራቸውን ያስረዳሉ።

በጉዳዩ ዙሪያ የጠየቅናቸው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም ዐቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አለምእሸት ገብረወልድ ተከታዩን ምላሽ ሰጠውናል።

"መደበኛ ነባር ተማሪዎች እስካሁን በግቢው ነው የሚገኙት። ማንም የወጣ ተማሪ የለም።"

"የዩኒቨርሲቲው አመራሮች በጉዳዩ ዙሪያ እየመከሩ ነው። የትኞቹ ተማሪዎች ናቸው መቆየት ያለባቸው በሚለው ላይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ እየተወያዩ ነው።"

"ዩኒቨርሲቲው የጸጥታ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች የመጡ ተማሪዎች የትኞቹ ናቸው የሚለውን ማጣራት ካደረገ በኋላ ውሳኔው እንደሚያሳውቅ" ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።
511 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:06:17
#ዝርፊያ

የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች በተለያየ ጊዜ ዘረፋን ጨምሮ እስከ ግድያ የሚደረስ ወንጀል ይፈፀምባቸዋል።

ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ሰምተናል።

ከሰሞኑን አንድ በዚሁ በኤሌክቶኒክ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ሚሰራ ሰራተኛ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት አመክቷል።

ስሙ ሚኪያስ ተፈሪ የተባለው ወንድማችን ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚሰራባትን መኪና ይዞ ቆሞ ሥራ ሲጠባበቅ ነበር (ባለፈው ረቡዕ ምሽት)።

ከአገግልሎት ሰጪ ድርጅቱ ተደውሎ ከሳሪስ ጀሞ ሥራ እንዲሄድ ይጠየቃል ፤ የድርጅቱን ትእዛዝ ተቀብሎ ሦስት ሰዎችን አሳፍሮ ወደታዘዘበት ጀሞ ይሄዳል።

ደንበኞቹ ያሉበት ጀሞ ደረሱ። " ሂሳብ ስንት ቆጠረ?" ብለው ጠየቁ። ሂሳቡን ነገራቸው። እነርሱ ግን በያዙት ስለት አስፈራርተው መኪናውን ነጥቀው ተሰውሩ።

ሚኪያስ ቤተሰቡን የሚያስተዳድርበትን መኪና በዚህ መንገድ ተነጥቋል። ሚኪያስ ለፖሊስ ጣቢያ ድርጊቱን አሳውቋል። እስከዛሬ ሰኞ ድረስ አንዳችም ፍንጭ አልተሰማ።

መኪናው ከላይ በፎቶው የተያያዘ ሲሆን ታፋልጉት ዘንድ ጥሪ አቅርቧል ፤ (0922875988)

በሌላ በኩል ፤ በመሰል ስራ ላይ እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩ ወገኖች በተደጋጋሚ የሚሰሙት ዝርፊ እና ወንጀል ለስራቸው ስጋትን እየፈጠረ መሆኑን በመግለፅ የደህንነት ጉዳይ ይታሰብበት ፤ ወንጀለኞችንም ተከታትሎ አድኖ መያዝ ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል።
477 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:06:17
#SUDAN #ETHIOPIA

የኢትዮጵያ እና የሱዳን ጉዳይ !

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በመካከላቸው ያሉ ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸው ገለፁ።

ኬንያ ፤ ናይሮቢ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል-ቡርሃን ጋር ውይይት አድርገዋል።

ውይይቱን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ " ሁለቱ ሀገራት በሰላማዊ መንገድ ሊሠሩባቸው የሚችሉ በርካታ የትብብር መሠረቶች እንዳሏቸው አረጋግጠናል " ብለዋል።

" ያለን ትሥሥር ከየትኛውም መከፋፈል የሚበልጥ ነው " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " ሁለታችንም ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮችን #በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኝነታችንን ገልጸናል " ሲሉ አሳውቀዋል።
426 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:06:17
" ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አልተፈታም " - ቤተሰቦቹ

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤተሰቦች ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝን እንዲያከበር ጠየቁ።

ትናንት ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም 1ኛ የፀረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በ100 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ መወሰኑ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ቤተሰቦቹ ለዋስትና የተጠየቀውን ብር አስይዘው የመፈቻ ወረቀቱን ይዘው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (ሦስተኛ) ቢሄዱም ፍቺውን የሚያስፈፅም አካል ባለመኖሩ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገንን ሳይፈታው እንዳሳደረው ገልፀዋል።

በዛሬው ዕለትም ቤተሰቦቹ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን (ሦስተኛ) ቢገኙም እስካሁኑ ሰዓት ድረስ አራት የሚሆኑ መርማሪ ፖሊሶች፥ የመርማሪ ፖሊስ ሀላፊዎች እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነሩን ማግኘት እንዳልቻሉ ገልፀዋል።

በዚህም እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤቱ የወሰነው የፍቺ ጉዳይ መቋጫ አላገኘም ብለዋል።

የሚመለከታቸው አካላት ህግ እና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲከበር ጫና እንዲፈጥሩ ጠይቀዋል።

Via Tariku Desalgn
421 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:06:17
#SUDAN

ሲቪል አስተዳደሩን ገልብጠው ሙሉ በሙሉ ስልጣን ከተቆጣጠሩ ጊዜ አንስቶ በሱዳናውያን ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ እያስተናገዱ ያሉት ሌ/ጄነራል አብዳልፈታህ አልቡርሃን ጦሩ ቦታውን እንደሚለቅ ተናግረዋል።

ትላንት ሰኞ ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን በቴሌቫዥን ቀርበው የሱዳን ጦር ኃይል አገሪቱ ወደ ሲቪል አስተዳደር እንድትመለስ ለማድረግ ቦታውን ይለቃል ብለዋል።

የአገሪቱ ጦር ኃይል ሱዳን ወደ ዴሞክራሲ ለምታደርገው ሽግግር እንቅፋት እንደማይሆንና ምርጫ እንዲደረግ ወስኖ እየሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ጨምረውም በአገሪቱ ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማብቃት ከሲቪል ቡድኖች ጋር በሚደረገው ድርድር ላይ ጦር ሠራዊቱ የሚያደርገውን ተሳትፎ እንደሚያቋርጥ አሳውቀዋል።

ነገር ግን አገሪቱ ውስጥ ምርጫ ስለሚደረግበት እንዲሁም ጦር ኃይሉ ሥልጣን ስለሚያስረክብበት ሂደት የጊዜ ሰሌዳ ምንም አላሉም።

በሱዳን ውስጥ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሰረት የሚጠይቁት ተቃዋሚ ሰልፈኞች ሠራዊቱ ከፖለቲካው እንዲወጣ በመጠየቅ ለወራት የዘለቀ ተቃውሞ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል ሲል ቢቢሲ ፅፏል።
411 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:06:17
#Update

እጅግ በጣም በወሳኝ ሰዓት ይደረጋል ያተባለው የኢጋድ ስብሰባ ዛሬ ይካሄዳል።

በዚሁ ስብሰባ ላይ የአባል ሀገራት መሪዎች ናይሮቢ እየገቡ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

ናይሮቢ ከደረሱ መሪዎች መካከል የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የሱዳኑ ወታደራዊ አስተዳደር መሪ እና የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን ይጠቀሳሉ።

ከኢጋድ ስብሰባ ጎን ለጎን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሌ/ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሃን በወቅታዊ ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።

የዛሬው የኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እጅግ በጣም በወሳኝ ሰዓት የሚደረግ ስብሰባ ሲሆን የቀጣናው ጉዳይ ላይ በመሪዎች አማካኝነት ይመከርበታል።

መሪዎች ቀጠናውን በሚያሳስቡ ጉዳዮች ላይ ፣ ለሰላም እና ደህንነት እንቅፋት ስለሆኑ ጉዳዮች ፣ በድርቁ ሁኔታ ላይ በጥልቀት ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Photo Credit : IGAD & PMOEthiopia
405 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:06:17
#DireDawaUniversity

በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በጊዚያዊነት ተመድበው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ነባር ተማሪዎች " ግቢው ውጡ አለን " ሲሉ ቅሬታቸውን አድርሰውናል።

ተማሪዎቹ "ግቢውን ለቀን እንድንወጣ ተነግሮናል"፣ "የምግብ አገልግሎትም ተቋርጦብናል" ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀርባሉ።

በጉዳዩ ዙሪያ ያነጋገርናቸው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት መገርሳ ቃሲም (ዶ/ር) ተከታዩን ምላሽ ሰጠውናል።

"መደበኛ ነባር ተማሪዎች በግቢው መቆየት የሚችሉት እስከ ሰኔ 30/2014 ዓ.ም ብቻ ነው። ከሰኔ 30 በኋላ ዩኒቨርሲቲው የክረምት ተማሪዎችን ይቀበላል። በመሆኑም መደበኛ ነባር ተማሪዎችን የምናቆይበት አሰራር የለም።"

"በኮቪድ-19 ምክንያት የተደራረቡና የምንቀበላቸው 5 ሺህ የሚሆኑ የክረምት ተማሪዎች አሉብን። በቅርቡ የተቀበልናቸው የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ነው የሚገኙት። ከዚህ በተጨማሪ ከፍተኛ የበጀት እጥረት ገጥሞናል።"

በመሆኑም ሁሉም መደበኛ ነባር ተማሪዎች ግቢውን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።

ተቋሙ በአካዳሚክ ካላንደሩ መሰረት ነው የሚሰራው ያሉት ምክትል ፕሬዝዳንቱ፤ ተማሪዎቹ የዩኒቨርሲቲውን ውሳኔ ሊያከብሩ ይገባል ብለዋል።
394 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 23:06:16
#Update

ለቀናት ያህል የት እንደነበር ያልታወቀው ገጣሚ በላይ በቀለ ወያ ትላንት ምሽት ወደቤቱ መመለሱ ታውቋል።

ገጣሚ በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፁ ፤ " ከልዑል እግዚአብሔር ቀጥሎ ላዘናችሁልኝ ፣ ለራራችሁልኝ ፣ ለተጨነቃችሁልኝ ፣ ድምፅ ለሆናችሁኝ ሁሉ ከልቤ አመሠግናለሁ ። በህይወት ወደ ቤቴ ተመልሻለሁ ። ደህና ነኝ " ኢትዮጵያ ለዘልዓለም ትኑር " ሲል ፅፏል።

ገጣሚው በማን ፣ እንዴት እንደተወሰደ እንዲሁም የት እንዳነበረ በዝርዝር አልፃፈም።

ባለፉት 7 ቀናት ያለበት ባለመታወቁ እናት እና አባቱ አጠቃላ ቤተሰቦቹ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ወድቀው እንደነበር እና መንግስትም ሆነ ሌላ አካላ ልጃቸውን በሰላም እንዲመልስላቸው ጥሪ ሲያቀርቡ እንደነበር ይታወሳል።
393 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ