Get Mystery Box with random crypto!

#ደራሽ በሳምንት ለአምስት ቀናት የሚታየው ተከታታይ ድራማ ፦ በኢትዮጵያ ያለው የፊልም ኢንደስት | Zena Tube

#ደራሽ

በሳምንት ለአምስት ቀናት የሚታየው ተከታታይ ድራማ ፦

በኢትዮጵያ ያለው የፊልም ኢንደስትሪ በተቀዛቀዘበት በዚህ ወቅት በተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማዎች ኢንዱስትሪውን ለመነቃቃት ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል።

በዘርፉ ላይ ተግዳሮት ሆኖ የቆየውን የአቅም ችግር በመጠኑም ቢሆን በመቅረፍ ለሙያተኞች እንዲሁም ለተመልካቾች ትልቅ እድል ይዞ የመጣው አቦል ቲቪ ተጠቃሽ ነው፡፡

የሀገራችን የፊልም ኢንዱስትሪ ፈተና ውስጥ በገባበት በዚህ ወቅት አቅም ያላቸው ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀላቀላቸው ሰፊ የሥራ ዕድል ለሚፈጥረው ለዘርፉ ትልቅ ተስፋን የሚሰጥ ሆኗል።

አቦል ከኤምኔት ቻናሎች አንዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ80 በላይ #የኢትዮጵያ ፕሮዳክሽን ካምፓኒዎች በተለያየ መልኩ አብረው የመስራት ዕድል አግኝተዋል።

አቦል ቴሌቪዥን ለተመልካች ካቀረባቸው ውስጥ '' ደራሽ '' የተሰኘው ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ አንዱ ሲሆን ከ200 በላይ ባለሞያዎችን በማሳተፍ ከሰኞ እስከ አርብ በተከታታይ ይተላለፋል፡፡

ያንብቡ : https://telegra.ph/ደራሽ-08-03