Get Mystery Box with random crypto!

#VistOromia የቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ ሳምንት ከነሐሴ 4 እስከ ነሐሴ 7 በአዲስ አበባ ይካሄ | Zena Tube

#VistOromia

የቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ ሳምንት ከነሐሴ 4 እስከ ነሐሴ 7 በአዲስ አበባ ይካሄዳል።

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ያዘጋጀው "የቱሪዝም እና ቴክኖሎጂ ሳምንት" ከፊታችን ነሐሴ 4 ጀምሮ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

መድረኩ በተለይ ሁለቱን ትልልቅ ዘርፎች አካቶ በማቅረብ በሀገራችን የመጀመሪያው ሲሆን ከመንግስት እንዲሁም ከግል ተቋማት ያሉ የዘርፉ ዋነኛ ተሳታፊዎችን ያሳተፈ ነው።

4 ቀናት በሚቆየው በዚህ መርሐግብር የቱሪዝም ኤግዚቢሽን፤ የቱሪዝም ውይይት መድረክ፤ የቱሪዝም ሃካቶን 2014 (Hackathon 2022)፤ ቱሪዝም ቴክኖሎጂ እና ዲጂታል መፍትሄዎች የሚቀርቡበት ሲሆን በተጨማሪም ከቱሪዝም እና ከመንግስት ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ትስስር ለመፍጠር (Networking) ምቹ ሁኔታን የሚያመቻች መድረክ ነው።

በተለይ ፦

ቱሪዝም፥ ከቴክኖሎጂ ጋር ስላለው ጥልቅ ትስስር፤
ዘርፉ ስላለው ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅም፤
በማክሮ ኢኮኖሚ ማዕቀፍ ውስጥ ያለው ድርሻ
የትራንስፖርት፣ የመሰረተልማትና የኢንቨስትመንት ልማት ለዘርፉ ስለሚኖረው ሚና የፖናል ውይይት ይካሄዳል ተብሏል።

በተጨማሪ ቱሪዝም ፖሊሲ ላይ ጠቃሚ ግብዓቶች የሚገኙበት ይሆናል ተብሏል።

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ከነሐሴ አራት እስከ ነሐሴ 7 በስካይ ላይት ሆቴል በሚያከናውነው በዚህ ትልቅ ኤግዚቢሽን ላይ ፍላጎቱ ያላቸውና ከዘርፉ ተዋንያን ጋር መገናኘት ለሚፈልጉ በሙሉ በስፍራው ተገኝተው መሳተፍ እንደሚችሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መረጃ ገልጿል።