Get Mystery Box with random crypto!

ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal

የሰርጥ አድራሻ: @zena24now
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 34.80K
የሰርጥ መግለጫ

The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-21 15:33:02 የአቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አፅም በዓል በደብረ ሊባኖስ ገዳም በርካቶች በተገኙበት ተከበረ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ሊባኖስ ወረዳ ግንቦት 12 ቀን 2015 ዓ.ም በደብረ ሊባኖስ ገዳም የአቡነ ተክለሃይማኖት ፍልሰተ አፅም ዓመታዊ ክብር በዓል በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በድምቀት እንደተከበረ ተገልጿል ።

ለክብረ በዓሉ ከአዲስ አበባ ፣ቢሾፍቱ ፣ ከደብረብርሃን እና ከሌሎች አካባቢዎች የተውጣጡ በርካታ ምዕመናን በተገኙበት በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ጌታቸው በዙ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል ።

ይኸው ክብረ በዓል አቡነ ተክለሃይማኖት መጀመሪያ ከተቀበሩበት ዋሻ አፅማቸው ተነስቶ ግንቦት 12 ቀን በደብረ ሊባኖስ ገዳም ያረፈበትን ዕለት ለማሰብ የሚከበር ነው ። ደብረ ሊባኖስ ገዳም የካቲት 16 ቀን 1267 ዓ.ም በፃዲቁ አቡነ ተክለሃይማኖት የተመሰረ ሲሆን ገዳሙ ለዕይታ ማራኪ የሆነ አቀማመጥ ሲኖረው ዳግማዊ እየሩሳሌም በመባል ይታወቃል ።

በአበረ ስሜነህ
#ዳጉ_ጆርናል
2.7K viewsTrue, 12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 13:34:30
ክፍት የስራ ማስታወቂያ

Telegram join
https://t.me/Bruk_Sales_consultant

በሀገራችን  የሪል እስቴትገቢያ እና ሽያጭ  መሰረታዊ  የፍላጎቶችን ለማድረስ እና የሚታዩ  ችግሮችንም  በቀላሉ ለመቅረፍ የሚስችል ከመሆኑም በላይ ለራስዎም መልካም የስራ እድል በመፍጠር  በቂ ልምድ  እውቀት እና ክህሎት ካላቸው  የሪል እስቴት ገቢያ እና ሽያጭ አማካሪዎች  ጋር ለመስራት የሚስችልዎትን  እድል አመቻችተናል ።

ስራዎት ሳይበደል ጊዜ ሳይባክን ከ25ሺ  እሰከ 100ሺ ብር ማግኘት የሚስችለዎትን የኮሚሽን ስራ  አዘጋጅተናል ። አሰፈላጊ የሆነ የሪል እስቴት ስልጠናወችንም እንሰጣለን ። ከዚህ በፌት የሪል እስቴት የስራ ልምድ ያላችሁም ከሆነ በደስታ እንቀበላለን ።
ይግዙ ይሽጡ ያማክሩ ያለዎትን ሪሶርስ በቀላሉ ይጠቀሙበት ።
መረጃ እውቀትም ገንዘብም  ነው ።
ጊዜ ወርቅ ነው ።

ይደውሉ

ብሩክ ሠጠኝ
የገበያና ሽያጭ ባለሙያ/አማካሪ

+251912898237


Telegram join
https://t.me/Bruk_Sales_consultant
2.9K viewsTrue, 10:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 12:03:35
አትሌት ፀሀይ ገመቹ አሸነፈች

በህንድ ቤንጋሉር በተካሄደው የ10 ኪ.ሜ ውድድር አትሌት ፀሀይ ገመቹ ስታሸንፍ ሌላኛዋ ኢትዮጲያዊት ፎይለን ተስፋዬ እንዲሁም አትሌት ደራ ዲዳ የሁለተኛና የሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

በወንዶች የኬንያዊያን አትሌቶች የበላይነት የተመዘገበ ሲሆን ንብረት መላክ ፣ ሚልኬሳ መንገሻ ፣ሰለሞን በሪሁና ገመቹ ዲዳ ከአምስት እስከ ስምንተኛ ደረጃ ተከታትለው ገብተዋል።

#ዳጉ_ጆርናል
2.8K viewsTrue, edited  09:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-21 11:58:39
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ጉዳትና ኪሳራ ማድረሱን መንግሥት ይፋ አደረገ!

በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለይም ማዕከሉን በትግራይ ክልል አድርጎ ለሁለት ዓመታት በተካሄደውና በሌሎች የተወሰኑ አካባቢዎች በነበረው ጦርነት፣ ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳትና ኪሳራ በአገር ላይ መድረሱን ገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. የገንዘብ ሚኒስቴርን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረቡት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ ተቋማቸው በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተካሄደው ጦርነት የደረሰውን ጉዳትና የመልሶ ግንባታ ፍላጎት የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት (Damage and Needs Assessment) በማከናወን፣ የጥናት ውጤቱን ለመንግሥት እንዳቀረበ ተናግረዋል።

በጥናት ግኝቱ መሠረትም ያጋጠመው አጠቃላይ ጉዳትና የኢኮኖሚ ኪሳራ በአጠቃላይ 28 ቢሊዮን ዶላር እንደሚሆን ሪፖርታቸው አመላክቷል። ይህም በወቅቱ የውጭ ምንዛሪ ተመን ከ1.5 ትሪሊዮን ብር በላይ ነው።

ለቋሚ ኮሚቴው ያቀረቡት ሪፖርት ላይ ከተቀመጠው መረጃ መረዳት እንደተቻለው፣ ‹‹22 ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 20.4 በመቶ የሚገመት ጉዳት›› ደርሷል። በዚሁ ምክንያት የደረሰው የኢኮኖሚ ኪሳራ ደግሞ፣ ‹‹ስድስት ቢሊዮን ዶላር ወይም ከጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 5.5 በመቶ የሚገመት የኢኮኖሚ ኪሳራ (Economic Loss)›› መድረሱን ሪፖርቱ ያመለክታል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://www.ethiopianreporter.com/118763/

Via YeneTube
#ዳጉ_ጆርናል
2.9K viewsTrue, edited  08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 23:02:25
3.4K viewsTrue, 20:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:43:23
ማንቸስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ

የአርሴናልን በኖቲንግሃም ፎረስት መሸነፍ ተከትሎ ማንቸስተር ሲቲ ባለፉት ስድስት አመታት ለአምስተኛ ጊዜ የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መሆን ችሏል። በክለቡ ታሪክ የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ቁጥር 9ኛው ነው።

#ዳጉ_ጆርናል
3.6K viewsTrue, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 21:27:32
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፀጥታ ኀይሎች ተወሰደ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ አመሻሹን በፀጥታ ኀይሎች ከመኖሪያ ቤቱ መወሰዱን ቤተሰቦቹ ለዋዜማ ተናግረዋል። ተመስገን ለምን እንደታሰረና ወዴት እንደተወሰደ ገና አለወቅንም ያሉት ቤተሰቦቹ የመንግስት ፀጥታ ሰራተኞች ምሽት አንድ ሰዓት ተኩል ገደማ ወደ መኖሪያ ቤቱ ዘልቀው እንደወሰዱት ከዓይን እማኞች ሰምተናል ብለዋል።

Via ዋዜማ ራዲዮ
#ዳጉ_ጆርናል
3.6K viewsBeⓒk, edited  18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 15:51:15 የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ995 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

       ባለዕድል ለሆኑ ደንበኞቹ 311. 5 ሚሊየን ብር ከፍሏል


የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በ2015 በጀት ዓመት 13 የሎተሪ አይነቶችን ለሽያጭ እና ለዕድል ጨዋታ አቅርቦ 995 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር ጠቅላላ ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡ይህም የእቅዱን 88 በመቶ ያሳካበት ሲሆን ከዚሁ ጎን ለጎን አስተዳደሩ ለሽያጭ እና ለእድል ጨዋታ ካቀረባቸው ሎተሪዎቹ 363.9  ሚሊየን ብር በላይ  የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን በብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ  አስተዳደሩ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው በፀጥታ ምክንያት ከተዘጉ ቅርንጫፎች እንዲሁም ከፈጣን እና ከቢንጎ ሎተሪዎች ሲሆን የውጪ ምንዛሬ እጥረት ኖሮ የሚፈለገው ያህል ለገበያ ማቅረብ እንዳልቻለ ግን አስታውቋል።በተጨማሪም በተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ህገ ወጥ የሎተሪ ጨዋታዎች የሚያካሄዱ ግለሰቦች የአስተዳደሩ ፈተናዎች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

አስተዳደሩ በዓመቱ ከማስተዛዘኛ እስከ 20 ሚሊየን ብር ባለዕድል ለሆኑ ደንበኞች 311 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ጠቅላላ ክፍያ መፈፀሙን አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ጨምረዉ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል
3.9K viewsTrue, 12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 14:26:29
ሰላም
በትርፍ ሰአት  ቢዝነስ ላይ በመስራት ተጨማሪ ገቢ ማግኘት የምትፈልጉ ሰዎች ብቻ በተለይም አዲስ አበባ ለምትኖሩ ልዩ እድል አለን
በውስጥ መስመር በማውራት ወይም በመደወል የእድሉ ተጠቃመሚ መሆን ይችላሉ
በ0 ኢንቨስትመንት 100%ገቢ የሚገኝበት

ብሩክ ሠጠኝ
የገበያና ሽያጭ ባለሙያ

+251912898237
@Bruk23

Telegram join

@Bruk_Sales_consultant
@Bruk_Sales_consultant
3.8K viewsTrue, 11:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 12:34:38 Updated አጫጭር መረጃዎች

የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 15 መምህራን ህይወታቸውን ያጡበት አደጋ በተመለከተ

የመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኝበት ሮቤ ከተማ ወደ ዶዶላና አዳባ ካምፓሶች ለማስተማር ሲጓዙ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 15 ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መምህራን ህይወታቸውን አጥተዋል።

50 ሰው ባሳፈረ አውቶቡስ ሲጓዙ የነበረ ሲሆን ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በተጨማሪ 20 ሰዎች ክፉኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሮቤና ሻሸመኔ ሆስፒታል ተልከዋል።

መምህራኑ የርቀት ተማሪዎች የሆኑ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፣ የስፖርት ፣የጤናና የግብርና ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎች ለማስተማር እያቀኑ እንደነበር በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችና የመምህራን ጉዳዮች ዲን ዶ/ር ለት በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርከሪው በተለምዶ ሰብስቤ ዋሻ ውስጥ ተገልብጧል።ይህው አካባቢ በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የሚደርስበት ነው።

ተሽከርካሪው ያልተነሳ ሲሆን ክሬን በመፈለግ ቀሪ አስክሬን ለማውጣት እየተሞከረ መሆኑን በስፍራው የሚገኙት ዶ/ር ለታ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።


በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል
3.7K viewsTrue, 09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ