Get Mystery Box with random crypto!

'…መልአከ ሰላም ቀሲስ ምስጢሩ ታፈረ በውድብሪጅ ደብረ መድኃኒት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ) ነጭ ነጯን

"…መልአከ ሰላም ቀሲስ ምስጢሩ ታፈረ
በውድብሪጅ ደብረ መድኃኒት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና መጋቤ ጥበብ ቀሲስ መምህር ሳሙኤል ግዛው በውድብሪጅ ደብረ መድኃኒት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን የቃና ዘገሊላን በዓል በታላቅ ደስታ፣ በሚደንቅ አገልግሎት አሳልፈን ውለናል። በእውነት ዛሬ ለእኔ ልዩ ቀኔ ነበር።

"…የደብሩን ካህናት፣ የደብሩን ሰበካ ጉባኤ አባላት፣ እና ምእመናንንም እጅግ አድርጌ ከልብ አመሰግናለሁ። ላሳያችሁኝ ፍቅር፣ ክብር ሁሉ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው። በእውነት ደስ ነው ያለኝ።

"…በዚህኛው የአሜሪካ ጉዞዬ ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደማታፍርብኝ፣ ልጄ ነው ብላ ከተደበቅኩበት አውጥታ አደባባይ አቁማ እንደምትባርከኝም አይቼበታለሁ። በአሜሪካ ያየሁት የሰው የሕዝብ ፍቅር የሚገርም ነው። ወደፊት ከዚህ የበለጠ ፍልሚያ ውስጥ በበረታ ጉልበት እንድገባ የሚያደርግ መንፈሳዊ ኃይልም ያገኘሁበት ጉዞ ነው።

• የነገ ሰው ይበለን…!