Get Mystery Box with random crypto!

'…የአዲስ አበባ ፖሊስን የደንብ ልብስ የለበሱ የኦሮሙማው ፖሊስ አባላት በሽሮ ሜዳ በሚገኙ የባህል | Zemedkun Bekele (ዘመዴ) ነጭ ነጯን

"…የአዲስ አበባ ፖሊስን የደንብ ልብስ የለበሱ የኦሮሙማው ፖሊስ አባላት በሽሮ ሜዳ በሚገኙ የባህል ልብስ መሸጫ ቤቶች ይሄዳሉ። ከዚያም ቤቱን ይዘጉታል። መጀመሪያ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም ያለበትን የሀገር ልብስ በሙሉ ይሰበስባሉ፣ በፌታል፣ በሻንጣም ይከታሉ። ቀጥሎም ለእናታቸው፣ ለሚስታቸው፣ ለልጃቸው፣ ለገርል ፍሬንዶቻቸው የሚሆን ሰንደቅ ዓላማ የሌለበትን የሀበሻ ቀሚስ በሙሉ ሰብስበው ይወስዳሉ። ለሌሎች የኦሮሞ ባህል አልባሳት ሻጮችም በመጠነኛ ብር ያስረክባሉ። ከሁሉም ያሳቀኝ የኦሮሞ ፖሊሶቹ ለአዲስ አበባ ሴተኛ አዳሪዎች በገንዘብ ምትክ የዘረፉትን እንደ ክፍያ የመጠቀማቸው ነገር ነው። አንድ የኦሮሞ ፖሊስ በዘረፈው 1 የሀበሻ ቀሚስ ከ4 እስከ 6 ጊዜ ያህል በነፃ የዝሙት አገልግሎት ያገኛልም ተብሏል። አቤት ውርደት።

"…ተቀጥቅጠው ለአቢይ የተገረዱት የአልባኒያ ኮሚንስቶቹን ደብረ ጽዮንና ጌታቸው ረዳ በወርሀ ህዳር በአክሱም ጽዮን፣ ዛሬ ጥር 7 ደግሞ በሽሬ እንዳ ሥላሴ ከጸሎተ ኪዳን፣ እስከ ቅዳሴ ተሳትፈው፣ ታቦተ ሕጉንም አንግሠው አክብረው፣ ጌቾ ትንሽ ሰብኮ፣ ደብረ ጺዮን ደጀ ሰላም ገብቶ ሲለጋ ውሎ፣ መመለሱም ተሰምቷል። ደፂና ጌቾ በመቀጠል መጪውን የጥምቀትን በዓል ከከተራ እስከ ቃና ዘገሊላ፣ አስተርዕዮ ማርያምን፣ የካቲት ኪዳነ ምህረትንም ጭምር እንዲሁ ሰዓታት ሁላ እየቆሙ አስቀዳሽ እንደሚወጣቸውም ተሰምቷል። አይ ጊዜ። የጨነቀ’ለት አለ አዝማሪው።

"…በመጨረሻም ኦሮሙማው OMN የታከለ ኡማ የሁለት ልጆቹ እናት ጎንደሬዋ የቀደሞ ሆስተስ ለጥምቀት በአዲስ አበባ ያዘጋጀችውን ዝግጅት አሰርዞ ለአገው ሸንጎ ግን በአዲስ አበባ እንደሚያከብሩላቸው ተስፋ ሰጥተዋቸዋል። አይ ኦሮሞ አሁን በእነሱ ቤት ዐማራና አገውን አለያይተው ትልቅ ቦለጢቃ ሠርተው ልባቸው መውለቁ ነው።

• ፋኖ ግን እየመጣ ነው…!