Get Mystery Box with random crypto!

'ርዕሰ አንቀጽ' '…ጅቡ በሬዎቹን ለመብላት ወስኗል። የማይቀረው ፍልሚያም ተጀምሯል። በሬዎቹ ከ | ዘመድኩን በቀለ(ZemedkunBekele) (አድናቂዎች)

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ጅቡ በሬዎቹን ለመብላት ወስኗል። የማይቀረው ፍልሚያም ተጀምሯል። በሬዎቹ ከተነጣጠሉ ተራ በተራ ይበላሉ። አንድ ከሆኑ፣ በኃሳብ፣ በተግባር፣ በሥራ ከተናበቡ፣ አንዱ ሲነካ ሌላኛው አለሁ ካለ ጅቡን በቀንዳቸው ወግተው፣ በእግራቸው ረግጠው ያሸንፉታል። አልያ ግን ተራ በተራ ይበላቸዋል። አራቱ በሬዎች ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋ፣ ወሎ።

"…ከእለታት በአንድ ቀን መልካቸው ቀይ፣ ነጭ፣ ጥቁር እና ግንባሩ ቦቃ የሆኑ አራት በሬዎች ጫካ ውስጥ ተስማምተው ይኖሩ ነበር አሉ። አንበሳን ጨምሮ የትኛውም የጫካ አውሬ ቢመጣ ክብ በመሥራት በአራቱም ማዕዘን ፊታቸውን ወደ አደጋ ጣዩ አዙረው አደጋ አድራሹን በላተኛ ጠላት ይከላከሉታል። እየተዋጉትም አላስጠጋ ይላሉ። የሚደፍራቸውም ጠፋ።

"…ጅብ ግን ተስፋ ሳይቆርጥ በየእለቱ ይሞክር ነበር። ግን አልቻለም። አንድ ቀን ግን አያ ጅቦ ሃሳብ መጣለት። እነዚህን አራት በሬዎች መብላት ያልቻልኩት እኮ በሬዎቹ አንድነት፣ ኅብረት፣ ቅንጅት ስለፈጠሩ ነው። እናም በተናጥል አጣልቼ ለምን ተራ በተራ አልበላቸውም ብሎ መጣና እንዲህ አላቸው። ስሙኝማ እናንተው። ለምን ሁልጊዜ ማታ ማታ እንደምመጣ ግን ታውቃላችሁ? ይላቸዋል። አናውቅም እንጃ ይሉታል። ስሙ እናንተ ኃይለኞች ናችሁ። አንበሳ እንኳን ያልደፈራችሁ። ነገር ግን እናንተ ሰላም እንዳታገኙ፣ እኛንም ወደ እናንተ የሚጠራን ይሔ ነጭ በሬ ነው። እሱ ባይኖር ኖሮ እናንተ በጨለማ አትታዩም ነበር። እናም እሱ ያስጨርሳችኋል” የሚል መጥፎ ሃሳብ በውስጣቸው ለቀቀባቸው። ሦስቱ በሬዎችም እውነት ለአንዱ ብለን ለምን ዘወትር ከጠላት ጋር ስንዋጋ እንኖራለን ብለው በማሰብ ሦስቱ በሬዎች የጠላትን ምክር ሰምተው ተባብረው ነጩን በሬ አባረሩት፡፡ ጅቡም ነጩን በሬ ብቻውን አግኝቶ ቅርጥፍ አድርጎ በላው።

"…ጅቡ ሌላ ጊዜ ተመለሰና ለበሬዎቹ “ግንባረ ቦቃው ካለ አሁንም ለአደጋ የተጋለጣችሁ ናችሁ፣ እያለ፣ በሌላቀንም ቀዩ በሬ እያለ አለያይቶ ተራ በተራ በላቸው። መጨረሻ ላይ ለቀረው ጥቁሩ በሬ ከሌሎቹ ከመለየቱ እና ብቻውን ከማስቀረቱ በፊት "አንተ እኮ ሦስቱም ባይኖሩ መልክህ ጥቁር ስለሆነ ብቻ ማንም አያይህም፣ በሰላምም መኖር ትችላለህ ብሎ ሰብኮትም ነበር። ጥቁሩ ብቻውን ቀረ። አያ ጅቦም መጣለት። በሬውም “ደግሞ ዛሬ ምን ፈልገህ መጣህ? ልትበላኝ ባልሆነ ብሎም ጠየቀው?”። ጅቡም መለሰለት አለውም “አንተ እኮ የተበላኸው የመጀመሪያውን ጓደኛህን አሳልፈህ የሰጠህው ጌዜ ነው” በማለት ቀረጣጥፎ ቀንድና ጭራውን ሳያስቀር በላው።

"…ሸዋ ብቻ እየተዋጋ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ፣ ጎጃም ዝም ካልክ በሸዋ ብቻ አይቀሩልህም። ሸዋ ሲነካ ሦስቱም በሰላማዊ ሕዝባዊ ተቃውሞ አገዛዙን ማስጨነቅ አለባቸው። እኔ አማች ነኝ ብትል፣ እኔ ባለሃብት ነኝ ብትል፣ እኔ እንዲያ እንዲህ ነኝ ብትል ጅቡ እንደው ሊበላህ ቆርጦ ተነሥቷል። የጅቡን ነጣጥሎ መብላት የምታስቆመው በአንድነት በመቆም ነው። አዲስ አበባም ሰምተሃል።

"…ካነበባችሁት በኋላ በርዕሰ አንቀጹ ላይ ሃሳባችሁን ትሰጡ ዘንድ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ።

"…አሸበርቲው ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ…!