Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ለፔጄ ተከታታይ ጓደኞቼ በሙሉ…! '…ይሄ እንደከባድ ሱሰኛ በቀን 10 ጊዜ ዘው እያላችሁ | ዘመድኩን በቀለ(ZemedkunBekele) (አድናቂዎች)

ይድረስ
ለፔጄ ተከታታይ ጓደኞቼ በሙሉ…!

"…ይሄ እንደከባድ ሱሰኛ በቀን 10 ጊዜ ዘው እያላችሁ በምትጎበኙት የቴሌግራም ፔጄ ላይ የምለጥፍላችሁ መረጃ እንዲሁ እንደዋዛ በቀላሉ የሚመጣ አይምሰላችሁ። ያለምን ክፍያ በብላሽ ስለምታገኙት አትናቁት። በስንት ድካምና ልፋት፣ በስንት ውጣውረድ መረጃዎቹ ተቆፍረው፣ ተቆፍረው ተገኝተው ወደ እናንተ እንደሚደርሱ እኔና ፈጣሪዬ ነን የምናውቀው። እናም እንደቀላል አትቁጠሩት።

"…እኔ የምጽፈውን መረጃ ተደብቆ አንብቦ ዞር ማለት ነውር ነው። መረጃውን አንብቦ ሼር ማድረግ በተለይ በአሁን ጊዜ ዐማራውን ይጠቅማል። ሼር አድርጉት። ልቅሶ፣ የቡና ላይ ወሬ፣ ተራ አሉባልታ፣ መንጫጫትም የሌለበት ቀሽም፣ ልምጥምጥ፣ ኧረ ወየው ወየውም ያልሆነ ጀግና ጀግና የሚሸት አለአይደለ በቅመም የታሸ ወኔያም የሆነ ኮመንት መስጠትም መሬት ላይ ላለው ዐማራ ይጠቅመዋል። ከእንግዲህ እንዲያውም ከጻፍኩት ኮመንት ስር የመንደር ወሬ ኮመንት የሚሰጠውን እቀስፈዋለሁ።

"…የአረመኔውን የአብይ አገዛዝ ሙሉ ካድሬው ፔጄን ነው እንደሚኮመኩሙ መረጃው አለኝ። ቢያነቡም ግን የማወጣው መረጃ፣ የምጦምረው ጦማር ሴራውን ስለሚያፈራርሰው ላይክም፣ ሼርም አያደርግም። ኮመንትም አይሰጥም። ኮመንት የሚሰጡ ቢመጡ እንኳ ባለጌ፣ አጀንዳ አስቀያሽ፣ ፈሪና ልክስክስ ተሳዳቢ ሆነው ነው የሚመጡት። እኔ ታዲያ ምኔ ሞኝ ነው ሰከንድም አላቆያቸው ስቀስፋቸው። ፔጄ እንዲህ የጨዋዎች መገኛ የሆነው እኮ ቀሳፊ ስለሆንኩ ነው።

"…አገዛዙ የላይክ ብዛት ያስፈራዋል። የኮመንቱ ብዛትም ያስቀዝነዋል። ዋናው ፕሮፓጋንዳው ነው። እሱን ማፈራረስ የሚቻለው ተደብቆ በመንበብ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም እንዲደርስ ላይክም፣ ሼርም፣ ኮመንትም ማድረግ ነው። ሰምተሃል ምደረ አፈጣዲቅ ሽንታም ቦቅቧቃ ሁላ።

"…ዐማራዬ ግን ወጥር፣ መክት፣ አንክት…!