Get Mystery Box with random crypto!

የእርዳታ ጫማ መሆኑ ነው…!! '…አዲሱ በሃጂ ኢብራሂም ቱፋ የሚመራው የእነ አህመዲን ጀመበልና የ | ዘመድኩን በቀለ(ZemedkunBekele) (አድናቂዎች)

የእርዳታ ጫማ መሆኑ ነው…!!

"…አዲሱ በሃጂ ኢብራሂም ቱፋ የሚመራው የእነ አህመዲን ጀመበልና የእነ ሙጂብ አሚኖ የኦሮሚያ ሙጅሊስ ከወለጋ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ መጠለያ ካም ተጠልለው ለሚገኙ የዐማራ እስላሞች በትኖላቸው የሄደው የእርዳታ ጫማ ነው ተብሏል።

"…በእርዳታው ኃይለኛ ዜና ተሥርቶበታል። እርዳታው ሲጫን፣ ሃጂ ቱፋ እና መጅሊሳቸው ሲሸኙ፣ የሃሩን ሚዲያ ካሜራማኖች እየተከረባበቱ ሲዘግቡ፣ ኦኤምኤን ሲያጮኸው፣ አብዱርሃማን ለሃጩን፣ ይቅርታ ምራቁን እያንጠባጠበ ሲዘግበው አይተናል።

"…ስደተኞቹም ተሰብስበው ቪድዮ ተቀርጸው ተበትነዋል። ለሌላ ሽቀላ ማለት ነው። መኪናውን ከበው ቪድዮም ተነሥተዋል። እንዲያመሰግኑም ተደርገዋል። ካሜራው ከሄደ፣ ጋዜጠኞቹም ከተመለሱ በኋላ ለዐማራ እስላም ስደተኞች ከኦሮሚያው የሃጂ ቱፋ መጅሊስ የተላከው ጫማ እንዲህ አይነት ሆኖ ተገኝቷል። ይሄ ማለት ከወለጋ ተፈናቅለው በደቡብ ወሎ ሃርቡ ከተማ መጠላያ ውስጥ ላሉት የዐማራ እስላሞች ከአዲሱ መጅሊስ የተላከው የልብስ እና የጫማ ርዳታ ነው የተባለው ነው።

•…እኔ ዘመዴ ፈጣሪ ይቅር ይበለኝና ስጠረጥር ስጠረጥር ግን ይሄ ጫማ ባለፈው ለኢድ ስግደት በበጠበጡ ጊዜ ሲሮጡ የጠፋው ጫማ ተሰብስቦ የተላከላቸው ይመስለኛል። ከሆነ ግን ከምር ነውር ነው። ኃጢአትም ነው። አይመስላችሁም…?

"…እየኮመታችሁ…!!