Get Mystery Box with random crypto!

'…ሰውየው የነካው ሰው፣ የጨበጠው፣ የሳመው ሰው፣ ያቀፈው፣ የዳሰሰው፣ ያቀረበውና ያሻሸው ሰው፣ ያ | ዘመድኩን በቀለ(ZemedkunBekele) (አድናቂዎች)

"…ሰውየው የነካው ሰው፣ የጨበጠው፣ የሳመው ሰው፣ ያቀፈው፣ የዳሰሰው፣ ያቀረበውና ያሻሸው ሰው፣ ያሳሳቀው፣ ያሞገሰው፣ ያወደሰው ሰው ይዘገይ እንደሁ እንጂ የዚያ ሰው መጨረሻው ወይ ሞት ነው፣ ወይ እስርቤት ዘብጥያ መወርወር ነው፣ ወይ ደግሞ በህዝብ ዘንድ መጠላት አክ እንትፍ መደረግ ነው የሚገጥመው።

"…ይሄ ብዙዎችን የገጠመ የቆየ የተለመደ ነገር ነው። አዲስ ነገርም አይደለም። እንጂ በዚህ እልል ያለ ደረጃ አንድ አሽቃባጭ መረን የለቀቀ ነውረኛ ለአፉ ለከት በሌለው ልጅ ላይ ብቻ የተፈጸመ ነገር አናስመስለው። ታስሮ ሲፈታ አያያዛቸው አሪፍ ነበር፣ እንክብካቤያቸው የተለየ ነበር፣ እስር ቤት ሳይሆን እናቴ ቤት የገባሁ እስኮመስለኝ ድረስ ነው የተንከባከቡኝ ለሚሉት ለዘንድሮ ታሳሪዎችም ድምጽ ልሁን ብዬም አልደክምም። አሽተው ይፈቱታል። በቃ ሂኢ…!!

"…ወላ ዶ/ር አምባቸው በሉት፣ ጄነራል ሰዓረ፣ ሲሳይ አጌና በሉት፣ ዳንኤል ክብረት፣ ታማኝ በየነ በሉት አቤል ሙልጌታ፣ ጃዋር መሀመድ ብቻ ሰውየው ትከሻውን የነካው ሰው፣ አብሮት ቆሞ የገለፈጠ ሰው መጨረሻው አያምርም። ኢትዮጵያንም እንዲህ እያቀፈ፣ እያሞካሸ፣ እያሻሸ፣ እያቆላመጣት እያንቆለጳጰሳት ነው በቁሟ ያደረቃት፣ የሬሳ ክምር ምድር ያደረጋት። በቀረው እናንተ ሙሉበት።

• ይሄ የሃገር ሃዘን፣ የልቅሶ፣ የዋይታ፣ የሞት ንጉሥ መልአከ ሞት የሆነ ሰው በእውነት አይቅረባችሁ። አይንካችሁ። አይዳስሳችሁ፣ አይጨብጣችሁ። አይሳማችሁ። አይተሻሻችሁ። አሜን ነው…?