Get Mystery Box with random crypto!

የመነኑት አለም ሰልችቷቸው የሰው ግርግር ተሰደው ቢሄዱ ከገዳሙ መንደር መች ሆነ እና ለ'ራ | የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

የመነኑት
አለም ሰልችቷቸው የሰው ግርግር
ተሰደው ቢሄዱ ከገዳሙ መንደር
መች ሆነ እና ለ'ራሳቸው ብቻ
ለ'ኛ ላሃጥያተኞች ለሆንን
ለዳቢሎስ መጫወቻ
በአለም እየኖርን ለሆን' አስመሳዮች
ሊጸልዩልን ነው ለ'ኛ እድለቢሶች
የመነኑትማ እንዴት ታድለዋል
ይህን አለም ንቀው መንግስቱን ናፍቀዋል
በአለም እየኖሩ
በክርስቶስ ፍቅር ልባቸው ታውሯል
እንዴት መባረክ ነው እንዴትስ መታደል
'ራስን ዝቅ አ'ርጎ ክርስቶስን መምሰል
መሆን ባይቻለን
ምን አለ ሕጉን ብንጠብቅ
ምንስ ይጎድለናል ከአምላክ ብንታረቅ
በአለም እየኖርን ሰክረን በንዋይ
ልባችን ደንድኖ ጠፍቶ አስተዋይ
መሆናችን ሳይታወቀን እንደ ትዕቢተኛ
ተዋርደን ሆነናል እኛስ ሀጥያተኛ
ሳጥናኤልም ቢሆን ክብሩን የተቀማው
በትዕቢቱ ነው ከጥልቁ የወደቀው
አለምንም ትተው ገዳም የመነኑ
ስለሀጥያተኞች አምላክን የሚለምኑ
በነሱ ፀሎት ነው እስካሁን ያለነው
እንደ ሀጥያታችን ዋጋ ያልከፈልነው
የላመ የጣመ ምግብ ሳያምራቸው
ቤት ገንዘብ መኪና ምቾት ሳያሳስባቸው
እፍኟን ባቄላ እሷኑ ቀማምሰው
በመሬት ተኝተው ድንጋይ ተንተርሰው
ዘውትር ሳይሰለቹ በሚፀልዩት
በእነርሱ ሀይል ነው በእነርሱ ፀሎት
አለም የቆመችው በመነኮሱት

ሰላም ቤዛ
ግጥሟን ከወደዳችሁላት ላይክ እና ሼር ተባበሯት

ለመቀላቀል

@zemaritnsae
@zemaritnsae