Get Mystery Box with random crypto!

አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ትግራይ ክልል የሚሄደውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቀላጠፍ የሚደረገውን ጥረት ተመ | Zehabesha

አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ትግራይ ክልል የሚሄደውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቀላጠፍ የሚደረገውን ጥረት ተመለከቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ወደ ትግራይ ክልል የሚሄደውን የሰብአዊ ድጋፍ ለማቀላጠፍ የሚደረገውን ጥረት በአፋር ክልል ሰርዶ ኬላ ተገኝተው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አወል አርባ እንዲሁም ሌሎች የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን መንግሥት ወደ ትግራይ ክልል የሚላኩ ሰብአዊ እርዳታዎች ለማሳለጥ እያደረገ ከሚገኘው ሁሉን አቀፍ ጥረት በተጓዳኝ አሸባሪው ህወሓት ለጥፋት ዓላማው ሊጠቀምባቸው የሚችሉ ቁሳቁሶች እንዳይተላለፉ በትኩረት እንዲሠራ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።