Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሽንፈትን አስተናግዷል! በ ካሜሮን አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የሰላ | Zeget😜😜😜️

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሽንፈትን አስተናግዷል!

በ ካሜሮን አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የሰላሳ ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ አንድ ሁለተኛ ጨዋታ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በኬፕ ቨርዴ አቻው 1-0 ውጤት ተሸንፏል ።

የኬፕ ቨርዴን የማሸነፊያ ግብ ጁሊዮ ታቫሬዝ አስቆጥሯል ።

ያሬድ ባየህ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በኩል በ12ተኛው ደቂቃ ላይ በቀይ ካርድ ተሰናብቷል ።

የዛሬውን ጨዋታ ውጤት ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ምድብ አንድ ላይ አራተኛ ደረጃን ላይ የተቀመጠ ሲሆን ኬፕ ቨርዴ ምድቡን በሶስት ነጥብ ከካሜሮን ጋር በተመሳሳይ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቀጣይ ጨዋታውን ሀሙስ ከአዘጋጇ ካሜሮን ጋር ያደርጋል ።