Get Mystery Box with random crypto!

ለለበሳችሁት ቆብና ቀሚስ፣ ለጨበጣችሁት መስቀል፣ ለተቀበላችሁት ክህነትና፣ ለተሾማችሁት እረኝነት ታ | ዳንኤል ገብረማርያም

ለለበሳችሁት ቆብና ቀሚስ፣ ለጨበጣችሁት መስቀል፣ ለተቀበላችሁት ክህነትና፣ ለተሾማችሁት እረኝነት ታምናችሁ ለመፍትሔ ሥሩ። ቸሩ አምላክ ይርዳችሁ።

ለማስታወስ ያህል አባቶቼ ሆይ በመግለጫ የሚቆም ግድያ እና በልመና የሚረጋገጥ የቤተክርስቲያን ፍትሕ ከቶ የለም። ግድያና መፈናቀሉ፣ ስደትና መከራው የሚያበቃው ፍትሕም የሚመጣው በሥራ እንጂ በልምምጥ አይደለም። ስለኾነም ቤተክርስቲያንን በሚመጥንና ዘመኑን በዋጀ መልኩ የተጠና የመፍትሔ ሥራ ይሠራ። ያሉን አማራጮች ኹለት ብቻ ናቸው፦ "ወይ ሥራ መሥራት ወይም ደግሞ በዝምታ ውስጥ ኾኖ መጥፋት"። እናም እኛ ልጆቻችሁ ስለቤተክርስቲያን አብዝተን እንጨነቃለንና ሥራ አሠሩን፣ በሚገባ ምሩን፣ እንደሥርዓቱና እንደትውፊቱ አስተዳድሩን። እባካችሁ አታሳፍሩን፣ አታስመርሩን፣ ለመከራ አትስጡን ተስፋም አታስቆርጡን። ልጆች ነንና ብንሳሳት አርሙን፣ ቡራኬያችሁም ዘወትር ይድረሰን። አሜን።

"እስመ በልዓኒ ቅንዓተ ቤትከ" እንዲል ቅዱስ ቃሉ በድፍረት ያይደለ በፍርሃት፣ በትዕቢት ያይደለ በትሕትና ስለቤተክርስቲያን በሚያቃጥል ፍቅር ውስጥ ኾነን እንዲህ ጠየቅን፣ ገና እንጠይቅማለንና እንደድፍረት አይቆጠርብን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

@zedaniel24 @zedaniel24