Get Mystery Box with random crypto!

ግንቦት ፩ ልደታ ለማርያም ልደቱ የኛ ወይስ የአንቺ? ባንቺ ልደት... መርገሙ ከራቀ | በእውነት ስለ እውነት

ግንቦት ፩ ልደታ ለማርያም

ልደቱ የኛ ወይስ የአንቺ?

ባንቺ ልደት... መርገሙ ከራቀ
በደል ከወደቀ
ጌታ ከወረደ
ሳጥናኤል ከራደ

ባንቺ ልደት....ዓመተ ፍዳ ተፈጽሞ
ምህረት ተሹሞ
ጌታ ከሰማይ ሊወርድ
ከኛ በስጋ ሊዛመድ

ባንቺ ልደት..የሀዘናችን ሰንሰለት..በሀዲስ ኪዳን ስትፈቺ
እመቤቴ ይኸ ልደትሽ...የኛ ልደት ነው ...ወይስ የአንቺ?

ስለዚህ እመቤታችን....

ልደትሽ ....ልደታችን ነው፡፡
አንቺ የወጣሽው...ከማህጸን ነው
እኛ ግን .....ከጨለማ ነው
ይኸውም...በልደትሽ ነው፡፡

#ሰአሊለነ_ቅድስት

እንኳ አደረሳችሁ!!!
ይህ ቀን የእመቤታችን ሳይሆን የዓለሙ ሁሉ ልደት ነው፡፡