Get Mystery Box with random crypto!

እንዳላጣሽ (በድሉ ዋቅጅራ) . . በመኖርሽ - ማለዳ ወፎች ሲዘምሩ፣ ዜማቸው ይገባኛል፤ በመኖርሽ | ግጥም

እንዳላጣሽ (በድሉ ዋቅጅራ)
.
.
በመኖርሽ -
ማለዳ ወፎች ሲዘምሩ፣
ዜማቸው
ይገባኛል፤
በመኖርሽ -
ምሽት ጉጉት ሲያሟርት፣
ሰቀቀኑ
ያስፈራኛል፤
በመኖርሽ -
ጨረቃን አድማስ ላይ ሳያት፣
ውበት
ድምቀቷ
ያጓጓኛል፡፡

ብቻዬን
የለኝም ቅኝት፣
ብቻዬን
የለኝም ስስት፣
ብቻዬን
የለኝም ጉጉት፣

እንዳላጣሽ፡