Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል ሁለት ስለ ወንጌል invest እናድርግ። 1ኛ ቆሮንቶስ 9 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁴ በእሽ | ዩአንገሊዎን

ክፍል ሁለት

ስለ ወንጌል invest እናድርግ።

1ኛ ቆሮንቶስ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ።
²⁵ የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።


ወዳጆች የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን እንዲሆን ስለ ወንጌል invest እናድርግ ስለ ወንጌል እንሩጥ የክርስቲያን ሕይወት እና ኑሮ ወንጌልን ማዕከል ያደረገ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳችን ሲናገር 1ኛ ቆሮንቶስ 9²³ በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።²⁴ በእሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት፥ ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ። ምን ማለት ነው እግዚአብሔር በወንጌል ውስጥ ባስቀመጠልና በጻሐፈልን መሠረት እንኖራለን ።።።ስለዚህ ሕይወታችን እና ኑሮችን በሙሉ ለክርስቶስ ወንጌል የሚገባ መሆን አለበት መጽሐፍ ቅዱሳችን እንደተናገረው ማለት ነው ፊልጵስዩስ 1፥27 “ ስለ ኑሮአችሁ እሰማ ዘንድ፥ ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ።”
ሕይወታችን በተመለከተ አገልግሎታችንን በተመለከተ ዘመናችንን በተመለከተ ሁሉ ስለ ወንጌል invest ማድረግ አለብን ስለ ወንጌል መሮጥ አለብን ። invest ስናደርግ ወይም ስለ ወንጌል ስንሮጥ እግዚአብሔር ባደለን ወንም እግዚአብሔር በሰጠን ነገር ላይ መሆን አለበት ጊዜአችንን ፍቅራችን ጉልበታችን እድሜአችንን ዘመናችንን በሙሉ እግዚአብሔር ባደለን ወይም በሠጠን ነገር invest ማድረግ አለብን ለምን ካለን የወንጌል ማሕበርተኞች እንድንሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን ማድረግ ስለሚገባን ወዳጆች እግዚአብሔር በሕይወት ያልሠጠን ነገር ነገር የለም ነገር ግን እግዚአብሔር የሰጠን መልሰን መስጠት ሲከብደን እንዲሁም የግላችን ለማድረግ ስንሞክር ከስኬት እንጎላለን ከእግዚአብሔር ደስታ እንጓላለን ደስታ አልባ ስኬት አልባ እንሆናለን ።
ስኬት የሚባል ነገር በሕይወታችን ሊታይ አይችልም ከእግዚአብሔር ፍቃድ ውጪ የሚደረጉ የስኬት ጉዞ ላም በሌለበት ኩበት እንደመልቀም ያህል ነው። ስለዚህ እንድንኖጥ በተፈቀደልን መንገድ በመሮጥ የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ማድረግ አለብን ።በተፈቀደልን መንገድ እሮጠን እናገኛለን invest አድርገን እንደሰታለን ስለዚህ እግዚአብሔር ስለሁሉም ስራችን ይከፍለናል ።
“የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው፥ እኛ ግን የማይጠፋውን።” 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥25 እንደሚለሁ ቃሉ የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ማድረግ እንድንችል እግዚአብሔር ፀጋውን ያብዛልን ።

https://t.me/Yoangeliwon