Get Mystery Box with random crypto!

“በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።” 1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23 ክ | ዩአንገሊዎን

“በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23

ክፍል አንድ

የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ነው።


እኛ ሁላችንም አሁን ባለንበት በዚህ ዘመን የወንጌል ጉዳ ጉዳያችን ነው ለማለት ድፍረት ይኖረን ይሁን? ቅዱሳን አባቶች ለወንጌል የከፈሉት ዋጋ ለወንጌል ያደረጉትን ትግል ተመልክተን የእኛን ዘመን ክርስቲያኖችን እያመዛዘንን ብናይ እውነት የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ነው ብለን ልንናገር ድፍረት እናገኝ ይሁን ? ቅዱሳን አባቶች ወንጌልን ሲሰብኩ የመጣባቸውን የመከራ ዶፍ ስቃይና እግልትት ለእምነታቸው የነበራቸው ቆራጥነት ኢየሱስን ለማሳየት እና ለሞተላቸው ለመኖር ያላቸው ፍላጎት ወንጌልን ለትውልድ ለማድረስ ያደረጉት ጥረት አስተውለን ይሁን?
በአገራችን በኢትዮጵያ የተሐድሶ ለውጥ ጥያቄ የፕሮስታንት አብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ ከምታውቃቸው ከ614 ዓመታት በፊት ተነስቶ እንደነበረ ያውም ሀገር ደም ተብላ መጠራት በነበረባት በጥንት ስሟ ኢባ ተብላ በምትጠረው በደብረብርሃን ከተማ በደም የታተመ ታሪክ እንዳለንስ እናውቅ ይሁንን?
ይህም የተሐድሶ ጥያቄዬ የወንጌል እውነትህ ያሸነፋቸው ስግደት ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ መሆንና ድነት በእምንት በክርስቶስ ብቻ የሚገኝ ነጻ ስጦታ መሆኑ የተረዱ ደቂቀ እስቲፋኖሳዊያን ወይም ክርስቶሳዊን በአስራ አምስተኛው ምእት ዓመት በኢትዮጵያ በነበረችው ቤተክርስቲያን ወደ ቃሉ የመመለስ ጥያቄ በይበልጥ የተነሳበት ዘመን መኖሩን አሁን ያለን ሰዎች ይሄን ታሪክ እናውቃለን ወይ?
በኢትዮጵያ ነገስተ ነገስት ታሪክ መካከከል ዓፄ ዘረዓ ያዕቆብ ለእግዚአብሔር በሚመስል ቅናት የወንጌል አርበኞችን ዘግናኝ ጭካኔ ይፈፅም እንደነበረ የሚነገልለት ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ለደቂቀ እስጢፋኖስና ለተከታዮቹ በተደጋጋሚ የሚያቀርብላቸው ጥያቄ ይሄን ይመስላል ነበር ።
መምራቹን ስደብ (ወንጌልን ያስተማራቸውን አባ እስጢፋኖስን ማለት ነው ) እንዲሁም ለእኔ ስገዱ የሚል ነበር እነርሱም በበኩላቸው ደማቸው እንደጎርፍ እየፈሰሰ ገላቸው እንደ ቋንጣ እየተተለተለ ደረታቸው በጦር ዓይናቸው በእሾህ እየተወጋ ንጉስ ፊት በቀረብ ቁጥር ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር አንሰግድም መምህራችንን አባ እስጢፋኖስን አንሰድብም በማለት የእግዚአብሔር ፍቅር ልባቸውን እንደሞላ ለስጋቸው ሳይሳሱ በእምነታቸው የንጉስን ጥያቄ ድል እንደነነሱ እንመለከታለን::
ታድያ እኛ ለራሳችን ምኞት በብዙ እየሰገድን በልባችን ያለውን የእግዚአብሔር ፍቅር ችላ እያልን የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ነው ለማለት አሁንም ድፍረት ይኖረን ይሁን? በእኛ ዘመን በነጻነትን ወንጌል ሰምተን በነጻነት እየኖርን የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ለመድረግ ለምን ከበደን?
የወንጌል ጉዳ ጉዳያቸው አድርገው በአገራችን በኢትዮጵያ ቅድሳን አባቶች ለትውልድ እውነተኛው ወንጌል እንዲደርስ የከፈሉትን መስዕዋትነት መምህር ብርክ ገበረ ሊባኖስ ተስፋዬ የሰው ያለህ በሚል መጽሐፍ ከፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ መጽሐፍ ለብቻ የለለቀሙትን የእስጢፋኖሳዋን ለወንጌል ያላቸውን ቆራጥነት ለእምነት ያላቸውን መሠጠት ያልደበረዘ ንፁ ወንጌል በመሥበካቸው ስግደት ለእግዚአብሔር ብቻ በማለታቸው የከፈሉትን ዋጋ ሲዘረዝሩ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ አስቀምጠዋል


1.በእጆቻቸውና እግርቻቸው ያሉትን ጅማቶች በምላጭ እየተለተሉ ያወጡባቸው ነበር ይህም ብርታት እንዳያገኙ ሽባ ለማድረግ ነው።
2.ምላሳቸውን ይቆርጧቸው ነበር ይህም ተቀባይ ያገኘውን ትምህርታቸውን ማስተማር እንዳይችሉ ለማድረግ ነው።
3.አፍንጫቸውን እና ጆሮቸውን ይቋርጧቸው ነበር ይህም በሰው ዘንድ አስጠሊታዎች እንዲሆኑ ነው።
4.ቋንጃቸውን ይቋርጧቸው ነበር ይህም ከቦታ ወደ ባታ ተዘዋውረው ማስተማር እንዳይችሉ ለማድረግ ነው።
5.በጋለ ጉጠት ወስፌ ዓይናቸውን ያወጡባቸው ነበር ይህም ወንጌልን ሰምተው ተከታይ ለመሆን የሚመጡት ለማስደንገጥ ነው።
6.በጋለ ብረት ፊታቸውን ይተኩሷቸው ነበር ይህም ሰው በሩቅ አይቶ እንዲርቃቸው ነው ።
7.ቀኝ እና ግራ ጉንጫቸውን በምላጭ በመተልተል የተለያዩ ቅርጾችን ያወጡባቸው ነበር ይህም የነገስታቱ ባሪያዎች ናቸው ለማለት ነው።
8.የላይና የታች ከንፈራቸውን በመግፈፍ ጥርሳቸውን ባዶ ያስቀሩ ነበር ይህም በሰው ዘንድ መሳለቂያ ለማድረግ ነው።
9.ዒላማ በማድረግ በጦርና በቀስት ይወጎቸው ነበር ይህም የሚፈራ ካለ ለማስፈራራት ነው።
10.አንዳንድ ሴቶችን ጡታቸውን ይቆርጣቸው ነበር ኃፍረተ ሥጋቸው ውስጥ እሳት ይጨምሩባቸው ነበር ይህም ድርጊት ከእነርሱ በኃላ የእስጢፋኖሳዎን ትምህር ለሚከተሉት ለማስፈራራት የተደረገ ጭካኔ ነው።
11.የእጆቻቸውን የእግሮቻቸውን ጣቶች አንድ በአንድ እያሉ ይቄርጦቸው ነበር ይህም የሕመም ነርቦች በጣቶቻቸው ጣፍ በብዛት ስላሉ ስቃዩ ሲበዛባቸው አቋማቸውን ይቀይሩ ይሆናል ተብሎ ነው።
12.የሚገርማችሁ በእንደዚህ አይነት ስቃይ አልፈው ሲሞቱ እንኳን መቃብር በመከልከላቸው ለአራዊት ይሰጡቸው ነበር። በኢባ ሀገር ማለትም በደብረብርሃን ከተማ የቀሩትን ደቂቂ እስጢፋኖሳዎ ንጉሱ ሰብስቦ ከአንገት በታች ቀብሮ በራሳቸው ላይ ፈረስ ያስጋልብ ነበር ሰዎቹ ክርስትና ቀርቶ ሰበዓዊነትም አልነበራቸውም ቄሳር ከዚህ የሚበልጥ ግፍ ምን ሠራ ።
ንጉስ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ በእንደዚህ አሰቃቂ ሁኔታ ደቂቀ እስጢፋኖሳዋን ጨፍጭፎ ከገደለ በኃላ በከተማዋ ላይ ታላቅ ብርሃን ሲበራ የከተማዋን ስም ደብረብርሃን በማለት ሰየመው መባል ያለበት ደብረብርሃን ወይስ ሀገር ደም
ይህን ለወንጌል የተከፈለውን መሥዋዕትነት ስናስብ አሁን በእኛ ዘመን ድረ ዘመናዊነት በተስፋፋበት እንዲሁም የነጻነት ኑሮን እየሮርን እውነትም የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ነው ለማተለት አሁንስ ድፍረት ይኖረን ይሁን ? ወንጌል ላልሰሙት ወንጌል ወንጌልን እንስበክ ስንባል የወንጌል ስራን የጥቂት ሰዎች አገልግሎት እንደሆነ እያሰብን የወንጌል ጉዳይ ጉዳያችን ይሆናል ወይ መልሱ እኛው ጋር ይቆይ ።

https://t.me/Yoangeliwon