Get Mystery Box with random crypto!

Abidulmajed Melese

የቴሌግራም ቻናል አርማ ymah9 — Abidulmajed Melese A
የቴሌግራም ቻናል አርማ ymah9 — Abidulmajed Melese
የሰርጥ አድራሻ: @ymah9
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 389
የሰርጥ መግለጫ

Information is more than anything.
ድብቅ ሴራዎች ይጋለጣሉ ።
አዝናኝ እና ቁም ነገር አዘል ቀልዶች ይለቀቃሉ።
ሰበዐዊነት ይዘከራል ፣ይዳሰሳል ።
አላማየ በዲኔ ላይ የመረጃ ክፍተት እንዳይኖር መስራት ነዉ ።
ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮ፦
1) ከቁርኣን፣
2) ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]
3) ከታማኝ ዑለማዎችና
4) ከትክክለኛ ቂያስ ተጠናቅሮ ይቀርብበታል።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-11 21:04:15 አይ ጉድ !።
ፓስተሮች ሆስፒታል ሂደው አይፈውሱም፡፡
ምክንያቱም እዛ ያለው በሽተኛ የእውነት በሽተኛ ነው፡፡

ሮበርት ሙጋቤ
https://t.me/YMAH9
16 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 20:46:10 አንድ ዛፍ ሲወድቅ ሁሉም ድምጹን ይሰማል፤ ጫካውን የሞላው ዛፍ ሲያድግ ግን ማንም አይሰማውም።"
ብዙ ሰዎች የሚመለከቱት እድገትህን ሳይሆን ውድቀትህን በመሆኑ ላለመውደቅ ጥረት አድርግ!!

መንቁል! !።
22 views17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 21:04:41 መጝሪብ አዲስ ታሪክ ጻፈች
====================
የዓረቡ ዓለም እንዳለ ሆኖ መላው አፍሪካን አኩርተዋል። በዘርፉ አዲስ ታሪክን ጽፈዋል።

ከሰሜን አፍሪካ አቅጣጫ → ሞሮኮ → አል-መጝሪብ

2 billion people are with Morocco

Thank you Morocco for making Africa proud

Morocco becomes the first African team to reach the semi-final of a World Cup tournament.

በሁሉም ማሸነፎቻቸው ሱጁድ ማድረግንና የፈለስጢንን ሰንደቅ ይዘው ድምፅ መሆንን ከደጋፊ እስከ ተጫዋች አሳይተዋል። በዘርፉ ስመ ገናና የሆኑ ሃገሮችን እየገነደሱ ዘልቀው መላው አፍሪካን፣ የዓረቡንና የሙስሊሙን ዓለም አኩርተዋል።


መጨረሻችሁ ይመር! እስከ ዋንጫው ዝለቁ! ይመቻችሁ

https://t.me/YMAH9
https://t.me/YMAH9
43 views18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 13:37:44 ቢራ ለምን ሆድ ያሳድጋል?

እንዳዉ ተከተሉኝ እማ እናተዉ ¡¡

ቢራ መጠጣት የሚያስከትለው መዘዝ ለወንዶች አሉታዊ ነው. ይህንን ራስጌ መጠጥ በተደጋጋሚ በሚጠጡበት ጊዜ በወንድ አካል ውስጥ የኢስትሮጅን (የሴት ሆርሞን) ይዘት ይጨምራል.

Oxford university ጥናቱን እዉቅና ከመስጠቱም በ ላይ የማይካድ ሀቅ ብሎታል ።
"የቢራ ሆድ" ተብሎ የሚጠራውን መፈጠርን ስለሚያስገኝ ከመጠን በላይ ብሉበርን ለማከማቸት አስተዋፅኦ ያደርጋል.

ይህ ብቻ አይደለም በ ሰዉነተ ዉስጥ የስብ መጠን በመጨመር ለግፊት እና መሰል አደገኛ በሺታዎች መንስዔ መሆን ችሏል ።
እንዲሁም ወደ ከባድ የሆርሞን ውድቀት ይመራል ፣ይህም የወንድ ልጂን የተስተካከለ ቁመና ባልዲ በሆዱ የተሸከመ ሰዉ አስመስሎ ያበላሻል እና የወንዶች የጤና ችግር ያባብሳል።
በ 21 ክፍለ ዘመን መች እንደሚወልዱ የማይታወቅ ብዙ ወንዶች አሉ! ።

አላህ የከለከለን ነገር በዉስጡ ምንም ህይር የለዉም: አልሀምዱሊላህ አላኒዕመተል ኢስላም ።
አብዱልመጂድ መለሰ
https://t.me/YMAH9
https://t.me/YMAH9
https://t.me/YMAH9
54 views10:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 09:48:40 #ስትሮክ

#ከኛ_ይወዳጁ! follow በማድረግ ዘላቂ የጤና መረጃዎችን ያግኙ!

1.ስትሮክ ምንድን ነው?

• የራስ ቅል (ጭንቅላት)ውስጥ ደም ሲፈስ
• ወደ ጭንቅላት ውስጥ የጓጎለ ደም ሲገባ
• ወደ ጭቅላት የሚገባው ደም ሲቋረጥ ነው።
እንደ አጠቃላይ ስትሮክ ማለት ከላይ በተጠቀሱት ምክንያት አንጎል ሲጠቃ ነው።

2. ሁለት አይነት ስትሮክ አለ።

ሀ. 1ኛው ኢስኬሚክ(Ischemic) ስትሮክ የሚባል ነው።
• ይህ አይነቱ ስትሮክ በሰውነት ውስጥ ባሉና በተለያዩ የደም ቱቦዎች ውስጥ ደም ይጒጉልና ከዚያም ወደ አንጎል በመሄድ የአንጒል ህዊሳትን ሲያውክና ሲያውክ የሚፈጠር ነው። ይህም የአንጎል ህዋሳት ግልኮስና ኦክስጅን እንዳያገኙ ያደርጋቸዋል። 80% የሚሆነው ስትሮክ በዚህ ምክናየት ይከሰታል።
ለ. 2ኛው ሄሞረጅክ(Hemorragic) ስትሮክ የሚባል ነው።
• ይህ ደግሞ ቀጥታ አንጎል ውስጥ ደም ሲፈስ የሚከሰት ነው።ምክናየቱ ደግሞ ከፍተኛ የደም ግፊት፡ የደም ቱቦዎች መሳሳትና መቅጠን ነው።

#ዋና ዋና የስትሮክ ምልክቶች ምን ምን ናቸው?
1. የእጅ፡ የእግርና የፊት መደንዘዝና መስነፍ
2. እይታን ማጣት
3. መናገር አለመቻል
4. ሌሎች የተናገሩንንም መረዳት አለመቻል
5. ድንገተኛና ከባድ የራስ ምታት
6. የሰውነትን ሚዛን መጠበቅ አለመቻል

ስትሮክን መከላከል ይቻላል?
• አዎ 50% መከላከል ይቻላል።
#ለስትሮክ #የሚያጋልጡ #ነገሮች
1. ከፍተኛ የደም ግፊት
2. የልብ ችግር(ሁሉም አይደለም)
3. ከቁጥጥር ያለፈ የስኳር በሽታ
4. የኰሌስትሮል መጠን መጨመር
5. ማጤስ
6. መጡኑ የጨመረ የአልኮል መጠጥ
7. ውፍረት
8. ጭንቅላትንና ልብን የሚመግቡ የደም ቱቦዎች ላይ ችግር ካለ።
• ወንድ መሆን፡ እድሜ ከ65በላይ ከሆነ፡ በቤተሰብ ካለና ጥቁር መሆን የመጠቃት እድል ከሌሎች አኳያ ይጨምራል።
#ስትሮክ ሁለት ደረጃ አለው።

1. Major Stroke የሚባል፡ ለማከብ አስቸጋሪ የሆነና ወድያው ገዳይ የሆነ ነው።
2. Minor Stroke የሚባል፡ የሚታከምና በህክምና ለውጥ ማምጣት የሚቻልበት አይነት ነው።


እንደ ማጠቃላያ


#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

#ስትሮክ ሊከሰትባቸው የሚችሉባቸው መንገዶች ሁለት ናቸው፡- በጭንቅላት ውስ በሚከሰት የደደም መፍሰ ወይም ወደ ጭንቅላት ሊደርስ የሚገባው የደም ፍሰት መቀነስ ወይም መቋረጥ ፡፡

#የስትሮክ #ህመም #ምልክቶች

ለመራመድ መቸገር ወይም ሚዛን አለመጠበቅ
ለመነጋገር መቸገር
የሰውነት ክፍል (እጅ ወይንም እግር) ያለመታዘዝ
የአይን ብዥታ
ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ የራስ ምታት
ግራ የመጋባት ስሜት

#ለበሽታው #ሚያጋልጡ #ሁኔታዎች

#እድሜ፡- በእድሜ በገፋን ቁጥር በስትሮክ የመጠቃት እድላችን ይጨምራል
#ጾታ፡- ስትሮክ በአብዛኛው በወንዶች ላይ እንደሚከሰት ጥናቶች ያመለክታሉ
#በዘር ሊተላለፍ እንደሚችልም ጥናቶች ያመለክታሉ
#የደም ግፊት መጨመር
#የኮሌስትሮል መጠን መጨመር
#ሲጋራ ማጤስ
በስኳር ህመም መያዝ
#የሰውነት ክብደት መጨመር
#ከዚህ ቀደም በስትሮክ መጠቃት

#ስትሮክን #የመከላከያ #መንገዶች

የደም ግፊት መጠናችንን ማወቅ እና የደም ግፊታችን ከፍተኛ ከሆነም በሚገባ ለመቆጣጠር መሞከር፡፡ የደም ግፊት መድሃኒት የምንወስድም ከሆነ በትክክል እና ያለማቋረጥ መውሰድ፡፡
የስኳር ህመም ተጠቂ ከሆኑ የስኳር መጠኖን መቆጣጠር
ጭንቀትን ማስወገድ
ሲጋራ አለማጤስ
የአልኮል መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ መጠጦችን አለመውሰድ
የምንጠቀመውን የጨው መጠን መቀነስ
ቅባት የበዛባቸውን ምግቦች ያለማዘውተር
በቀን ለ 30 ደቂቃ ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ወይም የእግር መንገድ መሄድ
የሰውነት ክብደትን መቀነስ

https://t.me/YMAH9
https://t.me/YMAH9
51 views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 14:12:58 የሀሰት ወሬ ነው ብሏል ፖሊስ

በአዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ልዩ ስሙ ጉራራ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በሚገኘው ከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት ከክልል ሰንደቅ ዓላማ መሰቀል ጋር በተያያዘ የተማሪ ህይወት አላለፈም ሲል ፖሊስ አስታወቀ።

በከፍተኛ 12 ትምህርት ቤት የኦሮሚያ ክልል ሰንደቅ ዓላማ እንዲሰቀል በሚደግፉ እና በሚቃወሙ ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ ችግር የአንድ ተማሪ ህይወት አልፏል ተብሎ የሚነገረዉ የሀሰት መረጃ ነዉ ሲል ፖሊስ በማህበራዊ የትስስር ገፆች የተሰራጨውን መረጃ አስተባብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው “በትላንትናው ዕለት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የአንድ ተማሪ ህይወት አልፏል በሚል የሚሰራጨው መረጃ የሀሰት ነዉ” ብሏል።

https://t.me/YMAH9
https://t.me/YMAH9
62 views11:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 11:55:13 ትሀን በዛ ብየ ቤቴን አላቃጥልም! ! ።
አመግል ብላ ተኩላ፣ አይኗን አጠፋች ቸኩላ!
~
በውስጣችን ያሉ ችግሮች ብዙ ዓይነት ናቸው። እነዚህን ችግሮች መተራረማችን የልእልናችን መሰረት ነው። "በላጭ ህዝብ ሆናችሁ" የሚለው ሰማያዊ አዋጅ ስር ለዚህ ብልጫ ሁለት ምሰሶዎች ናቸው የተጠቀሱት። ከኢማን በተጓዳኝ የተጠቀሰው በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ነው። የመተራረም እሴት በሌለበት ህዝባዊ አንድነት አይኖርም።
እግር ከወርች ጠፍረው ካሰሩን ችግሮች ውስጥ ታዲያ አንዱ ዘረኝነት ነው። የሚጎመዝዛቸው ቢኖሩ እንኳ በዚህ ጉዳይ ላይ ደጋግመን መነጋገር አለብን። በርእሱ መነሳት ውስጡ የሚደፈርሰው የችግሩ ሰለባ ነው። ዘረኝነት የእልፎችን ህይወት እየነጠቀ፣ ንብረት እያወደመ፣ ትዳር እያፈረሰ፣ ደዕዋ እያደናቀፈ ነው። ዘረኝነት የብዙዎችን ዐቂዳ እየናደ ነው። በዘረኝነት የተነሳ ከላ ኢላሀ ኢለላህ ገመድ ይልቅ ለዘር ትስስር ቅድሚያ እየተሰጠ ነው። ዘረኝነትም አይነት አለው። ላ ኢላሀ ኢለላህ የሚልን ሙስሊም ቋንቋው ስለተለየ ብቻ ያለምንም በደል ከኢ አማኝ ጋር ተሰልፎ መጨፍጨፍ በርግጠኝነት ነፍስ ማጥፋት ከሚባለው እጅግ ሰቅጣጭ ጥፋት የራቀ ጥፋት ነው። ይሄ ወደ ክህደት የሚሻገር ወንጀል ነው።
እንዲህ አይነትን ጥፋት ማውገዝና ማስተማር የሁሉም ኃላፊነት ቢሆንም የተሻለ ውጤት ለማምጣት ግን ሁሉም በራሱ ዘር ላይ ቢሰራ የተሻለ ነው። ምክንያቱም መካሪው ከሌላ ዘር ሲሆን ምክርን ከመቀበል ይልቅ በዘር ጥላቻ መፈረጅ ነው የሚታየው። መካሪው የራስ ሲሆን ግን ችግሩ ባይጠፋም ይቀንሳል። ስለዚህ የኦሮሞውን ኦሮሞው፣ የአማራውን አማራው፣ የትግሬውን ትግሬው፣ የአፋሩን አፋሩ፣ የስልጤውን ስልጤው፣ የጉራጌውን ጉራጌው፣ ... ሲናገረው የተሻለ ይሆናል። ሌላው ላይ እንደሚደረገው ተናጋሪውን በዘር ጥላቻ መፈረጅ አይኖርም። የሚያደርግ ቢኖር እንኳ ገበያ አያገኝም። ይሄ አንድ ነው።
በሌላ በኩል ቀደም ብየ እንደገለፅኩት ሁላችንም አንድ ህዝብ ነንና እከሌ ጋር የተከሰተውን ችግር ብሄራቸው ስለተለየ ብቻ ሌሎች ዝም ይበሉ እያልኩ አይደለም። ነገር ግን አንድ ጥንቃቄ ያስፈልገናል። ብዙ ጊዜ እንደሚስተዋለው መነቃቀፍችን፣ መተራረማችን ብሽሽቅ የተጫጫነው ሊሆን አይገባም። የፖለቲካ ነጥብ ማስቆጠሪያ እንዳይሆንም መጠንቀቅ አለብን። የሆነ ጥፋት በአንድ "የሌላ" ብሄር ሰው ሲፈፀም ሆ ብለን ተነስተን ከአጥፊው አልፈን ሌሎቹንም በጅምላ ስንጎነትል ብንውል ነገ "ከኛ" የሆነ በሽተኛ ተነስቶ ፀያፍ ቃል ሲናገር "እነሱም" በተራቸው በጅምላ ይነሳሉ። ጉዳዩ ከምክክር ይልቅ ብሽሽቅና ፉክክር ሆነ ማለት ነው። ስለዚህ ከጅምላ ፍረጃ ልንርቅ ይገባል። ችግሩንም ላንቀርፍ የችግሩ አካል ያልሆኑ ወገኖቻችንን ወይ ወደ ጠርዝ እንገፋቸዋለን። ወይ ያለ ጥፋታቸው እናሸማቃቸዋለን። ችግራችንን እንፈታለን ብለን ይበልጥ እንዳናወሳስበው እንጠንቀቅ። ችግር የምንፈታበት መንገድ የጋራ ቤታችንን ባገናዘበ መልኩ ይሁን። "ትኋን በዛ ብየ ቤቴን አላቃጥልም" የሚባል ድንቅ ብሂል አለ።

https://t.me/YMAH9
https://t.me/YMAH9
61 views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 11:31:22 #በኔ ላይ…

ከአነስ ኢብኑ ማሊክ (رضي ﷲ عنه) ተይዞ:  ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿من صلّى عليَّ صلاةً واحدةً، صلّى اللهُ عليه عشرَ صلواتٍ، وحطَّ عنه بها عشرَ سيئاتٍ، ورفعَه بها عشرَ درجاتٍ.﴾

“በኔ ላይ አንድን ሰለዋት ያወረደ አላህ አስር ሰለዋትን ያወርድለታል። አስር ሀጢያቱን ይሰርዝለታል። ደረጃውን በአስር ከፍ ያደርግለታል።”

አልባኒ በነሳዒ ዘገባ ውስጥ ሶሂህ ብለውታል: 1297

https://t.me/YMAH9
https://t.me/YMAH9
53 views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 09:15:09 በነገራችን ላይ ኦሮምኛ online መማር የምፈልጉ ወንድሞች እና እህቶች ይችን ቻናል ተቀላቀሏት ።
https://t.me/ormifa
https://t.me/ormifa
51 views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 08:09:12 ምንኛ  ልብ  የሚነካ  ሀዲስ  ነው !!!
========= =========

አቡዘር አል-ገፋሪ በዘገበው ሓዲስ ነብዩ (ﷺ)  ከጌታቸው ሲዘግቡ እንዲህ አሉ፡-

አላህ እንዲህ አለ “ እናንተ ባሮቼ ሆይ!

እኔ በደል መፈጸምን በራሴ ላይ እርም አድሪጌዋለሁ። በናንተ መካከልም በደልን መፈጸም እርም አድርጌዋለሁ። ስለዚህ አትበዳደሉ።
51 views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ