Get Mystery Box with random crypto!

ሁሉም ሽልማቶች ፈተናውን ላሸነፈው ናቸው! ፈጣሪ ሁልጊዜ እንለምነዋለን ህይወታችንን እንዲያስተካክ | ይሁዳ የጥበብ ልጅ ፩

ሁሉም ሽልማቶች ፈተናውን ላሸነፈው ናቸው!

ፈጣሪ ሁልጊዜ እንለምነዋለን ህይወታችንን እንዲያስተካክልልን ተጨማሪ እንዲሠጠን ብዙ ብዙ ጥያቄዋችን እናቀርብለታለን እርሱም ይሰማናል ፤ ነገር ግን ሲያደርግልን አናውቅም ምን እየሰጠን እንዳለ ፣ ከምን እያዳነን እንዳለ በፍፁም አንረዳውም ሁልጊዜ የጠየቅነውን ሁሉ በቀጥታ እንዲመለስልን እኛ ባልነው መንገድ እንዲከናወን እንፈልጋለን!

ወዳጄ የጠየቅከው ነገር ክብደቱ ምን ያህል ነው? በጣም አስፈልጎሀል ?የእውነት በህይወትክ ላይ ትልቅ ቦታ አለው? ታድያ ትላልቅ ነገሮችን በጠየቅከው ቁጥር ፈተናህ በዛው ልክ መብዛቱ ለምን አስከፋህ? ፈጣሪ እኮ ትልቁ መሻትህን እየሰጠህ ነው ታድያ መሸከም እንደምትችል ፣ በአግባቡ እንደምትይዝለት እና ምን ድረስ እንደሚገባህ ሳይፈትንህ እንዴት ይይህ አስታውስ እንጂ የምትፈልገውን ለማግኘት እኮ የሚገባህ ሰው መሆን አለብህ ስለዚህ ከስጦታው በላይ የሚገባው ሰው ስለመሆንና ፈተናህን ስለምታሸንፍበት መንገድ አስብ ሽልማቱማ በፈጣሪ እጅ ነው ስለሱ እሱ ያስብበታል፤ እመነኝ ይህን ስታደርግ ከሚገባህ በላይ ፈጣሪ ሲሰጥህ ታያለህ!

ብሩህ ምሽት ተመኘው
🇯 ‌🇴 ‌🇮 ‌🇳 🇺 ‌🇸 

​​​​​​​​​​​​
🇯 ‌🇴 ‌🇮 ‌🇳
#እኛ_ባለቅኔዎቹ_ነን መልካም ቀን
https://t.me/ytebeb
https://t.me/ytebeb
https://t.me/ytebeb
#ለተጨማሪም_አስተያየቶ_እና_ልምዶን_ለማካፈል @Yehudaw ☜
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌