Get Mystery Box with random crypto!

ድህረ-እውነት (post-truth) =================== * በሰው ልጅ እና በገሃዱ ዓለም | #ቁርጥራጭ ሀሳቦች በየቲ

ድህረ-እውነት (post-truth)
===================
* በሰው ልጅ እና በገሃዱ ዓለም መካከል የነበረው ግንኙነት ተበጥሷል፤
* የእውነት ጥያቄም አልፎበታል!! ጠንካራ የሆነ ወሬ ሁሉ እውነት ነው!!
አሁን የምንኖረው የድህረ-ዘመናዊው ዓለም አካል ‹‹Hyper Reality›› ወይም post-truth ይባላል፡፡ ይሄም ዘመን ‹‹ማንነት፣ እውነት…›› የሚባሉ ጥያቄዎችን መመለስ የማያስፈልግበት ዘመን ነው፡፡ አሁን ባለው ዓለም ውስጥ ዋናው ጥያቄ የእውነት ጥያቄ ሳይሆን አብሮ የመኖር ጥያቄ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ አስፈላጊው ነገር ዲስኩር ነው፤ ጠንካራ የሆነ ወሬ ሁሉ እንደ እውነት የሚቆጠርበት ዘመን ላይ ነን ያለነው፡፡ በመሆኑም፣ ከባህል ውጪ፣ ከፖለቲካ ውጪ፣ ከዲስኩር ውጪ፣ ከቋንቋ ውጪ ምንም ዓይነት እውነት የለም።
በድህረ-ዘመናዊው ዓለም ውስጥ አንድ ነገር እውነትም ሐሰትም መሆን ይችላል፤ ለምን? ምክንያቱም ከኋላ ማጣቀሻ ሪፈረንስ ስለሌለን፤ ነባራዊ የሆነ ሜታፊዚካዊ መሰረት ስለሌለን ፡፡ ስለ አንድ ነገር እውነት ወይም ሀሰት ለማለት በመጀመሪያ ስለ ገሀዱ ዓለም መስማማት አለብን፡፡ በድህረ-ዘመናዊው ዓለም ላይ ግን እንደዚህ ዓይነት ስምምነት የለም፤ We don’t have objective metaphysical foundation.
ይሄ ምን ማለት እንደሆነ የዘመናችንን የዕለተለት ህይወት እንደ ምሳሌ ወስጄ ላስረዳ፡፡ ለምሳሌ፣ አንድ ነገር እውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ጎግል ውስጥ ገብተህ ያንን ነገር Search ስታደርግ ብዙ ጊዜ ካገኘኽው፣ ያ ነገር እውነት ነው ማለት ነው፡፡ የዚያን ነገር እውነትነት የግድ ገሀዱ ዓለም ውስጥ ወጥህ ‹‹ይሄ ነገር ተፈጥሯል ወይስ አልተፈጠረም›› ብለህ መጠየቅ የለብህም፤ ወይም ደግሞ ዛሬ ፌስቡክ ላይ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች አንድን ፖስት ሼርና ላይክ ካደረጉት ያ ፖስት እውነት ነው፡፡ አሁን ዓለም እየሰራበት ያለው እውነታ ይሄ ነው። ‹‹ድህረ-እውነት (Post-truth)›› ማለት ይኼ ነው፡፡ በገሃዱ ዓለም እና በሰው ልጅ መካከል ያለው ግንኙነት ተቆርጧል፤ እውነትን ፍለጋ ወደ ገሃዱ ዓለም መሄድ አያስፈልግም፡፡
በድህረ-ዘመናዊው ዓለም ውስጥ “Rationality, Objective Truth, Universal Knowledge” ለሚባሉ ነገሮች ቦታ የለውም፤ እነዚህን ጥያቄዎችና ፍለጋዎች already አልፈናቸዋል፡፡ ድህረ-ዘመናዊው ዓለም ውስጥ universal የሆነ ዕውቀት የለም፤ መስማማት የሚባል ነገር የለም፡፡ ‹‹ወንበሩ አለ? ወይስ የለም? እኔ አለሁ? ወይስ የለሁም?›› የሚለው ጥያቄ ከ500 እና ከ600 ዓመታት በፊት የነበረ የእነ ዴካርት ጥያቄ ነው፡፡ አሁን ያንን ጥያቄ ትተነዋል፤ አልፈነዋል፡፡ አሁን ያለው ጥያቄ ‹‹ፍፁማዊ የሆነ እውነት በሌለበት፣ Legitimation Crisis ወይም ደግሞ የእሴት ግጭት ባለበት ዓለም ውስጥ እንዴት መኖር እንችላለን?›› የሚለው ጥያቄ ነው የበለጠ አስፈላጊ ሆኖ የመጣው።
ከፍልስፍና ትምህርት አንድ እንደቃረምኩት የከተብኩት