Get Mystery Box with random crypto!

ግሪክ እና ሮም ከመመስረታቸው ከአንድ ሺህ ዓመታት በፊት 'ድራቪዲያን' በመባል የሚታወቁ ኩሩ እና | የተሰባበሩ ፊደላት

ግሪክ እና ሮም ከመመስረታቸው ከአንድ ሺህ ዓመታት በፊት 'ድራቪዲያን' በመባል የሚታወቁ ኩሩ እና ታታሪ ጥቁር ወንዶች እና ሴቶች በኢንዱስ ሸለቆ ውስጥ ኃይለኛ ሥልጣኔን ገነቡ። ከእነዚያ መነሻዎች፣ በህንድ ውስጥ ያሉ የአፍሪካ ነገሥታት የክልሉን ንግድ፣ ባህል እና እምነት ሥርዓት አቀላጥፈውታል።

ዶ/ር ክላይድ ዊንተርስ፣ የ "Afrocentrism: Myth or Science? " ደራሲ፡ እንዲህ ሲል ጽፏል።

“ኢትዮጵያውያን ከህንዶች ጋር በጣም የጠበቀ ግንኙነት ነበራቸው። እንዲያውም በጥንት ጊዜ ኢትዮጵያውያን አብዛኛውን ሕንድ ይገዙ ነበር። እነዚህ ኢትዮጵያውያን 'ናጋ' ይባላሉ። ሳንስክሪትን (Sanskrit) የፈጠረው ናጋ ነው። በ500 ቅልደ. የጥንት የድራቪዲያን ሥነ ጽሑፍ ንባብ ስለ ናጋ ትልቅ መረጃ ይሰጠናል።
በህንድ ባህል ናጋ ማዕከላዊ ህንድን ከቪላቫር (ቦውመን) እና ሚናቫር (ዓሣ አጥማጆች) አሸንፈው ወስደዋል።"

በመቀጠል እንዲህ ይላል።

"የሕንድ ተረቶች እንኳን ለሥልጣኔያቸው መሠረት የጣሉትን የጥቁር ዘር ያከብራሉ፣ የሕንድ ቅዱሳን መጻሕፍትም መገለጥ {enlightenment ከኢትዮጵያ እንደመጣ ያረጋግጣሉ። እንዲያውም የሕንድ የመጀመሪያው አምላክ 'ሺቫ' (Shiva) የሚባል የተገመደ ፀጉር ያለው (አኹን ባሕታውያን ርና ራስተፈርያንስ የሚያዘወትሩት የፀጉር ዘዬ dreadlocked) ያለው ጥቁር ሰው ነው።

ግዙፍ የሺቫ መታሰቢያ በኮይምባቱሬ፣ ህንድ በአዲ ዮጊ የሚገኘውም የመጀመሪያው ሰው እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠራል፣ በሂንዱይዝም ውስጥ ሺቫ “አጥፊው” ተብሎ ይጠራል። ሺቫ የዮጋ አባት ነው።

ስለ ኢትዮጵያዊው ሻህዛዳ ኮጃ ባርባክ {Shahzada Khoja Barbak} ብዙም የሚታወቅ ነገር የለም። በ1487 የቤንጋል ግዛትን ድል አድርጎ የሐበሻ ሥርወ መንግሥት ስለመሰረተው ይኽ ኢትዮጵያዊው ግን ሲዲ እንደነበረ ይታወቃል። ሲዲ፣ ሲዲኽ፣ ሺዲ፣ ሳዋሂሊ ወይም ሀበሺ በመባል የሚታወቁት በህንድ እና በፓኪስታን የሚኖሩ ጎሳዎች ሲሆኑ የምስራቅ አፍሪካ ክልል ባንቱ ህዝቦች ናቸው።

ይኽ ንጉሥ ወደ ስልጣን እንደመጣም በአንድ ሰው እንደተገደለ ይነገራል። ቦታውን የወሰደው ማሊክ አንዲል ካን ሱልጣን {Malik Andil Khan Sultan} ነበር። ዙፋኑን ሲይዝ ማሊክ አንዲል ካን ስሙን ወደ ሰይፉ-ዲ-ዲን አቡል ሙዛፈር ፊሩዝ ሻህ
{Saifu-d-din Abul Muzaffar Firuz Shah}ቀይሯል ፣ በእርግጥም በሕንድ ታሪክ ውስጥ ጥበበኛ ፣ለጋስ፣ ንጉስ መሆኑን አስመስክሯል።

በስሙ በተገኙ ሳንቲሞች መሠረት፣ ከ1487-1490 ነገሠ። ለተገዥዎቹ ሰላምና መፅናኛን አስገኘ፣ “በቸርነቱ ተወዳዳሪ የሌለው”፣ “በብዙ ድካም እና ስቃይ ያከማቹትን ያለፉትን ሉዓላዊ ሀብቶች ለድሆች ሰጠ። ከቢብሊዮቴካ ሕንድ {Bibliotheca India} የተገኘ ታሪክ ለድሆች ያለውን ርኅራኄ ያሳያል፡-

የሚገርመው የወቅቱ የመንግሥት አባላት ይህንን ለድሆች የሚሰጠውን የበዛ ልግስና አልወደዱም እና እርስ በርሳቸው፡-

“ይህ አቢሲኒያዊ ያለ ድካምና ጉልበት በእጁ የወደቀውን ገንዘብ ዋጋ አያደንቅም። የገንዘብን ዋጋ የሚያውቅ የሚማርበትን መንገድ እና እጁን ከከንቱ አባካኝነት የሚከለክልበትን መንገድ መፈለግ አለብን።"

ከዚያም ንጉሱ በዓይኑ እንዲያየው እና ዋጋውን በማድነቅ ስብህናውን ከሃብቱ እንዲያጣብቅ ሀብቱን ኹሉ መሬት ላይ ሰበሰቡ። ንጉሱም ሀብቱን ባየ ጊዜ “ይህ ሀብት በዚህ ቦታ ለምን ተተወ?” ሲል ጠየቀ። የመንግስት አባላቱም “ይህ ለድሆች የሰጠኸው ሃብት መጠን ነው” አሉ። ንጉሱም “ይህ መጠን እንዴት ይበቃል? ያንሳል ሌላ ጨምሩበት።" አለ

ዛሬም በእርሳቸው በተገነባው የጋኡር (Gaur)
ከተማ መስጊድ፣ ግንብ እና የውሃ ማጠራቀሚያ መጎብኘት ይችላሉ።

.......ይቀጥላል




t.me/yetesebere