Get Mystery Box with random crypto!

በሕንድ እስከ መመለክ የደረሱ ኢትዮጵያዊ ነገሥታት አስደናቂ ታሪክ (ቱካ ማቲዎስ) on Fac | የተሰባበሩ ፊደላት

በሕንድ እስከ መመለክ የደረሱ ኢትዮጵያዊ ነገሥታት አስደናቂ ታሪክ

(ቱካ ማቲዎስ) on Facebook

ክፍል አንድ

፩፪፫፬፭፮፯፰፱፲

የቅዱሳት መፃሕፍት አስገራሚ እና ምስጢራዊ ማስረጃዎችን ብንተዋቸው እና ሣይንስ እንኳን የሚለውን ብናይ የመጀመሪያዎቹ ዘመናዊ ሰዎች (ሆሞ ሳፒያንስ) ቀደምት አፍሪካዊ ተወላጆች በመሆናቸው፣ የአፍሪካ ህልውና በአለም ዙሪያ በቅርብ ጊዜ የሰው ልጅ ዘመን ውስጥ በኖሩት የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ሊገለጽ ይችላል።

አፍሪካውያን የዚኽች ፕላኔት ቀደምት ተወላጆች መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፣ ጥቁሮች ብዙ የአለም ቀደምት ፣ ዘላቂ ስልጣኔዎችን እንደፈጠሩ እና እንደያዙ የሚያሳዩ ብዙ መረጃዎች አሉ።

ለዛሬ ወደ ጥንታዊቷ ሕንድ ጉዞ እናድርግ ፣ "ኢትዮጵያ ግዛቷ እስከ ሕንድ ነበር" ሲባል አብዛኞቻችን ሰምተናል ፣ በዚኽ ጉዳይ ላይ ምናልባት "ይኽም አለ ለካ?" የሚያስብሉ ተሰውረው የቆዩ ገራሚ መረጃዎችን እናያለን።

የኢትዮጵያ ግዛት ስለነበረችው ሕንድ
ኢትዮጵያዊ የሕንድ ነገሥታት አስገራሚ የአገዛዝ ታሪክ
ኢትዮጵያ ለሕንድ ለቻይና እና ለሩቅ ምሥራቅ ያበረከተቻቸው ለማመን የሚከብዱ ተሰጥዎዎች
{{የሚሉ ርዕሶችን በጥልቀት እና በሥፋት እንዳስሳለን}}

በአፍሪካ እና በህንድ መካከል ያለውን የመጀመርያ ትስስርን የሚያንፀባርቁ ልዩ ዋጋ ያላቸው ጽሑፎች ከ2,000 ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል።

በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን መገባደጃ አካባቢ ህንድን እንደጎበኘ የሚነገርለት የቲያናው 'አፖሎኒየስ'
“ኢትዮጵያውያን ከህንድ የተላኩ ቅኝ ገዥዎች ናቸው፤ አባቶቻቸውን በጥበብ ጉዳይ የሚከተሉ ቅኝ ገዥዎች ናቸው” የሚል እምነት ነበረው።

የጥንቱ ክርስቲያን ጸሐፊ 'ዩሴቢየስ' የሥነ ጽሑፍ ሥራ፣ “በአሜኖፊስ 3ኛ (ኃያሉ 18ኛው ሥርወ መንግሥት ጥንታዊ የግብፅ ንጉሥ) የኢትዮጵያውያን አካል ከሀገሪቱ ወደ ኢንደስ ተሰደደ፣ በናይል ወንዝ ሸለቆ ውስጥ ተቀመጠ የሚለውን ትውፊት ጠብቆታል። ” በማለት ተናግሯል።
እና አሁንም ሌላ የጥንት “ኢቲነራሪየም አሌክሳንደርሪ” የሚለው ሰነድ “ህንድ በአጠቃላይ ከሰሜን ጀምሮ እስከ ፋርስ የሚገዛውን በመቀበል ቆይቷል ፣ አኹን ደግሞ የግብፅ እና የኢትዮጵያውያን ተራ ነው” ይላል።
የዲዮዶረስ ሲኩለስ አስተያየትም (በ45 ዓ.ዓ. አካባቢ) ተመሳሳይ ጭብጥ አለው።

“ከኢትዮጵያ (ኦሳይረስ) በዓረብ በኩል አለፈ፣ በቀይ ባህር ላይ እስከ ሕንድ ድንበር ድረስ እና በጣም ሩቅ በሆኑት የባህር ዳርቻዎች ድንበር ተሻገረ። እንዲሁም በህንድ ውስጥ ብዙ ከተሞችን ሠራ፣ አንዱን ኒሳ ብሎ ጠራው፣ ያደገበትን በግብፅ የነበረውን (ኒሳ)'ን ለማስታወስ ፈቃደኛ ሆነ።" ይለናል

የሕንድ ታላቅ ወንዝ መጠሪያ የሆነው ኢትዮጵያዊው ንጉስ ጋንጌስ

ሳሙኤል ፑርቻስ ያስተላለፈው እና በጄ.ኤ ሮጀርስ የተጠቀሰው የኢትዮጵያ ንጉስ ጋንጌስ ታሪክ አለ። ጥቅሱ እንዲህ ይላል።

"ነገር ግን ከሁሉም (የኢትዮጵያ ነገሥታት) ጋንጌስ (Ganges) በጣም ዝነኛ ነበር፣ ከኢትዮጵያ ሠራዊቱ ጋር ወደ እስያ አልፏል ፣ ስሙን እስከተወለት 'ጋንጌስ' ወንዝ ድረስ ያለውን ሁሉ ድል አደረገ፣ ይኽ ታላቅ የሕንድ ወንዝ አስቀድሞ 'ክሊያሮስ' ተብሎ ይጠራ ነበር።

አንዳንዶች "ይኽ መሆኑ አኹን ላይ ምን ይጠቅማል?" ብለው ይጠይቁ ይሆናል ፣

ዳያካር ራኦ እንዲህ ይላል፡- "ጥቁሮች የበለፀገ የትውልድ መነሻ መሰረት ነጥባቸውን ካላወቁ ፣ እድገት እንደሚመጣ በማሰብ በማያልቅ ክብ መንቀሳቀስ ይቀጥላሉ"

ሕንድ ውስጥ ስላሉ ጥቁሮች ሲነሳ ምናልባት ብዙ ጥቁሮች በተለያዩ አለማችን ክፍሎች ይኖራሉ አሜሪካን ማየት ይቻላል የሕንዱን የሚለየው ታድያ ምንድነው? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፣
ህንድ ከአሜሪካ የተለየች ናት። በህንድ አብዛኛው ህዝብ የተቀላቀለበት የዘር ግንድ ሲኖረው በአሜሪካ ግን እንደዚያ አይደለም።

አሜሪካ ውስጥ አፍሪካውያን ከ1500 እስከ 1800
በባርነት ለ300 ዓመታት ተጓጉዘው በእርሻ ላይ እንዲያገለግሉ ተግዘዋል።
እነዚኽ ጥቁሮች የተለየ ቡድን ስነበሩ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ምንም ዓይነት ጋብቻ ከነጮቹ ጋር አያደርጉም ፣ ስለዚህ "አፍሪካውያን" የመጀመሪያውን የዘር ባህሪያቸውን ይጠብቃሉ።

አሁን ህንድን እንመልከት ፣ በህንድ ከአፍሪካ ስደት የጀመረው ከ50,000 ዓመታት በፊት ነው።

አርያንስ (=ነጭ) ወደ ህንድ የፈለሱት ከ4,000 ዓመታት በፊት ነበር። ለመጀመሪያዎቹ 2,500 ዓመታት ከአካባቢው ሰዎች ጋር ተጋብተዋል። በእነዚህ 2500 ዓመታት ውስጥ ጥቂት የአሪያን ያልሆኑ ገዥ ስርወ መንግስታት ይታሰባል።

'ሪግ ቬዳ' የተባለው እጅግ ጥንታዊው የህንድ መጽሐፍ እንኳን የአሪያን ያልሆኑ ነገሥታት ስሞች አሉት (ከ1500-1000 ቅልክ. አካባቢ ሊሆን ይችላል)።
ጥቁር ቀደምት የሕንድ ነገሥታት ከአርያን ነጮች ጋር ብዙ ጊዜ ጦርነት እንደገጠሙ ተጽፏል።

ባለፉት 1,500 ዓመታት (ከ500 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ)፣ በቅርብ ጊዜ በተደረገ አንድ የዘረመል ጥናት መሠረት፣ በ "ካስት ሥርዓት" ምክንያት ጋብቻው እየቀነሰ ሄደ።
( ስለዚኽ "ካስት" ስለሚባለው ጥቁሮችን ሆን ተብሎ በስነልቦና እና በአካል ለመስለብ የተዋቀረ ማሕበራዊ አስከፊ ሕግ በኋላ እናያለን)

ይኽም ኾኖ ጥቁሮቹ አልጠፉም - ትንሽ ሆኑ - ምክንያቱም በእነዚህ 1,500 ዓመታት ውስጥ በህንድ ውስጥ ኢንዶ-አሪያን ያልሆኑ በርካታ ገዥ ስርወ መንግስታት ነበሩ።

የገዥ ስርወ መንግስታት የአሪያን ያልሆኑ መሆናቸው አስፈላጊነት በነገስታት ላይ ምንም ገደብ ስለሌለ የአሪያን ሴቶችን ማግባት ይችላሉ ማለት ነው።

እያነሳሁ ያለሁት ነጥብ በህንድ ውስጥ እንደ አሜሪካ ያሉ 'አፍሪካውያን' እምብዛም የሉም። የህንድ ህዝብ ድብልቅ ነው። አፍሪካ-አሜሪካውያን በኢኮኖሚ የተሻለ የአሜሪካ ኢኮኖሚ አካል በመሆናቸው የተወሰነ ድምጽ አግኝተዋል። ሕንድ ውሥጥ ያሉ ጥቁሮች ግን እስካኹን በአስከፊ ባርነት ውስጥ እየማቀቁ ይገኛሉ።

በጃይፑር፣ ራጃስታን፣ ህንድን ድል አድራጊዎች እና ባሪያዎች ሆነው የመጡ የአፍሪካውያን ዘሮች ናቸው። ለዓመታት የህንድ መንግስት ከአፍሪካ ጋር ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ለመሸፋፈን፣ ምሁራን ከሚጠቃቅሱት እውነታ ሳይቀር ለማምለጥ ሞክሯል። ጭቆና ምንም ያኽል እንዳይወጣ ቢታፈን ቀዳዳ አያጣምና ፣ አፍሮ-ህንዶች ብቅ ማለት ጀምረዋል።

ህንድን የገዙ የአፍሪካ ነገሥታት

በምስራቅ አፍሪካ እና በህንድ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ በህንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ከ 2,000 ዓመታት በላይ ቆይቷል ።
ንግዱ ዛሬ ደቡብ እስያ እና ምስራቅ አፍሪካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያሳይ ረጅም ታሪክን ይጀምራል።

ብዙዎች በቅርቡ የተቀበሉት ፣ በሕዝብ ብዛት በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ ጥቂት የአፍሪካ ዝርያ ያላቸው ህንዶች መኖራቸውን እና ወደ ከፍተኛ ማሕበራዊ ደረጃ ከፍ ብለዋል ።

በጣም ጥቁሩ ሰው እዚህ በጣም የተከበረ እና ከሌሎቹ በጣም ጥቁር ካልሆኑት የተሻለ ነው ተብሎ ይታሰባል።

እኔ ልጨምር በእውነት እነዚህ ሰዎች አማልክቶቻቸውን እና ጣዖቶቻቸውን ጥቁር እና ሰይጣኖቻቸውን እንደ በረዶ ነጥተው ይሳላሉ። እግዚአብሔር እና ቅዱሳን ሁሉ ጥቁሮች ናቸው ፣ ሰይጣናት እና ክፉ መናፍስት ሁሉም ነጭ ናቸው ይላሉና። {ስለዚኽ ጉዳይ ማርኮ ፖሎ፣ በ1288 የፓንዲያን መንግሥት ከጎበኘ በኋላ ተናግሯል}