Get Mystery Box with random crypto!

አስታወስሽው....? በህልሜ እየመጣ... እንቅልፌን ያሳጣኝ፣ ፈገግታሽ ብቻ ነው... ጤናዬን የ | የተሰባበሩ ፊደላት

አስታወስሽው....?


በህልሜ እየመጣ... እንቅልፌን ያሳጣኝ፣
ፈገግታሽ ብቻ ነው... ጤናዬን የነሳኝ።

ጠረንሽስ ብትይ... ከንፋሱ በልጦ፣
የቤቴን ግድግዳ... እንደልብ ቆራርጦ፣
በጣም አውዶኛል... መንፈሴን አቅልጦ፣

አረ ልስላሴሽ... እሱስ መቼ አጣሁት፣
ሸካራው መዳፌ...
ከገላሽ ላይ ሲያርፍ : እራሴን እስክስት፣
አለም በቃኝ ብዬ...
ለማለፍ ሲዳዳኝ : ያሳለፍኩት ህይወት።

ደግሞ እነቃለሁ...
አሊያም 'ቃዣለሁ
ስምሽን ጠርቼ ... እምምሻለሁ።

ምንድን ነበር... መሐላው..?
አው ትዝ ይለኛል... አላስታውሰውም
አንቺን እኮ 'ማይሽ...በእውነት አይደለም።

አሁን አስታወስሽው...?
ወይስ ግራ ገብቶሽ... የፊቱንም ጣልሽው..?

አንቺ እኮ ህልም ነሽ...
እንኳን የመያዙ ... አንቺም ታመልጫለሽ፣
ግድ የለም ይረሳሽ... አንዴ ልለምንሽ፣

የበፊቱን አይተሽ... የተንከባከብኩሽ (በህልምም ቢሆን)
ብርዱ በረታብኝ...አየት አድርጊ ደርሰሽ


ንጉሡ ተሰማ(ጢያ)

t.me/yetesebere