Get Mystery Box with random crypto!

የስኬት ቁልፍsuccss quote

የቴሌግራም ቻናል አርማ yesktkulef — የስኬት ቁልፍsuccss quote
የቴሌግራም ቻናል አርማ yesktkulef — የስኬት ቁልፍsuccss quote
የሰርጥ አድራሻ: @yesktkulef
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 85
የሰርጥ መግለጫ

ለማንኛውም ሀሳብ ወይም አስተያየት
👇👇👇👇
@gezawit3294

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-09-08 17:57:23 "ለጠላቶችክ ደስታ ብለክ ሳይሆን መሸነፍክ ለሚያስከፋቸው ሰዎች ብለክ ጠንካራ ሁን"

ዛሬ ውስጥህ ሰላም አጥቶ መኖር አስጠልቶካል? ተስፋ እንዳትቆርጥ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ዛሬ ሰዎች ከሰው ክብር ዝቅ አርገውክ በሚጠሉክ ሰዎች ተከበሀል? የሚወዱክ ይመጣሉ፤ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ዛሬ ስንት የደከምክበት ቢዝነስ ብልሽትሽቱ ወጥቷል? ቀና በልና አማራጮችን ተመልከት፤ ነገ ሌላ ቀን ነው።

ዛሬ በትዕምርትህ የተዘጋጀከውንና የደከምክበትን ያህል ውጤት አላመጣህም? ትምርት በቃኝ እንዳትል፤ ነገ ሌላ ቀን ነው።

የተሸነፍከው የወደክ ፣ የተሰበርክ ቀን አይደለም። የተሸነፍከው በወደክበት ለመቅረት አምነክ የተቀመጥክና ዳግም መሞከር ያቆምክ ዕለት ነው።

በል ተነስ የእኔ አንበሳ ፤ ይቺ ምድር ለተሸናፊ ቦታ የላትምና "ለችግሮችህ በሙሉ ትልቅ ችግር ሁንባቸው።"
223 views14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-07 22:48:53 እንደምነሽ እቱ

እቴ ሆይ እንዴት ነሽ እንደምን ሰነበትሽ
አማን ሰላም ነው ወይ ከደጁ ከቀየሽ
መንገድ አካሄድሽ እንዴት ነው
ጎዳናሽ
ምሽትና ለሊት ቀንና አዋዋልሽ
እንዲያ እንደበፊቱ ገና ከመንጋቱ
ፀሀይ ከመውጣቱ
ማለዳ ተነስተሽ ነጠላን አንግበሽ
ድርሳን መፃፍ ይዘሽ ደጀ ሳሌም ሄደሽ
ፀሎት ታደርሻለሽ?
ተዚያ ተመልሰሽ ስራሽን ከውነሽ
ማድረግ ወዳለብሽ ወደዚያ ትሄጃለሽ?
ጓጉተሽ ሲመሽ ደሞ ልብሽ ለመሄድ ቆሞ
ቀሚሱን ጎትተሽ አጣፍተሽ ነጠላ
ከነፍስ ስንቅ አለም ከጉባኤ ተድላ
ከህይወት ምግብ ቤት ትቋደሻለሽወይ?
ወይስ ደሞ እቴ ሆንሽ ምናምንቴ
ፍለጋ ወተሻል ማንነትሽ ጠፍቶ
የሴትነት ወግሽ ማተብሽ ተፈቶ?
እኮ እንዴት ነሽ እቴ
ገና ከመንጋቱ ፀሀይ ከመውጣቱ
ያ ወዛሙ ፊትሽ በአመድ መንጣቱ
የቅንድብሽ ጥቁረት የከንፈር ቅላቱ
የልብስ ያለ የሚያሰኝ ያረግሽው እጥረቱ
ራስሽ በሁማንሄር ተከምሮ መታየቱ
እኮ ገና ከመንጋቱ አልሆንሽማ እቱ?
እቴ ሆነሻል ወይ ስራ ፈት
የስንቱን ልብ የሚያስት
ሆነሻል ወይ ተላካፊወጪ ወራጅ አሰላፊ
ገንዘብ ወዳድ ተሸናፊ
እግዜር የተለያት የጂኒ ጓደኛ
ሆነሻል ወይ እቴ በሱስ አደገኛ???
ጭንቀት ሊገለኝ ነው የቱ ተስማምቶሻል
የላይኛውን ነው የታቹን መርጠሻል?
ንገሪኝ እታለም እንደ ቀድሞ በይኝና
ይረፍ ልቤ ባንቺ በደስታ ይኩራና
ግን እንደታችኛው ከሆነ እንደኋላ
ንገሪኝ ላልቅሽልሽ ህርምሽን እንዳልበላ
በይ ንገሪኝ ከፊቱ ነሽ ከኋላ
የጥንቱ ማተብሽ ጠበቀ ወይ ላላ?


ሶሊ ነኝ(ቤቲ)
7:03am 18/12/2013ዓ.ም

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
251 views19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-31 21:20:46
#ለራሳቹ_መልካም_እይታ_ይኑራቹ

ማንም ስለናንተ ጉድለትና ውድቀት ሊናገር ይችላል፤ ሰዎች እናንተ ካለቹ እልፍ መልካም ነገሮች ይልቅ ጥቂቷን ስተታቹን ማጉላት ይቀናቸዋል፤ ምክንያቱም እንደነዚህ አይነት ሰዎች በጥቂቷ ስተታቹ ተጠልፋቹ እንድትወድቁ ስለሚፈልጉ ነው።

ማንም ስለ ስለናንተ ምንም ሊል ይችላል እናንተ ግን ለራሳቹ መልካም እይታ ይኑራቹ፤ የሌላቹን(የጎደላቹን) ነገሮች አግዝፋቹ ለራሳቹ አትንገሩት፤ ምክንያቱም እናንተ የሌላቹ ነገሮች ሁሉ ተደምረው ያላቹን አንዱንም እንኳ ስለማይበልጡ።
ጌታም ልክ እንደዚህ መስታወት ውስጥ እንዳለው አፕል ነው እኔና እናንተን የሚመለከተው፤ እግዚአብሔር ጉድለታችንን አያሳየንም ምክንያቱም የጎደለን ስለሌለ

የተወደዳቹ የአባቴ ብሩካን እናንተ በእግዚአብሔር ፊት ከሰማይና ከምድር ይልቅ ዋጋቹ እጅግ ታላቅ ነው፤ ከምንም በላይ ቅዱሱ የእግዚአብሔር መንፈስ ማደሪያ ናቹ፤ ስለዚህ ለራሳቹ መልካም እይታ ይኑራቹ
259 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-13 20:31:54 መነሳሳት


በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡
496 views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-13 20:30:11 የዛሬ 13 ዓመት የተጠና ጥናት ነበር....

አሁን እንዴት ሆኖ ይሁን ???


ይህ ጥናት እ.ኤ.አ. በ2008 የተካሄደ ነው፡፡
1. በአዲስ አበባ ብቻ ከ130 ሺ በላይ ሴተኛ አዳሪዎች አሉ፡፡
2. ከአዲስ አበባ ሕዝብ 19 በመቶ ጫት ይቅማል፡፡
3. በአዲስ አበባ ወደ 13645 የሚሆኑ መጠጥ ቤቶች አሉ፡፡
4. በአዲስ አበባ ወደ 1890 ጭፈራ ቤቶች አሉ፡፡
5. በኢትዮጵያ በብሔራዊ ደረጃ በየሁለት ደቂቃው አንድ ሕፃን በውርጃ ምክንያት ሕይወቱን ያጣል፡፡ በዓመት ቢሰላ ወደ 500 ሺ ይደርሳል፡፡
6. በአዲስ አበባ ካሉ የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤቶች 36 በመቶዎቹ ግብረ ሥጋን ይፈጽማሉ፡፡ ከዚሁ ውስጥ 11 በመቶዎቹ የፊንጢጣ ወሲብ /Anal sex/፣ 20 በመቶዎቹ በአፍ /Oral sex/ ይፈጸማሉ፡፡

የዛሬ 13 ዓመት የተጠና ጥናት ነበር....

አሁን እንዴት ሆኖ ይሁን ???
534 views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-20 22:31:26 ትንሽ ቦታ
ጎኔ ተንደላቆ ደልቶኝ የማድርበት፣
ማረፊያ አልጋ አልሻም መች ላንቀላፋበት፣
አዳራሽ አላልኩም ሙሉ ህዝብ የሚችል፣
ለፍቅር አጋፍቶ ለፀብ የሚያታግል
ትልቅ ሰፊ ቦታ አልሻም አዳራሽ
ቁስሌን ሚነካካ ህመሜን አባባሽ
በሁለት እግሮቼ ቆሜ ምስቅበት
በንፁህ ህሊና ደክምኝ የማርፍበት
አኩርፌ ብቻዬን ምተክዝበት
እስኪ ትንሽ ትንሽ ትንሽ ቦታ
ተጣልተን ማኩረፊያ
ታርቀን ምንስቅበት
እስኪ ትንሽ ትንሽ ትንሽ ትንሽ ቦታ
እስኪ ካለን ድንገት
ፍቅር እንገንባበት
ደግ ይሸመትበት
ህፆን ይደግበት
እስኪ እናስቀር ትንሽ ትንሽ ቦታ
ለክፍም ለደጉም ጊዜ አለን አለቃ

በ ግዕዛዊት ተፃፈ
( ፍቅርን ለናፈቁ ባለጊዜ የተከተበ)13/10/13 ዓ,ም
205 views19:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-16 21:03:40
የምትወደውን ሠው ስታይ ፈገግ በል እንደምቶደው ይረዳል ጠላትህን ስታገኝም ፈገግ በል ጥንካሬክን ይመለከታል ጥሎህ የሄደንም ሠው ስታገኝም ፈገግ በል ፀፀት ይሠማዋል የማታቀውን ሠው ስታገኝ ፈገግ በል ሰላም ያስገኝሀል
1.5K views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-16 20:41:08
በህይወትህ ውስጥ ከባዱ ነገር #መሳሳት አይደለም፣ለማስተካከል ምንም አለማድረግ ነው።ችግሩ ትላንት የገጠመን አስጠሊታ ነገር አይደለም ግን ካለፈውምንም አለመማር ነው። ሁሌም#ተሳሳትኩ ማለት የለብንም፡ግን ደግሜ#እንዳልሳሳት-ምን-ላድርግ ማለት ነው ያለብን አሁንም ደግመን ብንሳሳት ምን ላድርግ ማለት ነው። ያለብን አሁንም ደግመን ብንሳሳት ምን እማርበታለው ማለት ነው ያለብን፤ለዚች አጭር እድሜማ ስህተት ሰራሁ ብለን አንተክዝም! ውብ ምሽት ተመኘሁላቹ
390 views17:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-15 16:32:07
346 views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ