Get Mystery Box with random crypto!

አሰላሙዓለይክ ያሷሂበል ኢስራዕ ወል ሚዕራጅ! የአርሽን ከተማ ጂብሪል የፈራውን፣ በጫማው ሄደበት ሙ | ሁስነል ኹሉቅ

አሰላሙዓለይክ ያሷሂበል ኢስራዕ ወል ሚዕራጅ!
የአርሽን ከተማ ጂብሪል የፈራውን፣
በጫማው ሄደበት ሙሐመድ ብቻውን።
የኔ ነቢ ጌትዬው በሩሑል አሚን በሰደደላቸው የጥሪ ካርድ የአርሹ ድግስ ላይ ሲሐድሩ
ምድር ሸብ ረብ ብላ ነበር። የመኽሉቃቱ ሩሕ ሁሉ በያለበት ሆኖ "ሶለሏህ ዓላ ሙሐመድ!"
እያለ አጅቧል። ፍጡር የተባለ አንድም ሳይቀር ያንን ውድ ገና በጀርባው አሳርፎ
አጃኢበኛውን ጉዞ እንዲያደርግ እጣ በወጣለት ቡራቅ ቀንቷል።
አበደን አዲስ ነው ያንቱ መወለድ እንደሚሏቸው የተሰጧቸው ተዓምራትም ሰርክ አዲስ
ናቸውና የወርሃ ረጀቡን ክስተት ሁሌም እንዘክረዋለን! ውዱ ጌታዬ ለውዱ ረሱል ሰ.ዓ.ወ
የሰጠውን ለማንም አልሰጠም!ለ‘ርሳቸው ያሳዬውንም ለማንም አልገለጠም!ከስጦታዎቹም
ሁሉ በላጩ ሲዲቁ አቡበክር ረ.ዓ ሲቀሩ ሰዎች አይደለም በእውን በህልም እንኳን
መከሰቱን ለማመን የተቸገሩበት፣ የመካ ጣኦታውያን የተሳለቁበት፣ በተከበረው ረጀብ
ከመካ እስከ አቅሷ ከዚያም ወደ ሰማዬ ሰማያት ቡራቅ ጋልበው ያደረጉትና ተኝተው
የነበረበት ፍራሽ ሞቅታው እንኳን ሳይበርድ የተመለሱበት ከስሌት በላይ የሆነው የኢስራዕና
የሚዕራጅ ጉዞ ነው።
ለዚህም ነው አባቶቻችን
አይገርምህም ወይ ያ‘ላህ መለገስ፣
መካ ተወልዶ አርሽ ላይ መንገስ። ሲሉ ግርምታቸውን የገለፁት!
መወደዱንማ ኢሳም ተወደደ፣
መወደዱንማ ኑህም ተወደደ፣
ያለ ነቢ የለም በአርሽ የሰገደ። እያሉ የነቢን ልዩ መሆን ያንጎራጎሩት!
ዓመል ሁዝን ነበር የሀዘን አመት!ነብዬ ሁለቱን ታላላቅ ድጋፎቻቸውን እናታችንን ኸዲጃን
ረ.ዓ እና አጎታቸውን አቡ ጧሊብን ያጡበት!ግና ሳይደግስ የማይጣላው ጌታዬ ሃዘናቸውን
መርሻ፣ ላጡት መካሻ፣ ውድቀት እንዳይሰማቸው የበለጠ ከፍ ማድረጊያ ሰጣቸው!
ቀልባቸው በኢማንና በሂክማ ተዘፍዝፎ በጂብሪል አጃቢነት ከቀያቸው ወደ አቅሷ ገሰገሱ።
በመስጅደል አቅሷ ነብያቱን ሁሉ አሰልፈው በኢማምነት ካሰገዱ በኋላም ወደ ላይ ጉዞ
ጀመሩ። በዬ ሰማዬ ሰማያቱ ደጆች ያሉት ጠባቂዎች በደስታ እያሳለፏቸው የነብያቱን ሁሉ
ማረፊያ እያዩ እየዘዬሩ ቀጠሉ በይቱል መእሙርን ደገፍ ብለው የተቀመጡትን አባታችንን
ኢብራሂምን ዓ.ሰ እስኪያገኙ ድረስ። አሁንም ወደ ላይ አቀኑና ጂብሪል ዓ.ሰ "አንተ ተቀደም
ከዚህ በላይ አልተፈቀደልኝም!" ያለበት ሲድረቱል ሙንተሃም ዘለቁ። ከዛም "ቃበ ቀውሰይኒ
አው አድና" በተባለው አኳኋን እስከቆሙበት ደረሱ!
ኢስራዕ ጌትዬ እንዳለው ተዓምር ነው። የኔ ነቢ ጉዞውን እንዳጠናቀቁ ስለ ተዓምሩ የሰማው
አቡ ጀህል ሰዎችን ሰብስቦ አሳቀባቸው። ሌሎቹም አምኖ መቀበል ከበዳቸው። ኡሙሃኒያ
ከነገሩ አስደናቂነት የተነሳ ስለዚህ ጉዳይ ቢያወሩ ሰዎች ዋሾ ይሏቸዋል ብላ ፈርታ
እንዳይናገሩ ሐቢቢን አስጠንቅቃቸው ነበር። ይህንን ሳይ
ወገበ ቀጭን ትከሻው ሰፊ፣
ምነው በሆንኩኝ የ'ሱ አሳላፊ። እንዳሉት ምነው እኔም ኖሬ ሰዎች ዋሾ ሲሏቸው እንደ
ሲዲቅ ባመንኩ፣ ምነው ከጎናቸው ሆኜ የአንጀተ ቀጭኗን ሴት ጭንቀት በተጨነቅኩ፣
ምነው በታላቁ ሹመት የተደሰቱትን ደስታስ ባዬሁ ብዬ እመኛለሁ!
ቢሲሪል አስራር ኢስራዕ ወል ሚዕራጅ ለሀዘናቸው መፅናኛ የላከው ጌታ ከሃም ጘም
መውጫ ይላክልን፤ ሐጃችን ይሙላ፤ ነቢ የኔ ናቸው ይበሉን!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ዓላ ሰይዲና ወ መውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሰይዲና ሙሐመድ!


                             
                                
                                      
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ


  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡
እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ

@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄