Get Mystery Box with random crypto!

# ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ ! የኔ ነብይ የኛ ነብይ..! ሸፊዑል ሙዝኒቢን አሕመድ ኑሩ ዘይኔ! ጌትዬ እ | ሁስነል ኹሉቅ

# ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ !
የኔ ነብይ የኛ ነብይ..! ሸፊዑል ሙዝኒቢን አሕመድ ኑሩ ዘይኔ!
ጌትዬ እንኳን ለታላቁ ሙሐመድ ለሌላውም ደግ ባሪያ ሲል ሁሉን ያደርጋል። ሱልጣን ኢብን
አድሃም በአንድ ማለዳ በመንገዳቸው ላይ አንድ ጥንብዝ ብሎ ሰክሮ ትውከት ያስቸገረው
ወጣት ያያሉ። የሚገርመው ግን ወጣቱ ምንም እንኳን በዛ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም ደጋግሞ
"አሏህ አሏህ" ይል ነበር። ይሄኔ ኢብራሂም ኢብን አድሃም ለአሏህ ስም ጥራት ተጨንቀው
እንደ አሽከር ጎንበስ ብለው አፉን ያጥባሉ። ወጣቱ ከስካር እንደነቃ ሸይኹ በሠሩት ሥራ
ተማርኮ እዛው ተውበት ያደርጋል። በዚያው ቅጽበት ያ ወጣት ከደጋጎቹ ጎን መሰለፉን
ጌታቸው ይገልጥላቸዋል። ተገረሙ፤ ተደነቁ። ጌትዬውን እዬጠየቁ መንገዳቸውን ቀጠሉ።
"ይህ ሠው ከተውበቱ በኋላ አንድም ዒባዳ የለውም። ታድያ እንዴት ከቅርብ ወዳጆችህ
ተርታ ልታሰልፈው ቻልክ?" አሉት። "አንተ ለ’ኔ ብለህ ፊቱን አጠብከው፣ እኔ ደግሞ ላንተ
ብዬ ቀልቡን አጠብኩለት!" አላቸዋ።
የዓለሙን ራሕመት፣ በእዝነቱ ለእዝነት የላከውን፣ ዓይነታውን ሙሐመድ፣ ኸልቁን
አሷራፊውን፣ ወዳጁን ከርራሚውን፣ "ዑመቲ ዑመቲ" ብሎ ታጥቆ የሚያነባውን ነብይሳ?
ሰይደል ዓረቢ ወል አጀም፣ ጂስሙሁ ሙቀደስ ሙዕጦር ሙጥሀር፣ ሙነወር ፊል በይቲ ወል
ሐረም፣ ሸምሱዱሃ በድሩ ዱጃ፣ ሶድረል ዑላ፣ ኑረል ሑዳ ብለው የሚያወድሱትን ገበርሳ?
አንድ ደግ ሠው እንዲህ አሉ። "ነቢ በመናሜ ዘዬሩኝና አንድን ጥያቄ አነሳሁላቸው። ያ
ረሱለሏህ በአንድ ሶለዋት አሏህ አስር ሠላም የሚያወርድባቸው ሙእሚኖች ከልባቸው
ተመስጠው ሶለዋት የሚያወርዱትን ነው ወይስ በምላሳቸው ብቻ የሚያነበንቡትን? ረሱሉ
መለሱ። ‘ልጄ ሆይ በምላሳቸው ያለ ተፈኩር የሚያወርዱት ናቸው የአሏህን አስር ሶላት እና
ሰላም በምላሹ የሚቋደሱት። እነዚያ በኔ ላይ የተመስጦ ሶለዋትን የሚያወርዱትማ
የጀባታቸውን መቃም አሏህ እንጂ ማንም አያውቀውም’!"
ባደፈ ቀልባችን፣ ባልጠራ አንደበታችን፣ በሚንጎላጀጅ ዓይናችንም ቢሆን፣ ጥሪው ሸርጥም
ባይሞላ ስንጠራችሁ አትቅሩ እያልን አርሒቡ እንላለን አርሂቡ ነቢ ግቡልን። አይጠዬፉንም፤
ጌትዬውም ስማቸውን ሰምቶ በባዶ አይመልሰንም። መለኪያው፣ ሚዛኑ እኛ ሳንሆን
ሙሐመድ የሚለው ትልቁ ሥም ነው። "ዓለሙን ለርሱ ሲል የኸለቀው ጀሊል!" እንዳሉት
ለሙሐመድ ሲባል ሁሉ ይሆናል!
ያልነው ሁሉ ይሁንልን ነቢ መጀን!
ታግ የተደረጋችሁት በምክንያት ነው ውዶቼ! ከመሰሎቻችሁ ጋር ሁሉ የሶለዋቱ ሰዋብ
ይድረሳችሁ፤ አርሽ የተንቀጠቀጠለትን ወጣት ሶሀባ እጣ ለናንተ ያርገው፤ የዑማው አውራ፣
የዲኑ ዋልታና ማገር ያድርጋችሁ!እወዳችኋለሁ!
ሐይያ ዓለ ሶለዋት
# ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ !
አሏሑመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!



                             
                                
                                      
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ


  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡
እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ

@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄