Get Mystery Box with random crypto!

ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ውጥረት ለማርገብ ኬንያ ያቀረበችው የባሕር ጠረፍ ስምምነት ሃሳብ የ | YeneTube

ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ውጥረት ለማርገብ ኬንያ ያቀረበችው የባሕር ጠረፍ ስምምነት ሃሳብ የለም አለች!

ኬንያ የኢትዮጵያ እና የሶማሊያን ውጥረት ለማርገብ ቀጣናዊ የባሕር ጠረፍ አገልግሎት ስምምነት አማራጭ ለአገራቱ አቅርቤያለሁ ማለቷን ሶማሊያ ውድቅ አደረገች።

ኬንያ አቀረብኩት ያለችው አማራጭ በቀጠናው የሚገኙ የባሕር በር የሌላቸው አገራት በንግድ ስምምነት መሠረት የባሕር መተላለፊያ አገልግሎት እና ጥቅም የሚያገኙበትን ዕድል የሚፈጥር ነው ተብሎ ነበር።የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ ከኬንያ በኩል የተባለው ዓይነት የቀረበ ስምምነት የለም ብሏል።

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲዔታ ዓሊ ኦማር ባላድ “ሶማሊያ እና ኢትዮጵያን የሚመለከቱ የባሕር ጠፈር ስምምነት ዘገባዎች ሙሉ በሙሉ መሠረተ ቢስ ናቸው” ሲሉ ሚያዝያ 4/2016 ዓ.ም በኤክስ ገጻቸው አስፍረዋል።አክለውም “ሶማሊያ በግዛት አንድነቷ ላይ እንደማትደራደር” ጠቅሰው “በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ላይ ትኩረት እንዲደረግ” ጠይቀዋል።

@YeneTube @FikerAssefa